የጦር ሠራዊት መለዮ ደንብ |
ኒሻኖችና ሜዳዮች
የክብረ በዓልና የማታ ልብስ በተለበሰ ጊዜ በተለይ ሲታዘዝ ኒሻንና ሜዳይ በግራ ደረት ላይ ይደረጋል፡፡ ሜዳዮች እንደ ተመደቡት የጦርነት ቀን ተራ ይደረጋሉ፡፡ ሜዳዮች ቁጥራቸው የበዛ እንደሆነ ሊደራረቡ ስለማይገባ በሁለት ወይም በብዙ መስመር እንዲደረደሩ ማድረግ ይቻላል፡፡
ጥቃቅን ኒሻኖችና ሜዳዮች
በመንግስት ወይም በሕዝብ ልዩ በዓል ጊዜ በጥሪው ወረቀት ላይ የተመለከተ እንደሆነ የማታ ልብስ ሲለበስ በጥቃቃን የተሰሩ ኒሻኖችና ሜዳዮች ይደረጋሉ፡፡
የኒሻንና የሜዳይ ማሰልጠኛ ጥብጣብ
የያንዳንዱ ኒሻን ወይም ሜዳይ የጥብጣቡ ወርድና ቁመት ሊያዘው ለኒሻኑ ወይም ለሜዳዩ በተወሰው መጠን ይደረጋል፡፡ ለሜዳዮች ማድረጊያ በግራ ደረት በኮት ላይ ወርዱ 3 .ሳሜ ርዝመቱ በሚያስፈልግ መጠን የሆነ ጥብጣብ ይሰፋል ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ቀጭንና ጠፍጣፋ የብረት ዘንግ ላይ ጥብጣቡ ሳይራራቅ ይደረጋል፡፡
ኒሻኖች የሚደረጉበት ጊዜ
በትልቅ ሰልፍ ጊዜና በማታ ልብስ ላይ በመንግስት በሕዝብ በኦፊሲዬል በዓል ጊዜ ኒሻኖች ይደረጋሉ፡፡ የውጭ አገር መንግስት ኒሻኖች በሸላሚው መንግስት ደንብ በተወሰነው መሠረት በቀኝ ወይም በግራ ደረት ይደረገሉ፡፡ የኢትዮጵያ የጦር መኮንኖች በውጭ አገር ሳሉ የዚያ አገር መኮንኖች ኒሻኖቻቸውን ባደረጉ ጊዜ እነርሱም ኒሻኖቻቸውን ያደርጋሉ፡፡
ጥብጣብና ኒሻን
በመንግስት በዓልና በትልቅ ሰልፍ ጊዜ ወይም የማታ ልብስ ለብሶ በትከሻ የሚነገት ኮርዶን ኒሻን የሚደረግ ሲሆን በቀኝ ትከሻ ላይ ይውልና ከቀበቶ ሥር ሆኖ ይነገታል፡፡ ኮማንደር ኒሻን ያላቸው በትልቅ ሰልፍ ጊዜ ወይም ከማታ ልብስ ጋር ኒሻናቸውን እንዲያደርጉ በተለይ በታወቃቸው ጊዜ የኒሻኑን ጥብጣብ ከኮት ብሳት ስር እንደሚውል አድርገው በአንገት ላይ ያጠልቁታል፡፡ ኒሻኑም እንደሚታይ ይደረጋል፡፡
የመንግስት ኦፊሴዬል ወይም የሕዝብ በዓላት
ሀ/ ግርማዊ ንጉሠ ነገስት ወይም የግርማዊ ንጉሥ ልዩ እንደራሴ ባሉበት የሚከበር በዓል ወይም በተለይ ታዞ ከንጉሠ ነገሥቱ ልጆች አንደኛው ባለበት ሰልፍ ሲደረግና ክበረ በዓል ሊከበር የቤተ መንግስት በዓል ይባላል፡፡
ለ/ በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የመንግስት በሆነ ማኅበር ጥሪ (ግብዠ) ሲደረግ እንደ ኦፊሴዬል በዓል ይቆጠራል፡፡
ሐ/ በማንኛውም ዓይነት ማኅበር ጥሪ (ግብዣ) ሲደረግ እንደ ሕዘብ በዓል ይቆጠራል፡፡
የኒሻንና የሜዳይ አደራረግ ተራ
የኒሻንና የሜዳይ አደራረግ ተራ እንዲሁም ኒሻንና ሜዳይ በሚደረግበት ጊዜ የጥብጣቡ አደራረግ ለኒሻንና ለሜዳይ እንደተወሰነው ሆኖ ያደራረጉ ተራ ቀጥሎ ተመልክቷል፡፡
ሀ/ የኢትዮጵያ ኒሻኖችና ሜዳዮች
የሰሎሞን ኒሻን፤ የንግሥተ ሳባ ኒሻን፤የሥላሴ ኒሻን፤የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን፤የኢትዮጵያ ኮከብ ኒሻን፤የቅዱስ ጊዮርጊስ ጦር ሜዳይ፤የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የጦር ሜዳይ፤የዳግማዊ ምኒልክ የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ፤የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የብሄራዊ አገልግሎት ሜዳይ፤የአርበኝነት ሜደይ፤የውስጥ አርበኝነት ሜዳይ፤የስደተኝነት ሜዳይ
ለ/ የውጭ አገር ኒሻኖች በየተሰጠበት ቀን ተራ
ሐ/ የውጭ አገር ሜዳዮች በየተሰጠበት ቀን ተራ፡፡
የውጭ አገር ኒሻኖችና ሜዳዮች
ሙሉ ፈቃዳ ለተሰጣቸው ለውጭ አገር ሽልማቶች የኢትዮጵያ ኒሻኖች ደንብ ይጸናባቸዋል፡፡
ኒሻኖቹ ወይም ሜዳዮቹ በደረት ላይ በተደረጉ ጊዜ የነዚህ ሽልማቶች ጥብጣቦች በደረት ላይ አይደረጉም፡፡
የውጭ አገር ሜዳዮች ከጦር ሜዳዮች በቀር ለውጭ አገር ኒሻኖች የተወሰነው ደንብ ይጸናባቸዋል፡፡ የውጭ አገር የጦር ሜዳይ በሁሉም አይነት መለዮ ላይ እንደ ኢትዮጵያ ሜዳይ በግርማዊ ንጉሠ ነገስት ፈቃድ ይደረጋል፡፡
ኮርዶን ኒሻን
በትከሻ የሚነገት ኮርዶን ኒሻን በትልቅ ሰልፍ ጊዜ ይደረጋል፡፡ ከአንድ ዓይነት ይበልጥ ኮርዶን ኒሻን ያላቸው ሰዎች የከፍተኛውን ተራ ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም የሌሎቹን ተራዎች ፕላኮች እንደማዕረጉ ተራ አንድ ወይም ይበልጥ ሊያደርጉ ይቻላል፡፡ወደ ጡረታ በተዛወሩ መኮንኖች ላይ ይህ ደንብ ይጸናል፡፡
|
No comments:
Post a Comment