Thursday, September 15, 2011

መስቀሉ የት ነው ያለው? http://www.danielkibret.com/2010_08_01_archive.html

መስቀሉ የት ነው ያለው?

በእምነት ታሪክ ውስጥ የታሪክ፣ የአርኬዎሎጂ እና የቅርስ ጥናት ሰዎችን ያስጨነቁ ሁለት ጥያቄዎች አሉ፡፡ ታቦተ ጽዮን እና ጌታ የተሰቀለበት መስቀል የት ነው ያሉት? የሚሉት ጥያቄዎች፡፡ እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ አሰሳዎች፣ ቁፋሮዎች፣ መዛግብትን የማመሳከር ሥራዎች፣ አሉ የተባሉ የይዞታ ጥያቄዎችን የመመርመር ፍተሻዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ግን የዓለም ቅርሶች መናኸርያ የሆነችው ኢትዮጵያ ሁለቱንም በተመለከተ ለዓለም የምትገልጣቸው ነገሮች አሏት፡፡


ሰሞኑን በሀገራችን ኢትዮጵያ የመስቀል በዓል በመከበር ላይ በመሆኑ «ለመሆኑ ጌታ የተሰቀለበት መስቀል የት ነው ያለው?» የሚለውን ጥያቄ በተመለከተ ያሉ መረጃዎችን እንቃኝ፡፡

የመስቀሉ መጥፋት

በአብያተ ክርስቲያናት ከሚነገረው ትውፊት በስተቀር ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎት የነበረው መስቀል እንዴት ሊጠፋ እንደቻለ የተመዘገበ ታሪክ እኔ አላገኘሁም፡፡ አብዛኞቹ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ግን አይሁድ በመስቀሉ ላይ ይደረግ የነበረውን ተአምራት በመቃወም ከክርስቲያኖች ነጥቀው እንደ ቀበሩት ይተርካሉ፡፡ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ የቆስጠንጢኖስ የሕይወት ታሪክ /Life of Constantine/ በተሰኘው መጽሐፉ ላይ በክርስቲያኖች ዘንድ ታላቅ ሥፍራ የነበረው የጌታ መቃብር ተደፍኖ በላዩ ላይ የቬነስ ቤተ ጣዖት ተሠርቶ እንደ ነበር ይናገራል፡፡ አውሳብዮስ በዝርዝር አይግለጠው እንጂ ይህ የቬነስን ቤተ መቅደስ በጎልጎታ ላይ የመሥራቱ ጉዳይ የሮሙ ንጉሥ ሐድርያን በ135 ዓም ኢየሩሳሌምን Aelia Capitolina አድርጎ እንደ ገና ለመገንባት የነበረው ዕቅድ አካል ነው፡፡

አይሁድ በሮማውያን ላይ እስከ ዐመጹበት እና ኢየሩሳሌም ከክርስትና በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ እስከ ጠፋችበት እስከ 70 ዓም ድረስ መስቀሉ በክርስቲያኖች እጅ እንደ ነበር ይታመናል፡፡ በኋላ ግን ክርስቲያኖቹ የሮማውያንን እና የአይሁድን ጦርነት በመሸሽ ከኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ሌሎች ሀገሮች ሲሰደዱ፤ በኋላም በባር ኮባ ዐመፅ ጊዜ /132-135 ዓም/ ኢየሩሳሌም ፈጽማ በሮማውያን ስትደመሰስ የመስቀሉ እና የሌሎችም ክርስቲያናዊ ንዋያት እና ቅርሶች ነገር በዚያው ተረስቶ ቀረ፡፡ ንጉሥ ሐድርያንም የኢየሩሳሌም ከተማን ነባር መልክ በሚለውጥ ሁኔታ እንደ ገና ሠራት፡፡ ያን ጊዜ ነው እንግዲህ የቬነስ ቤተ መቅደስ በጌታችን መቃብር ላይ የተገነባው፡፡ ቆስጠንጢኖስ ለኢየሩሳሌሙ ኤጲስ ቆጶስ ለአቡነ መቃርዮስ በጻፈው እና ሶቅራጥስ እና አውሳብዮስ መዘግበው ባቆዩን ደብዳቤ ላይ ይህ ታሪክ ተገልጧል፡፡

ቀጣዮቹ 300 ዓመታት ለክርስቲያኖች የመከራ ጊዜያት ነበሩ፡፡ የሮም ቄሳሮች ክርስትናን እና ክርስቲያኖችን የሚያሳድዱባቸው ዓመታት በመሆናቸው መስቀሉን የመፈለግ ጉዳይ በልቡና እንጂ በተግባር ሊታሰብ አይችልም፡፡ ዓመታት እያለፉ ሲሄዱም ኢየሩሳሌም እየተዘበራረቀች እና የጥንት መልኳ እየተቀየረ በመሄዱ በጌታ መቃብር ላይም የሮማ አማልክትን ለማክበር ቤተ መቅደስ በመሠራቱ ነገሩ ሁሉ አስቸጋሪ እየሆነ ሄደ፡፡

የመስቀሉ እንደገና መገኘት

ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች መስቀሉን እንደገና ያገኘችው ንግሥት ዕሌኒ መሆንዋን ይናገራሉ፡፡ በ380 ዓም አካባቢ የተወለደው ታሪክ ጸሐፊው ሶቅራጥስ Ecclesiastical History በተሰኘው መጽሐፉ ላይ በምእራፍ 17 መስቀሉ እንዴት እንደ ተገኘ ዝርዝር መረጃ ይሰጠናል፡፡ ንግሥት ዕሌኒ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛ በጎልጎታ የጌታ መቃብር ላይ የተሠራውን የቬነስ ቤተ መቅደስ አፈረሰችው፤ ቦታውንም በሚገባ አስጠረገችው፡፡ በዚያን ጊዜም የጌታችን እና የሁለቱ ሽፍቶች መስቀሎች ተገኙ፡፡ ከመስቀ ሎቹም ጋር ጲላጦስ የጻፈው የራስጌው መግለጫ አብሮ ተገኘ፡፡

ሶቅራጥስ ከሦስቱ መስቀሎች አንዱ የክርስቶስ መሆኑን እንዴት ሊታወቅ እንደቻለ ሲገልጥ እንዲህ ይላል «አቡነ መቃርዮስ በማይድን በሽታ ተይዛ ልትሞት የደረሰችን አንዲት የተከበረች ሴት አመጡ፡፡ ሁለቱን መስቀሎችንም አስነኳት፤ ነገር ግን ልትድን አልቻለችም፤ በመጨረሻ ሦስተኛውን መስቀል ስትነካ ድና እና በርትታ ተነሣች፡፡ በዚህም የጌታ መስቀል የትኛው እንደሆነ ታወቀ» ይላል፡፡ ከዚያም ንግሥት ዕሌኒ በጌታ መቃብር ላይ ቤተ ክርስቲያን አሠራች፡፡ ከመስቀሉ የተወሰነውን ክፍል ከፍላ ከችንካሮቹ ጋር ወደ ቁስጥንጥንያ ስትወስደው ዋናውን ክፍል በጎልጎታ ቤተ ክርስቲያን ተወችው፡፡

ይህንን ታሪክ ሄርምያስ ሶዞሜን የተባለው እና በ450 ዓም አካባቢ ያረፈው ታሪክ ጸሐፊም Ecclesiastical History, በተሰኘው ጥንታዊ መጽሐፉ በክፍል ሁለት ምእራፍ አንድ ላይ ይተርከዋል፡፡ ዞሲማን እንደሚለው በ325 ዓም የተደረገው ጉባኤ ኒቂያ ሲጠናቀቅ የቆስጠንጢኖስ ትኩረት ወደ ኢየሩሳሌም ዞረ፡፡

ምንም እንኳን ሶዞሜን ባይቀበለውም መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ያመለከተው ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ ይኖር የነበረ አንድ አይሁዳዊ መሆኑን እና እርሱም ይህንን መረጃ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ከነበረ መዝገብ ማግኘቱን እንደ ሰማ ጽፏል፡፡ ንግሥት ዕሌኒ ባደረገችው አስቸጋሪ ቁፋሮ መጀመርያ ጌታ የተቀበረበት ዋሻ፤ ቀጥሎም ከእርሱ እልፍ ብሎ ሦስቱ መስቀሎች መገኘታቸውን ሶዞሜን ይተርካል፡፡ ከመስቀሎቹም ጋር የጲላጦስ ጽሑፍ አብሮ መገኘቱን እና የጌታ መስቀል ከሌሎች የተለየበትን ሁኔታ ከሶቅራጥስ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ይተርከዋል፡፡

ንግሥት ዕሌኒ በጎልጎታ፣ በቤተልሔም፣ በደብረ ዘይት፣ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርታ በሰማንያ ዓመቷ እንዳረፈች ሶዞሜን ይተርካል፡፡ ብዙ የታክ ጸሐፊዎች ዕረፍቷን በ328 ዓም አካባቢ መስቀሉ የተገኘ በትንም በ326 ዓም ያደርጉታል፡፡

በ457 ዓም አካባቢ ያረፈው ቴዎዶሮት የተባለው ታሪክ ጸሐፊም የመስቀሉን የመገኘት ታሪክ ተመሳሳይ በሆነ መንገድ ያቀርበዋል፡፡

መስቀሉ በኢየሩሳሌም

ንግሥት ዕሌኒ ለበረከት ያህል የተወሰነ ክፍል ወደ ቁስጥንጥንያ ከመውሰዷ በቀር አብዛኛውን የመስቀሉን ክፍል በብር በተሠራ መሸፈኛ አድርጋ በጎልጎታ ቤተ ክርስቲያን እንዲቀመጥ ለአቡነ መቃርዮስ ሰጥታቸዋለች፡፡ ይህ መስቀል በየተወሰነ ጊዜ እየወጣ ለምእመናኑ ይታይ እንደ ነበር አንዳንድ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በ380 ዓም ኤገርያ የተባለች ተሳላሚ መነኩሲት ቅዱስ መስቀሉ ወጥቶ በተከበረበት በዓል ላይ ተገኝታ ያየችውን ለመጣችበት ገዳም ጽፋ ነበር፡፡ /M.L. McClure and C. L. Feltoe, ed. and trans. The Pilgrimage of Etheria, Society for Promoting Christian Knowledge, London, (1919)/

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የመስቀሉ ክፍልፋዮች ወደ ተለያዩ ሀገሮች መወሰድ የጀመሩት በዚህ ጊዜ ነው፡፡ በሞሪታንያ ቲክስተር በተባለ ቦታ የተገኘውና በ359 ዓም አካባቢ የተጻፈው መረጃ የመስቀሉ ክፍልፋዮች ቀደም ብለው ወደ ሌሎች ሀገሮች መግባት እንደ ጀመሩ ያሳያል፡፡ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም መስቀሉ ከተገኘ ከሃያ አምስት ዓመታት በኋላ በ348 ዓም በጻፈው አንድ ጽሑፍ ላይ «ዓለሙ በሙሉ በጌታችን መስቀል ክፍልፋዮች ተሞልቷል» በማለት ገልጦ ነበር፡፡ ከዚህም ጋር «ዕጸ መስቀሉ እየመሰከረ ነው፡፡ እስከ ዘመናችንም ድረስ ይኼው እየታየ ነው፡፡ ከዚህ ተነሥቶም በመላው ዓለም እየተሠራጨ ነው፡፡ በእምነት ክፍልፋዮቹን እየያዙ በሚሄዱ ሰዎች አማካኝነት» ብሏል፡፡/On the Ten Points of Doctrine, Colossians II. 8./

ዮሐንስ አፈ ወርቅም የመስቀሉን ቅንጣቶች ሰዎች በወርቅ በተሠራ መስቀል ውስጥ በማድረግ ምእመናን በአንገታቸው ላይ ያሥሩት እንደ ነበር ጽፏል፡፡ በዛሬዋ አልጄርያ በቁፋሮ የተገኙ ሁለት ጽሑፎች የመስቀሉ ክፍልፋዮች በ4ኛው መክዘ የነበራቸውን ክብር ይናገራሉ፡፡ /Duval, Yvette, Loca sanctorum Africae, Rome 1982, p.331-337 and 351-353/፡፡ በ455 ዓም በኢየሩሳሌም የነበረው ፓትርያርክ ለሮሙ ፖፕ ለልዮን የመስቀሉን ቁራጭ እንደ ላከለት ተመዝግቧል፡፡

በአውሮፓ ምድር የተዳረሰው አብዛኛው የመስቀሉ ክፍልፋይ የተገኘው ከባዛንታይን ነው፡፡ በ1204 ዓም በአራተኛው የመስቀል ጦርነት ጊዜ የዘመቻው ተካፋዮች በዓረቦች ጦር ድል ሲመቱ ፊታቸውን ወደ ቁስጥንጥንያ አዙረው ከተማዋን፣ አድባራቱን እና ገዳማቱን ዘረፏቸው፡፡ በዚያ ጊዜ ተዘርፈው ከሄዱት ሀብቶች አንዱ ዕሌኒ ከኢየሩሳሌም ያመጣችው የመስቀሉ ግማድ ነበር፡፡ ይህንን ግማድ እንደ ገና በመከፋፈል አብዛኞቹ የአውሮፓ አብያተ ክርስቲያናት ሊዳረሱት ችለዋል፡፡ የወቅቱን ታሪክ ከመዘገቡት አንዱ ሮበርት ዲ ክላሪ «በቤተ መቅደሱ ውስጥ አያሌ ውድ ንዋያት ይገኙ ነበር፡፡ ከእነዚህም መካከል ከጌታ መስቀል የተቆረጡ ሁለት ግማዶች ነበሩ፡፡ ውፍረታቸው የሰው እግር ያህላል፤ ቁመታቸውም ስድስት ጫማ ይህል ነበር» ብሏል፡፡ /Robert of Clari's account of the Fourth Crusade, chapter 82: OF THE MARVELS OF CONSTANTINOPLE/

የመስቀሉ ለሁለተኛ ጊዜ መጥፋት

እስከ ስድስተኛው መክዘ ድረስ በኢየሩሳሌም ጎልጎታ የነበረው መስቀል በ614 ዓም በፋርሱ ንጉሥ ክሮስረስ 2ኛ /Chrosroes II/ ተወሰደ፡፡ የፋርሱ ንጉስ ኢየሩሳሌምን በወረረ መስቀሉን እና ፓትርያርክ ዘካርያስን ማርኮ ወደ ፋርስ ወሰዳቸው፡፡ እንደ ገና ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሰው ሕርቃል በ627 ዓም ባደረገው ጦርነት ክሮስረስ ድል ሲሆን ነው፡፡ ሕርቃል በመጀመርያ ወደ ቁስጥንጥንያ ካመጣው በኋላ እንደ ገና ወደ ኢየሩሳሌም ወስዶ በቀድሞ ቦታው በጎልጎታ አስቀምጦት ነበር፡፡

እስከ አሥረኛው መክዘ ድረስ በኢየሩሳሌም በቀድሞ ክብሩ ቢቆይም ዐረቦች አካባቢውን እየተቆጣጠሩ ሲመጡ በኢየሩሳሌም የሚኖሩት ክርስቲያኖች መስቀሉን በ1009 ዓም አካባቢ ሠወሩት፡፡ ለ90 ዓመታት ያህል ያለበት ቦታ ተሠውሮ ከኖረ በኋላ በመጀመርያው የመስቀል ጦርነት ጊዜ በ1099 ዓም ከተሠወረበት ወጥቶ እንደ ቀድሞው መታየት ጀመረ፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ መጥፋት

በ1187 ዓም በሐቲን ዐውደ ውጊያ ሳላሕዲን የተባለው የዓረቦች የጦር መሪ የመስቀል ጦረኞችን ድል አድርጎ ኢየሩሳሌምን ሲቆጣጠር በዚያ የነበረውን መስቀል መውሰዱን አንዳንድ የታሪክ መዛግብት ይገልጣሉ፡፡ ከዚያ በኋላ ግን መስቀሉ የት እንዳለ እስካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡ በወቅቱ የነበሩት የሮም ነገሥታት መስቀሉን ለማግኘት ከሳላሕዲን ጋር ብዙ ድርድር አድርገው ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡

በአብዛኞቹ ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የመስቀሉ ክፍልፋይ እንዳለ ሁሉም ይናገራሉ፡፡ አንዳንዶቹ አለ የሚባለው ክፍልፋይ ከመብዛቱ የተነሣ የሚያነሡት ትችት አለ፡፡ ጆን ካልቪን «ሁሉም ክፍልፋዮች ከመስቀሉ የወጡ ከሆነ፤ እነዚህን ሁሉ ብናሰባስባቸው አንድ መርከብ የግድ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ወንጌል ግን ይህንን መስቀል አንድ ሰው እንደ ተሸከመው ይነግረናል» ብሎ ነበር፡፡

ይህንን የካልቪንን ሂስ በተመለከተ መልስ የሰጠው ራውል ዲ ፈሌውሪ /Rohault de Fleury,/ በ1870 ዓም በዓለም ላይ አሉ በሚባሉት የመስቀል ክፍልፋዮች ላይ ጥናት አድርጎ ነበር፡፡ ራውል መጀመርያ የት ምን ያህል መጠን እንዳለ ካታሎግ አዘጋጀ፤ ከዚያም መጠናቸውን አንድ ላይ ደመረ፡፡ በታሪክ እንደሚነገረው የመስቀሉ ክብደት 75 ኪሎ፣ ጠቅላላ መጠኑም 178 ኪዩቢክ ሜትር ነው፡፡ ራውል ያገኛቸውና አሉ የተባሉት ክፍልፋዮች አንድ ላይ ቢደመሩ .004 ኪዩቢክ ሜትር /3.‚942‚000 ኪዩቢክ ሚሊ ሜትር/ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ቀሪው 174 ኪዩቢክ የሚያህለው ሜትር የመስቀሉ ክፍል ጠፍቷል ማለት ነው ብሏል፡፡ /Mémoire sur les instruments de la Passion, 1870/

ግማደ መስቀሉ በኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መዛግብት እንደሚሉት ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ የገባው በ14ኛው መክዘ በዐፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት ነው፡፡ በግሼን አምባ የተቀመጠው ደግሞ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን ወደ ኢየሩሳሌም ያደርጉ የነበረውን ጉዞ፣ የኢትዮጵያ ነገሥታት የነበራቸውን ታዋቂነት እና ወደ ሀገረ ናግራን ተጉዘው የሠሩትን ሥራ ስንመለከት ኢትዮጵያ እስከዚያ ዘመን ድረስ ግማደ መስቀሉን ለማግኘት ትዘገያለች ብሎ ለማሰብ ይከብዳል፡፡ በኢየሩሳሌም የሚገኘው የኢትዮጵያ ገዳም መስቀሉ ለወጣበት ቦታ እና ለጎልጎታ ያለውን ቅርበት፤ ዐፄ ካሌብም ከናግራን ዘመቻ በኋላ ዘውዳቸውን ለጎልጎታ ቤተ ክርስቲያን መላካቸውን ስናይ ይህንን የመሰለ ቅዱስ ንዋይ ኢትዮጵያውያን እስከ 13ኛው መክዘ ድረስ አንዱን ክፋይ ሳያገኙት ቆዩ ለማለት ያስቸግራል፡፡ ኤርትራ ውስጥ ግማደ መስቀሉ አለበት የሚባል አንድ ገዳም መኖሩን ሰምቻለሁ፡፡

ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ከሆነ በኋላ ነገሥታቱ በሳንቲሞቻቸው ላይ የመስቀል ምልክት ማድረጋቸው፣ እንደ ንጉሥ አርማሕ ያሉትም በበትረ መንግሥታቸው ላይ መስቀል ማድረጋቸው፤ ከቀደምት ክርስቲያን ነገሥታት አንዱ የሆነው ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ተብሎ መሰየሙን ስናይ የመስቀሉ ነገር በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውን ቀደ ምት ታሪክ ያመለክተናል፡፡

በዛግዌ ሥርወ መንግሥትም ዐፄ ላሊበላ ስመ መንግሥቱ ገብረ መስቀል መባሉን፣ ሚስቱም ንግሥት መስቀል ክብራ መባሏን፣ ከሠራቸው አስደናቂ ውቅር አብያተ ክርስቲያ ናት አንዱ ቤተ ጊዮርጊስ  በመስቀል ቅርጽ መሠራቱን ስናይ ኢትዮጵያውያን ከመስቀሉ ጋር ቀድመው መተዋወቃቸውን ያስገምተናል፡፡ በመሆኑም በዚህ ረገድ መዛግብትን የማገላበጥ እና የመመርመር ሥራ የሚቀረን ይመስላል፡፡

በዐፄ ዳዊት ዘመን መጥቶ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካኝነት በግሼን አምባ የተቀመጠው ግማደ መስቀል በይፋ የታወቀውና በነገሥታቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የመጣው ዋናው እንጂ የመጀመርያው ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡

ተክለ ጻድቅ መኩርያ ግብጻዊው ጸሐፊ ማክሪዝ Historia Rerum Isi amiticarumin Abissinia በሚለው መጽሐፉ የገለጠውን መሠረት በማድረግ «የኢትዮጵያ ታሪክ ከይኩኖ አምላክ እስከ ልብነ ድንግል» በሚለው መጽሐፋቸው ላይ እንደሚተርኩት አስቀድሞ በሰይፈ አርእድ ዘመን በግብጹ ሡልጣን እና በኢትዮጵያዊው ንጉሥ መካከል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ነበር፡፡ የልዑካን ቡድኑ መሪ የኢየሩሳሌሙ ፓትርያርክ አባ ዮሐንስ ነበሩ፡፡

ልዑካኑ ወደ ኢትዮጵያ ሲደርሱ ያገኟቸው ዐፄ ዳዊትን ነበር፡፡ በሁለቱ ሀገሮች መካከል የነበረውን ችግር በውይይት እና በስምምነት ፈትተው አስማሟቸው፡፡ ዐፄ ዳዊትም ግማደ መስቀሉን እንዲልኩለት የኢየሩሳሌሙን ፓትርያርክ አቡነ ዮሐንስን አደራ አላቸው፡፡ እርሳቸውም ከግማደ መስቀሉ ጋር ሌሎች ንዋያትንም ጨምረው ላኩለት፡፡ በግብጹ ሡልጣን እና በንጉሥ ዳዊት መካከል የተፈጸመው ስምምነት ለኢትዮጵያውያን ተሳላሚዎች እና ነጋዴዎች ጥበቃ ማድረግን የሚያካትት ስለ ነበር ግማደ መስቀሉን የያዙት የዐፄ ዳዊት መልእክተኞች ያለ ችግር ኢትዮጵያ ገቡ፡፡

አንዳንድ የታሪክ መዛግብት ዐፄ ዳዊት ጥቅምት ዘጠኝ ቀን 1404 ዓም በድንገት ሲያርፉ ግማደ መስቀሉ በሱዳን ስናር ነበር ይላሉ፡፡ ከስናር ያነሡት ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ መሆናቸውንም ይተርካሉ፡፡ ተክለ ጻደቅ መኩርያ ግን ዐፄ ዳዊት ወደ ኢትዮጵያ አስገብተውት በተጉለት ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት እንደ ነበር ይናገራሉ፡፡ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ የነገሡት በ1434 ዓም ነው፡፡ በእነዚህ ሠላሳ ዓመታትም አያሌ ነገሥታት ተፈራርቀዋል፡፡ እነዚህ ነገሥታት ግማደ መስቀሉን ለመውሰድ ያልቻሉበትን ምክንያት ማወቅ አይቻልም፡፡ ምናልባት ግን በነበረው የርስ በርስ ሽኩቻ ተጠምደው ይሆናል፡፡ ሌሎች መዛግብት እንጂ በኋላ ዘመን /ምናልባትም በዐፄ ልብነ ድንግል/ የተጻፈው የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ዜና መዋዕል የግማደ መስቀሉን ነገር አይነግረንም፡፡

ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ግሼን አምባ ላይ ግማደ መስቀሉን ያስቀመጠበት ሁለት ምክንያቶች ይኖራሉ፡፡ የመጀመርያው የአምባው የመስቀለኛ ምልክት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አምባው በዘመኑ በልዩ የንጉሠ ነገሥቱ ኃይል ይጠበቅ ስለ ነበር ነው፡፡ በግራኝ አሕመድ ወረራ ጊዜም ቢሆን ሌሎች ሀብቶች ከአምባው ላይ መዘረፋቸውን እንጂ የተቀበረውን ለማውጣት ሙከራ መደረጉን የግራኝን ታሪክ የጻፈው ዐረብ ፋቂህ አያነሣም፡፡

ግማደ መስቀሉን የማውጣት ጥረት ተደረገ የሚባለው በ1851 ዓም ዐፄ ቴዎድሮስ በጣም የሚወዷቸው ባለቤታቸው እቴጌ ምንትዋብ ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ ነው፡፡ ንጉሥ ቴዎድሮስ እቴጌ ምንትዋብን እጅግ ይወዷቸው ስለነበር በመስቀሉ አማካኝነት ከሞት ለማስነሣት አስበው ነበር፡፡ ይህንንም በወታደሮች ኃይል በማስቆፈር አስጀምረውት ነበር፡፡ በመካከል ግን ከጉድጓዱ ኃይለኛ ሽታ እና ጢስ ወጥቶ ከቆፋሪዎቹ የተወሰኑትን በመግደሉ ሃሳባቸውን ሠርዘው ባለቤታቸውን በግሼን አምባ ቀብረው ተመልሰዋል፡፡
 
 
ይቀጥላል

55 comments:

Haftu KALAyou said...
Diakon daniel kalehwot yasemaln
Dawit said...
በኢትዮጵያ የመስቀል በዓል ሲከበር የደመራ በዓል ትልቅ ቦታ አለው::ስለ ደመራ ሲነገር ደግሞ የአረጋዊው ኪራኩስ ታሪክም አብሮ የሚነሳ ነው::ይህ ጽሑፍ የደመራ በዓል መነሻ ታሪክን ድራሹን አያጠፋውም ትላላችሁ?
Anonymous said...
DANY REALLY U ARE DOING GOOD
I ALWAYS PRAY SO THAT MY GOD MAY BLESS U FOR THE SAKE OF NOT ONLY FOR U BUT ALSO FOR THE SPIRITUAL MINISTRY OPF THE CHURCH

KEEP YOUR SELF

FROM GONDAR
zegebriel said...
that is great dani. Gen yecheresekew sayemeselegn alekebegn. did u finidh it??????
Anonymous said...
Wedmachn Daniael,

Thank you very much for your well referenced article.
SendekAlama said...
+++

እውነት ለመናገር ይህንን ጽሁፍ ካነበብኩ በሁዋላ የማምነውም የማውቀውም ተጭበረበረብኝ። ሐይማኖትና ትውፊትን በተመለከተ የምትጽፋቸው ጽሁፎች በእርግጠኝነት «ሆነ! ተደረገ!» የሚሉ ቢሆኑ መልካም ይመስለኛል።

የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ በአንድ ወቅት ኢየሩሳሌምን ለመሳለም በኀብረት ሄደን በነበረበት ወቅት አስጎብኛችን በቁዋንቁዋና በሓይማኖት የማይመስለን ከአስጎብኚ ድርጂቱ የተወከለ ሰው በመሆኑ

- ጌታችን የተቀበረው እዚህ ነው ይለንና «አይ እዚያ ነው የሚሉም አሉ» ይለናል
- አብርሃም ይስሓቅን የሰዋበት ቦታ እዚህ ነው ይለንና «አይ እዚያ ነው የሚሉም አሉ» ይለናል
- እመቤታችን ጌታችንን እዚህ ዋሻ ውስጥ ወለደችው ይለንና «እነዚህ ዘንባባዋች መካከል ወለደችው» ብሉም የእስላሞችን መስጊድ ያሳዬናል
- የሙሴ መቃብር ይህ ነው ብሉንም አረፈው!

ሌላም ሌላም «ከተናገረው የደገመው» እንዲሉ ሊደግሙዋቸው የማያገቡ «ታሪኮችን» ከእምነታችን ጋር አደበላለቀብን። በእርግጠኝነት ያስተማሩን የአባቶቻችን ትምህርት ልቡናችን ውስጥ ባትኖር ኖሮና የፈረንጂን ቀሳጢነት አስቀድመን ባናውቅ ኖሮ በሕወታችን ስንመኘው ኖረን እንደ ፈቃዱ የፈጸመልንን ኢየሩሳሌምን የመሳለም ጉዞ ባዶ ባደረገብን ነበር።

ምንም እንኩዋን የኢየሩሳሌሙ ገጠመኛችን እና የዛሬው ጽሁፍህ ባይወዳደሩም እምነትንና ትውፊትን በተመለከተ ከአንተ ርግጠኛ ትምክርትን እንጂ የታሪክ ዳሰሳን እኔ በበኩሌ አለመርጥም።

የአገሬ ሰው ሠርግ ላይ ከአቅራራና ከፈከረ በሁዋላ «ማሩኝ» ብሉ ሽመሉን ይጥላልና እኔም በምንም መልኩ ጽሁፍህን እንጂ አንተነትክን ጥያቄ ውስች እንዳላገባሁ እንዲታወቅልንኝ እስክብርቶዬን ጥያለሁ።

ሰንደቅ አላማ
Anonymous said...
ቤተክርስቲያናችን ስለመስቀሉ መገኘት እና አከባበር የምታስተምረው ከዚ ጽሁፍ ጋር አይገናኝም
kindu said...
thank you d.daniel that was so fantastic. it's good to know the other side of the story of the Cross, this is what i think our fathers hide the Cross inorder to protect it from thiefs or outsiders that is way they say it is hiden. our fathers are so wise don't you think ? you teached us in 1999 in Durban south Africa about the founding of the Cross also that was contradict to this one i love both keep up the good work
can you please infform me where i can get the books of the 4th century fathers ?
Anonymous said...
"የካልቪንን ሂስ በተመለከተ መልስ የሰጠው ራውል ዲ ፈሌውሪ /Rohault de Fleury,/ በ1870 ዓም በዓለም ላይ አሉ በሚባሉት የመስቀል ክፍልፋዮች ላይ ጥናት አድርጎ ነበር፡፡ ራውል መጀመርያ የት ምን ያህል መጠን እንዳለ ካታሎግ አዘጋጀ፤ ከዚያም መጠናቸውን አንድ ላይ ደመረ፡፡ በታሪክ እንደሚነገረው የመስቀሉ ክብደት 75 ኪሎ፣ ጠቅላላ መጠኑም 178 ኪዩቢክ ሜትር ነው፡፡ ራውል ያገኛቸውና አሉ የተባሉት ክፍልፋዮች አንድ ላይ ቢደመሩ .004 ኪዩቢክ ሜትር /3.‚942‚000 ኪዩቢክ ሚሊ ሜትር/ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ቀሪው 174 ኪዩቢክ የሚያህለው ሜትር የመስቀሉ ክፍል ጠፍቷል ማለት ነው ብሏል፡፡ /Mémoire sur les instruments de la Passion, 1870/"


የሰውዬው ስም ፈረንሳዊ ነውና ስሙ ሮሆ ደ ፍለሪ ነው።

ቅዱስ መስቀሉ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከመጣብን መአት ያድነን!
ከፈለኝ said...
ቃለሕይዋት ያሰማልን የሁል ጊዜ ጥያቄየ ተመልሶልኛል ለመሆኑ ግን
ይህን መስቀል ያዩት አባቶች ሊኖሩ ይችላሉ ዳኒ
ሰይፈ ሥላሴ - ከባሕሬን said...
የጽሑፉ ዋና ጭብጥ ያለንን የመስቀል በዓል አከባበር ወይም ታሪክ የሚያጠፋ ሳይሆን ስለመስቀል ሌሎችም ሆኑ እኛ ኢትዮጵያውያን በደንብ ያልመረመናቸውና ገና ወደፊትም የሚያስደምሙ መረጃዎችና ምንጮች እንዳሉን የሚጠቁም ነው። በምናውቀው ብቻ እየተደነቅን ተወስነን እንዳንቀር ከእነ ዘርዓያዕቆብ መስቀል አስቀድሞም በሌሎቹ እጅ የገባው የመስቀል ክፍልፋይ በእኛ እጅ ሊገባ የሚችልበትን ሰፊ አጋጣሚ በእርግጠኛነት የሚያሳውቀን ነው። አመላካች ማስረጃዎችን መምህራችን ጠቆም ለማድረግ ሞክሯል።
ስለዚህም በዓሉን ከዚህ በበለጠ መንፈሳዊ ኩራት እንድናከብረውና ስለ መጀመሪያውንም መስቀል ታሪክም እንድናስብ የሚያደርግ ነው።
የሕይወትን ቃል ያሰማልን። መልካም የመስቀል በዓል
Anonymous said...
Dear Dn.Daniel,

I had a chance to a pay visit to Gishen Mariam and got lectured there regarding the holy cross. After I read yours I realized that there are some gaps.

Yours is merely dependent on some nonreligious books which probably be true or false.Moreover I found some gap with your article or I did not understand the case like after the third lost and its relation with Ethiopia. Even there is an other concept there in Gishew that is not officially known to any Christians.

To this end,I want to say that your concept is good but it requires additional clarification. Therefore I strongly suggest you to explore all truth about the holy Cross ,make sure you are not in line with the existing philosophy.

HM
Anonymous said...
በሚደንቅ መልኩ አጥሮ የቀረበልን የመምህራችን ጽሑፍ እጅግ ሰፊና ጥልቅ ምርምር የተደረገበት እንሆነ ያስታውቃል። ስለመስቀል በዓል አከባበር ወይም ታሪክ ስንነጋገር ዘርዓያዕቆብን እና ዘመኑን እያወሳን በቅርብ ታሪክ ብቻ ተወስነን ነው። ይኽም ቢሆን እኛንም ሆነ ሌላውን ዓለም የሚያስደምም በመሆኑ በዓሉ በሚደንቅ ሁኔታ በየዓመቱ ይከበራል። የጽሑፉ ጭብጥ ደግሞ በዓሉን ከዚህ በበለጠ ልናከብረት የሚስችለንን ከስድስተኛውና ከአምስተኛው መቶ ክ/ዘመን አስቀድሞ ከዚህኛው መስቀል በፊት ሌላው ዓለም የተከፋፈለው የመስቀል ክፋይ በመጀመሪያ እንደነበረ በእርግጠኛነት የሚያመላክቱንን የታሪክ ማስረጃዎች የሚያሳውቀን ነው። መምህራችን እንደገለጸው ከካሌብ እስከ ላሊበላ ያሉት ከመስቀል ጋር የተያያዙት ታሪኮች ለዚህ ፍንጭ እንደመሆናቸው መጠን እኛም በምናውቀው ብቻ እንዳንወሰን፣ ሌላውም ገና የሚደነቅባቸው ታሪክ እንዳለን እንድናስብና የታሪክ ተመራማሪዎችን ደግሞ ወደ ሩቅ ክፍለ ዘመናት ራቅ ብለው እንዲያጠኑና መረጃዎችን አሰናስለው እንዲያቀርቡ የሚጋብዝ ነው።
ለመምህራችን ረጅም እድሜን ከጤና ጋር እመኛለሁ። መልካም የመስቀል በዓል
ሰይፈ ሥላሴ - ከባሕሬን
Anonymous said...
Except for writings targeting doctrinal matters and/or spiritual development, I believe such academic researches are so much lacking in our church. What you are doing, Dn. Daniel, is very good in such areas. Some may say this or that isn't according to "tradition" but it is in my opinion good to bring into light what historical documents have to say. This may be the way to bring about open discussions both inside and outside the church.
I read sometime ago your research on the source of EOTC liturgies and people were complaining about it. But whatever you write complaints will always be there.
Write what you have to write! Let everybody have his own opinion.
Anonymous said...
ከኢየሩሳሌም እስከ ግሸን አድርሰህናልና ቃለ ህይወት ያሰማልን
Anonymous said...
Nice Study! Good translation :)
Anonymous said...
We need exploit facts from different directions!Because the fact is one and one!appreciate your efforts. God be with you!
Anonymous said...
Please also mention where you found this article too for further reading!
እኔ said...
አመሰግናለው

በዐፄ ዳዊት ዘመን መጥቶ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካኝነት በግሼን አምባ የተቀመጠው ግማደ መስቀል በይፋ የታወቀውና በነገሥታቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የመጣው ዋናው እንጂ የመጀመርያው ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡
ይህ ግን አልገባኝም
Anonymous said...
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡፡
የኔ አስተያተት ከላይ አስተያት ሰጪዎቹ እንዳሉት ከቤተክርስቲያን አስተምሮ ጋር ያለውን ዝምድና እና መለያየት ከምን የመነጨ እንደሆነ የሚገልጽ ምላሽ ብትሰጥበት የሚል ነው፡፡
እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልህ፡፡
ካሳሁን
T/D said...
@ Dawit yih tsihuf yedemeran beal endet dirashun yatefawal tilaleh. Sile meskel yeminimaribat and samint wist bizuwin bota yemiyizew sile demera yeminegerew new. Endih ayinet deep analysis (research) yebelete endinawik endinseram yiredanal biye asibalehu.

Dn Daniel thank you so much. Kale hiwot yasemalin. Egziabiher tsegawin yabzalih.
Anonymous said...
algebbagnimm!
Anonymous said...
***ስለ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ መግባት በሰፊው የሚያትተውን የብራናውን መጽሐፍ‹‹መጽሐፈ ጤፉትን›› እንዲሁም ሌሎች ጥንታውያን መጻሕፍትን በደንብ አድርጎ መመልከት ነው እንጂ እነ ተክለ ጻድቅ መኩሪያም ሆኑ ሌሎች የታሪክ ጸሓፊዎችን ዋና አብነት አድርጎ መጥቀስ ጥሩም ተገቢም አይደለም፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቹ ከአራት ምዕት ወዲህ ያሉ ታሪክ ጸሓፊዎች(የኢትዮጵያውያን ታሪክ ጸሓፊዎችም ጭምር) መነሻ የሚያደርጉት የውጭ ሃገር ጸሓፊዎችን ነውና.... የውጭ ሃገር ጸሓፊዎች ደግሞ በዋናነት ሁሉን ነገር ከኢትዮጵያ እንዲወጣ የሚፈልጉ ናቸውና .... ተቀባይነትና ተአማኒነት የለውም፡፡/ለዚህም ታላቁ ሊቅና መምህር አለቃ አስረስ የኔሰው የጻፉትን ‹ትቤ አክሡም መኑ አንተ› የሚለውን መመልከት ተገቢ ነው/፡፡ ዲ.ን ዳንኤል አንተም የምትጽፋቸው ጽሑፎችህ ጥሩ ቢሆኑም ብዙ ጊዜ በምንጭነት የምትጠቀመው የውጭ መጻሕፍትን ነውና ብተስተካክል....፡፡
***ወደ ኢትዮጵያ የገባው ግማደ መስቀሉ ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ባንዳንድ ዐይናማ ሊቃውንት መምህራን ዘንድ ደግሞ መስቀሉ ሙሉ ለሙሉ ነው ወደ ሃገራችን ኢትዮጵያ የገባው የሚሉም አሉና
ዲን.ዳንኤል ስለዚህ ብትጽፍ (አናባቢያንም ስለዚህ ነገር) ብትጽፉ ሳይሻል አይቀርም፡፡
Anonymous said...
Dn Daniel,

Your composition is good but I do not like this article it opens door so many criticisms for sure people use this article as reference for arguing negatively.
Please mention the saying or what EOTC says about.
Anonymous said...
It is a very good analysis. Meskel is one of the best celebration, i love it. But i think our knowledge about why it is celebrated colourfully is limitted. What i know was Eleni nigist demera demira bechisu akitacha eyetemrach meskelu yetekeberebetin bota agegnech askoferech agegnechiw. Our demera comemorates that, That was all I know. Here in Dn Daniel's research i got new insights as to how others percieve about the whereabouts of the Holly Cross. It is good to know the full story and then add with what we know from our church education.

The most important thing to me is believing in the power of the Holy Cross and giving due respect to church teachings about it. And knowing all the background info about it doesn't have any harm in our Meskel celebrations or beliefs.

God Bless You Dn Daniel.
Melkam yemeskel beal le Tewahedo lijoch bemulu
Anonymous said...
ደብረ ቁስቋም
አሁን ባለው ደረጃ አስተያየት መስጠት አይቻልም ምክንያቱም መጨተሻው ወይም ቀጣዩ ምን እንደሚል ማወቅ ያስፈልጋል የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣያል ይባል የለ.ለማንኛውም ግን እስከ አሁን ያለው ፅሁፍ በመስቀል ዙርያ ላይ ትልቅ ጥናት እንድሚያስፈልግ ጠቁዋሚ ነው.መልካም በዓል ለሁላችሁ.
አምላከ ቅዱሳን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን.
Anonymous said...
ሰላም ላንተ ይሁን ዳኒ እግዚአብሄርም እውቀትህን አብዝቶ ባርክ…..አሜን፡፡

ጽሁፎችህን በጣም አድርጌ እከታተላለሁ ብጣምም እወዳቸዋለሁ…..እስከዛሬም እውቀትህን በማድነቅ አምኜ ተቀብያለሁ…… በጣም ይቅርታ አድርግልኝና የዛሬውን ግን ከዚህ በፊት በቤተክርስቲያናችን ከልጅነቴ ጀምሮ ከተማኩትና አምኜ ከተቀበልኩት ትምህርት እጅግ የተለየ ነው፡፡ እውነት ለመናገር እኔ በመስቀል ላይ ያለኝ እውቀት ትንሽ ቢሆንም አይሁድ ተአምር ያደርግ የነበረውን የጌታችንን መስቀል ከክርስቲያኖች ለመደበቅ ሲሉ ቆፍረው ቀብረውት እንደነበርና ለዘመናትም ቆሻሻ ይደፋበት እንደነበር እና ንግስት እሌኒም የጌታዬን መስቀል ማግኘት አለብኝ ብላ በምትፈልግ ጊዜ የልቦናዋን ቅንነት ተመልክቶ ጌታ ባነደደችው ጭስ አማካኝነት እንደመራት እና የጌታንም እውነተኛ መስቀል እንዳገኘችው ነው የተማርኩት፡፡ በዚህም ደግሞ ሁልጊዜ በመስከረም 16 ደመራ በማብራት እንደምናከብረው አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን አገራችን ውስጥ ያለው ግማደ መስቀል እውነተኛ መሆኑን እና በግሸን ደብረ ከርቤ እንደሚገኝ ተምሬያለሁ፡፡ አረ ምን እሱ ብቻ በቅርቡ ያነበብኩት አንድ መጽሐፍ ደግሞ አንተ እንደምትለው የተሰነጣጠረ ሳይሆን ሙሉው መስቀሉ እኛ ጋር እንደሚገኝ አንቢቤያለሁ፡፡ ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ ‹‹ በዐፄ ዳዊት ዘመን መጥቶ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካኝነት በግሼን አምባ የተቀመጠው ግማደ መስቀል በይፋ የታወቀውና በነገሥታቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የመጣው ዋናው እንጂ የመጀመርያው ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡›› የሚል ነገር ካንተ አነበብኩ…..ይሄ ደግሞ ምን ማለት ይሆን……. በጣም ብቻ ግራ ተጋቻለሁ……… እውነተኛው የጥኛው እንደሆነ ግን ማወቅ እፈልጋለሁ………

እግዚአብሄር አብዝቶ ይባርክህ…..አሜን፡፡

Harry from Addis Ababa
Mahlet said...
Thank you Dn Daniel for distinguishing the tale tale from the reality and the fact.This is a well researched writing with a balance of history,fact and truth
Look forward to read the next part.
Anonymous said...
dejen
I am cofused now,most the histories that you mentioned I never heared of them, it is completely different from my parents thoght.
Anonymous said...
የኔ አስተያተት ከላይ አስተያት ሰጪዎቹ እንዳሉት ከቤተክርስቲያን አስተምሮ ጋር ያለውን ዝምድና እና መለያየት ከምን የመነጨ እንደሆነ የሚገልጽ ምላሽ ብትሰጥበት የሚል ነው፡፡
I agree with this comment.
ቬሮኒካ.ts. said...
በቅድሚያ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ አደረሳችሁ፡፡
ዲ/ዳንኤል ቃለ ሕይወት ያሰማልን፣ የአገልግሎት ዘመንህን ይባርክልን!!
ዳኒ ይህ ጽሑፍ አቀራረቡ በጥናት ያገኘኸውን እንጂ እስከዛሬ የመስቀል በዓልን ስናከብር የተማርነውን አይደለም፡፡ ለምሳሌ ለመስቀሉ መገኘት የነበረው የኪሪያኮስ አስተዋጽኦ፣ እስራኤላዊያን ቦታውን ቆሻሻ መድፊያ አድርገውት ነበረና በጊዜ ብዛት ተራራ በመፈጠሩ መስቀሉ የተቀበረበትን ተራራ ለመለየት ያደረጉትን ጥረት፣ ስለዕጣኑ ጢስ፣ እናም ግማደ መስቀሉ ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ግሸን የተመረጠበት ምክንያት “አንብር መስቀልየ በእደ መስቀል መስቀሌን በተመሳቀለ (በመስቀለኛ) ቦታ አስቀምጥ መባል በእርግጠኝነት የተማርነው በአንተ ጥናት ላይ በይሆናል መጻፉ

ሌላው ደግሞ
“በዐፄ ዳዊት ዘመን መጥቶ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካኝነት በግሼን አምባ የተቀመጠው ግማደ መስቀል በይፋ የታወቀውና በነገሥታቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የመጣው ዋናው እንጂ የመጀመርያው ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡” የሚለው በፍጹም አልገባኝም የበለጠ ብታብራራው

ለተቀማጭ ሰማይ … እንደሚባለው ሆኖብኝ የአንተን ጥናት ለመተቸት ሳይሆን እራሴን ለማሳተፍ ነው
ቀጣዩን በጉጉት እጠብቃለሁ
መልካም በዓል
KaleAb said...
Well well, Dn. Daniel, Did you just touch the untouchable?
When you dig deeper to study church matters, you better be ready for what you'll find. There is so much stuff in our church that is not supported by sound researched and documentation. We just accept it because that is what we've been told and we consider it part of our faith.
Dn. Daniel, I think you need make it clear to everyone whether you believe what you found in research or do you still accept what we have been taught in our church.

To the readers, we need to understand that every part of the church's teachings, other than the Dogma, can be questioned, re-examined and changed if needed.

We need to be open to ideas that challenge our long held believes and be free to discuss this matters. This will not dangerous at all in my opinion. In fact what is dangerous is to leave questions unanswered and open door to the heretics.
Anonymous said...
በስመ ሥላሴ ዲ/ዳኒ ምንድነው ያስነበብከኝ አሰኘኝ ብቻ ቀጣዩን እጠብቃለሁ የቤተክርስቲያን እምላክ ይጠብቅህ እሜን ማሽ ነኝ
Anonymous said...
Dn Daniel

Do you know your readers?

thanks
Anonymous said...
ነገሩ ሁሉ በአስተያየ ሰጪዎች በኩል ያየውት ምን የሰማ ቀን ያብዳል የሚል ሆኖብኛል።ይህ የሚያሳየን በጥናት ጉዳይ ላይ ብዙ መስራት እንዳለብን ነው። ይህ ታሪክ ነው ታሪክ በታሪክ ሂደት ላይ አንድ ነገር ሲተረክ በተለያዩ ማሕበረሰቦች ዘንድ ያለው አካሄድ አቀባበል የተለያየ
ሊሆን ይችላል የኛ ቤተ ክርስቲያን መምህራን በታሪክ አቀራረብ ላይ አንድ የሚያደርጋቸው ነገር እንዳለ ሁሉ የተለያዩ ጥቃቅን ለዩነቶችች በአብነት ት/ቤት ውስጥ ሰላለ ነው የላይ ቤት የታች ቤት እየተባለ የሚነገረው ።
ይህን በሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል እንዳንድ ጊዜ እኛ የሰማነው ብቻ ተመላልሶ ቢነገረን እንጂ
ሌላ ስንሰማ ጆሮችንን የሚያሳክከን ቁንጽል ዕውቀት ያለን ብዙ አለን። ክርስትና ለኛ ብቻ
አይደለም ለዓለሙ ሁሉ የማሳወቅ ኃላፊነት አለብን ለዚህ ደግሞ ከአገልጋዩ ጅምሮ ሌላውም
ተገልጋይ በቂ የሆነ እውቀት ሊኖረው ያስፈልጋል። ለመመጻደቅ ሳይሆን ራሳችን ድነን ሌላውን
ለማዳን።
በተረፈ ዳኒ እንደዚህ አይነት አቀራረብህ በራሴ ወድጀዋለሁ ። ይበል የሚያሰኝ ነው። አንዳንድ አስተያየቶች ይህን የመሰለ አለማቀፋዊ ጥናታዊ ጽሁፍ በእንጭጩ ለማስቀረ የማሸማቀቅ አስተያየታቸው ወደኃላ እንዳያደርግህ በተረፈ ሐይማኖታዊ የሆነ ዶግማ ቀኖናና ታሪክ ያላቸውን ለዩነት ብዙ አስተያየት ሰጪዎች በሚገባ ልታውቁ ያስፈልጋል።
መልካም የመስቀል በዓል ለዳኒ ለዚህ ተሳታፊዎች።
Anonymous said...
God bless you Dani for your hard work.

Even if you didn't finalize your writing, I just want to say a couple of things.

1- When we do research, we need to TEST the genuinity of our external evidence. I mean it shouldn't oppose our ቤተክርስቲያን አስተምሮ.

2- I think when we do research, the evidence we collect& the conclusion we make, It should support our ቤተክርስቲያን አስተምሮ because out there so many the "so called evidence" we shouldn't (don't) relay on.

3- I think it is well known when some historians write history they don't put the real facts. When we refer Arabs' or Western evidence, we find a lot of biased information so we have to carfull when we pass it others.

At last I want to mention one example here, one day ago the Iranian president said the 9/ 11 attacks on the United States may have been planned by Americans themselves. What I mean here is after some years some people may use it as evidence to support whatever their claim.
Anonymous said...
Thank you, Dane! this is my quation Bcz everybody have to many different history about this topic But it is not enough for me i need more explanation & more history.
Dane,I know you read to many historical books b4 posting this issue,so we need more............
AB from DC
Anonymous said...
መስቀሉ ላይ ከተሰቀልው ክጌታችን ላይ አይናችንን አንስተን በመስቀሉ ላይ ማድረጋችን ምን ይባላል?!
Anonymous said...
ዲ/ን ዳኒ ቃለ ህይወት ያሰማህ ! አሁን በቤተክርስቲያናችን የሚሰጠው ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ትምህርት እንከን እንደሌለበት እሙን ቢሆንም፤ታሪካችንን እና የይማኖታችንን ዳራ ማወቅ በዚህ ወቅት ይበልጥም ለዚህ ትውልድ ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ለአጭበርባሪዎች እና ስተው ለሚያስቱ በር ከመዝጋቱም በላይ ትውልዱ ወጥ የሆነ መረጃ በመያዝ የነበረውን አጥብቆ እንዲቀጥል ይረዳዋልና፡፡ ከላይ በአስተያየታችን ለመረዳት እንደሚቻለው እኛ አንባቢያን ብዙን ግራ እንደገባን የሚያመለክት ስለሆነ፤ ግራ ገብቶን እንዳንቀር የጀመርከዉን ሳታብራራ እና መቋጫ ሳትሰጥ እንዳትተወው አደራዬ የጠበቀ ነው ፡፡ ያለበለዚያም ጥናቱ ቀጣይነት ሊስፈልገው ከቻል ለአንባቢዎችህ አንዳች ማሳሰቢያ ምስጠት እንደሚጠበቅብህ ይሰማኛል፡፡ዲ/ን ዳኒ ለማንኛውም አንተ በርታ፤ ፈጣሪያችን ትጋቱን እና ፀጋውን ያድልህ !
አምላክችን ሀገራችንን እና ይማኖታችንን ይጠብቅልን!
ደ.ታ ዘባህርዳር
Z'Yisma nigus said...
"KE'EYESUS KIRSTOS MESKEL LELA TIMHIRT KENE YIRAK"

Kale hiwot yasemalen!!

As people said it needs more clarification.Eventhough our church has enough to say about demera,u are also expected to say sth about it.And be sure we will be Christians who can record what he/she has,it doesn't have contradiction with church teaching but what it shows is we have a problem of developing our knowledge by examining books(written by church fathers).

Any lets expect what ABA MESTET?
May God bless u and keep our mother church forever!!
haile leul said...
thank u dani. i love history unlike some say it wont be bread. i hope u will post us part two very soon
Anonymous said...
really controversial!
Anonymous said...
Dear Dn Daniel,

It is very good start but there remains a lot to dig out.

I did not see why you are sticking your self only on the books out of EOTC but I am saying that t=you do not have to use them, don't you think that the Brana books written by our innocent fathers have more information than any other books especially in religious context.

I wounder if you search some information about the holy cross at DebreKerbe before writing this article. Please try to refer books that found too.

It has been commend trend to read and believe on the perspective of other books than..

Your artcile is not full at least we need to the usual teaching of our church.

Make your article full!

H, NY
Dawit said...
"ነገሩ ሁሉ በአስተያየ ሰጪዎች በኩል ያየውት ምን የሰማ ቀን ያብዳል የሚል ሆኖብኛል።" ይህ ዐረፍተ ነገር በዚህ ጥናታዊ ጽሁፍ ላይ ጥያቄ ባላቸው ወይንም የማይስማሙባቸውን ነጥቦች ለይተው ባስቀምጡ ተሳታፊዎች ላይ የተሰነዘረ ጅምላ ጨራሽ ጽርፈት ነው። የልዩነት ሃሳብ፣ ጥያቄዎችና አሉታዊ እንኳን ቢሆኑ አስተያየቶች፣ አንድን ጥናት የበለጠ ለማሻሻል፤ ያልታዩ ነጥቦችን ለመለየትና ተጨማሪ ስራ ለመስራት ያግዛሉ እንጂ ተስፋ አያስቆርጡም። ይልቁንም ከላይ የጠቀስኩትንና ሌሎች ያን የሚመስሉ አስተያየቶች ረብዕ ምን እንደሆነ አይገባኝም። በአንድ ወቅት አዲስ ነገር ጋዜጣ የአንድ ዘፋኝ ስራችን በተመለከተ አንድ ዘገባ ሰራ። በዘገባው ያልተስማሙ የዘፋኙ ደጋፊዎች ጋዜጠኞቹን በአገኙት አጋጣሚ ሁሉ በስድብና ዛቻ አጣደፏቸው። ይህን ግዜ ምን አሉ:-"ዘፋኙ እንዲህ ያሉ ደጋፊዎች ስላሉት የሚኮራ አይመስለንም።" እኔም ዳንኤል የሚጽፈውን ሁሉ ያለ አንዳች ተቃውሞና የልዩነት ሃሳብ የማይቀበሉ ደናቁርት ናቸው የሚሉ ደጋፊዎች ስላሉት የሚኮራ አይመስለኝም።
Anonymous said...
I read here a comment saying "መስቀሉ ላይ ከተሰቀልው ክጌታችን ላይ አይናችንን አንስተን በመስቀሉ ላይ ማድረጋችን ምን ይባላል?! Who did that?? Who said we don't have to discuss other issues other than Our Lord Jesus Christ ho is God?

The Holy Bible says ለሚጠይቁቹ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃሁ ሁኑ.

With Love
Anonymous said...
My question is can we see the Gemade meskel in Gishen debre kerbe or not? because at the last statment on this article it says atse tewedros tried to dig it out because his wife was dead, but couldn't dig it out or something? Ezi lay teyake bimelesilin. Other than that Melkam ye meskel beal yadirgilin.
Anonymous said...
Dn Daniel,

We Ethiopian accept others book without justification we always claim justification for our books while our books are very old and written during olden times where people were less likely to be biased. I am confident that our fathers in olden time were very loyal for truth and God. I want to ask your thought what if you happen to read that the Holy Cross was burnt to ash at some time,..

I think you need to give attention for books that you get them.
DEREJE THE AWASSA said...
Dear Dn. Daneil
God bless you
I do have a couple of comments on this article.
1. in my understanding this article is not controversial to what we have known before. I think readers should focus on the skeleton of this story than words you used and literatures you sited. For instant you wrte this ‘አይሁድ በሮማውያን ላይ እስከ ዐመጹበት እና ኢየሩሳሌም ከክርስትና በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ እስከ ጠፋችበት እስከ 70 ዓም ድረስ መስቀሉ በክርስቲያኖች እጅ እንደ ነበር ይታመናል፡፡ በኋላ ግን ክርስቲያኖቹ የሮማውያንን እና የአይሁድን ጦርነት በመሸሽ ከኢየሩሳሌም ወጥተው ወደ ሌሎች ሀገሮች ሲሰደዱ፤ በኋላም በባር ኮባ ዐመፅ ጊዜ /132-135 ዓም/ ኢየሩሳሌም ፈጽማ በሮማውያን ስትደመሰስ የመስቀሉ እና የሌሎችም ክርስቲያናዊ ንዋያት እና ቅርሶች ነገር በዚያው ተረስቶ ቀረ፡፡’ that is the point. The Holly Cross Was buried Somewhere. This fact is analogues to what we know in our church literature and sayings.
On the second sub topi you write ‘ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች መስቀሉን እንደገና ያገኘችው ንግሥት ዕሌኒ መሆንዋን ይናገራሉ፡፡ በ380 ዓም አካባቢ የተወለደው ታሪክ ጸሐፊው ሶቅራጥስ Ecclesiastical History በተሰኘው መጽሐፉ ላይ በምእራፍ 17 መስቀሉ እንዴት እንደ ተገኘ ዝርዝር መረጃ ይሰጠናል፡፡ ንግሥት ዕሌኒ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዛ በጎልጎታ የጌታ መቃብር ላይ የተሠራውን የቬነስ ቤተ መቅደስ አፈረሰችው፤ ቦታውንም በሚገባ አስጠረገችው፡፡ በዚያን ጊዜም የጌታችን እና የሁለቱ ሽፍቶች መስቀሎች ተገኙ፡፡’ this is exactly similar story to the sayings and facts we have in church. The only missed message may be how this crosses are found. The answer is with us with smoking.
But many readers may be confused on the next sentence i.e ከመስቀ ሎቹም ጋር ጲላጦስ የጻፈው የራስጌው መግለጫ አብሮ ተገኘ፡፡ please readers it says ከመስቀ ሎቹም and it is plural it didn’t sayከመስቀሉ;; that is why singes and miracles are needed for identification of the true Cross. Thus one of the miracles were ሶቅራጥስ ከሦስቱ መስቀሎች አንዱ የክርስቶስ መሆኑን እንዴት ሊታወቅ እንደቻለ ሲገልጥ እንዲህ ይላል «አቡነ መቃርዮስ በማይድን በሽታ ተይዛ ልትሞት የደረሰችን አንዲት የተከበረች ሴት አመጡ፡፡ ሁለቱን መስቀሎችንም አስነኳት፤ ነገር ግን ልትድን አልቻለችም፤ በመጨረሻ ሦስተኛውን መስቀል ስትነካ ድና እና በርትታ ተነሣች፡፡ በዚህም የጌታ መስቀል የትኛው እንደሆነ ታወቀ» ይላል፡፡ this history is analogous to the fact we have in our church sayings.
Some of the comments focused on the man called የኪሪያኮስ. I think it is also mentioned on ምንም እንኳን ሶዞሜን ባይቀበለውም መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ያመለከተው ከከተማዋ በስተ ምሥራቅ ይኖር የነበረ አንድ አይሁዳዊ መሆኑን እና እርሱም ይህንን መረጃ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲተላለፍ ከነበረ መዝገብ ማግኘቱን እንደ ሰማ ጽፏል፡፡ ንግሥት ዕሌኒ ባደረገችው አስቸጋሪ ቁፋሮ መጀመርያ ጌታ የተቀበረበት ዋሻ፤ ቀጥሎም ከእርሱ እልፍ ብሎ ሦስቱ መስቀሎች መገኘታቸውን ሶዞሜን ይተርካል፡፡ ከመስቀሎቹም ጋር የጲላጦስ ጽሑፍ አብሮ መገኘቱን እና የጌታ መስቀል ከሌሎች የተለየበትን ሁኔታ ከሶቅራጥስ ጋር ተመሳሳይ በሆነ ሁኔታ ይተርከዋል፡፡ what do you think?
Please readers download this article and read again and again to compare with the story from the church. I couldn’t find any controversial idea.
2/ I do have strong comment on በዐፄ ዳዊት ዘመን መጥቶ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካኝነት በግሼን አምባ የተቀመጠው ግማደ መስቀል በይፋ የታወቀውና በነገሥታቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የመጣው ዋናው እንጂ የመጀመርያው ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡ this idea should have been supported with tangible evidences. But the evidences like ክርስትና ብሔራዊ ሃይማኖት ከሆነ በኋላ ነገሥታቱ በሳንቲሞቻቸው ላይ የመስቀል ምልክት ማድረጋቸው፣ እንደ ንጉሥ አርማሕ ያሉትም በበትረ መንግሥታቸው ላይ መስቀል ማድረጋቸው፤ ከቀደምት ክርስቲያን ነገሥታት አንዱ የሆነው ንጉሥ ዐፄ ገብረ መስቀል ተብሎ መሰየሙን ስናይ……… but this may not only by having fragment of the true cross. The can use the sign of cross and names like ገብረ መስቀል just by listing the story of Crucifying of Jesus Chris on the cross. I hope you will clarify such kind of ideas on the next part.
God Bless Tewahido
Anonymous said...
Selam Dn. Daniel,
Thank you Daniel for writing this article.

I see that you did a very good research. BTW, I agree with your suggestions too (I mean regarding your anticipation that some other part may have arrived even earlier).

I also did not see any kind of conflicts with our church's teaching. But I do understand that you need an objective reader, not worshiper or fault finder or yemiberegig. May God give to us (your readers) a purposefulness and to you strength and understanding.

Tekle
Anonymous said...
Hi Dn. Daniel,
This article seems a bit confusing and creating unanswered questions. Can you please first finish about Meskel and our church’s stand before you write anything else.
Anonymous said...
Hi Dn.
kalehiwote yasmalen
gera yitegaban anbabyian tsehufu eskemiyalke betegest entebeke yimketelew tewelde yihen yiabatochachene astemerote kealmeakfawi merea gare asenasle netsehu temerte endalen kalasawokenew mengawe yibetenale selezhi yitsehufuene mechersha betegest entebke.
egzihaber ethiopia yibark betekerstinen yitebke anteneme yikdusan ameleka yitbekehe.
Alex.ke A.A
Anonymous said...
waw! a lot of comments... from the title, I expected you would tell us the holy cross is inside our heart, but I got another story.
What I can say now is you made us to participate and being awake to discuss each other.I am sure you will finish it as soon as possible.

Blessings!
Anonymous said...
‘’በዐፄ ዳዊት ዘመን መጥቶ በዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ አማካኝነት በግሼን አምባ የተቀመጠው ግማደ መስቀል በይፋ የታወቀውና በነገሥታቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የመጣው ዋናው እንጂ የመጀመርያው ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡’’ ዳኒ ይህ አባባልህ ከላይ አንድ አንባቢ እንዳለው ሁሉ እኔም አልገባኝም በደንብ ብታብራራልን፤ ማብራሪያውን እጠብቃለሁ
ዲንፕል
Anonymous said...
ድንግል ትጠብቅህ በርታ የተዋህዶ ልጅ!!!!!!
ቬሮኒካ.ts. said...
“መስቀሉ ላይ ከተሰቀልው ክጌታችን ላይ አይናችንን አንስተን በመስቀሉ ላይ ማድረጋችን ምን ይባላል?!”
የሚባለውማ
“የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉት ሞኝነት ለእኛ ለምናምን የእግዚአብሔር ኃይል ነው 1ኛ ቆሮ 1፡18”
ምክንያቱም
አላፍርበትም ያመንኩትን አውቀዋለሁ 2ኛ ጢሞ 1፡12

No comments:

Post a Comment