ሰቆጣ
ሰቆጣ | |
![]() | |
ሰቆጣ ከተማ | |
ከፍታ | 2266 ሜትር |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክፍላገር | ሰሜን ወሎ (ላሳታ) |
የሕዝብ ቁጥር | 13፣700 |
ሰቆጣ ፣ ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከሰቆጣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤ.ክ. ይገኛል። በዚሁ ቤተ ክርስቲያንላስታን ከሰቆጣ ሆነው ያስተዳደሩ ዋግሹሞች ደረቅ ቅሪቶች ይገኛሉ።
ማውጫ[ይደበቅ] |
[ለማስተካከል]ታሪክ
ከአክሱም መዳከም በኋላ በአረብ ጸሐፊዎች ዘንድ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰውኩባር የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ገናና ማዕከል ሰቆጣ እንደነበር በታሪክ ግንዛቤ አለ[1]። ስለሆነም ይመስላል፣ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች መቀመጫቸው ሰቆጣ ነበር።
ከጥፋት በተረፉ መዝገቦች ዘንድ ሰቆጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው በ1738ዓ.ም. ሲሆን፣ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ወደ ላስታ ባደረጉት ዘመቻ ሰቆጣ ውስጥ በዋግ ሹም ነዓኩቶ ለአብ(የዋግ ሹም ቴዎድሮስ አባት) ቤት ለ5ቀን እንዳረፉ ዜና መዋዕላቸው በማተቱ ነው [2][3]።
ከዚያም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ የአውሮጳ ተጓዦች ሰቆጣን ሲጎበኙ፣ ዋልተር ፕላውዴን ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 5 ብቻ ነጋድራሶች አንዱ በሰቆጣ ይገኝ እንደነበር መዝግቧል። ከዚያም በ1800ዎቹ መጨረሻ ሰቆጣን የጎበኘው ኤ.ቢ.ዋይልድ ሰቆጣን የላስታ ዋና ከተማ አድርጎ ሲጠቅስ፣ የሰቆጣ ቤተ መንግስት ባለ ሶስት ፎቅና በ1650ዎቹ የተገነባ እንደነበር ያትታል። ቤተ መንግስቱን የሰሩት የፋሲል ግቢን አናጺዎ እደሆኑም መላምት ያቀርባል[4]። ይሄው የአውሮጳ ተጓዝ፣ በ1880ዎቹ የሰቆጣ ገበያ ከአካባቢው ካሉት ሁሉ ግዙፉ እንደነበር ፣ የዝሆን ጥርስ እና በቅሎ ገበያው የደራ እንደነበር፣ እንዲሁም 21፣000 በሬዎች፣ 2፣900 ላሞች፣ 10ሺህ ፍየሎች፣ 1፣500 በጎች በየአመቱ ለግብይት ይቀርቡበት እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም[5] ።
ጥር2፣ 1929 ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ እንደጣሉ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል[6]። ከሶስት ወር በኋላ ሰቆጣን ሲቆጣጠሩ፣ ለከተማው መንገድ በመስራት እና የአካባቢውን መስጊድ በማደስ ይታወቃሉ። በዚህ ወቅት የህቡ ቁጥር 4500 ነበር [7]።
በ1972ዓ.ም. ሰቆጣ ለተወሰነ ጊዜ በህ.ወ.ሐ.ት ቁጥጥር ስር የነበር ሲሆን ከዚያም በኋላ የቀድሞኢ.ሕ.አ.ፓ አባል ቡድኖች ያቋቋሙት ኢ.ህ.ዴ.ን ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሉን ማዕክል በሰቆጣ አድርጎ ነበር[8]። በዚህ መሃል የተነሳውና ለብዙ ሰዎች መጎሳቆልና ሞት ምክንያት የሆነውየ77ቱ ድርቅ ሰቆጣን ያማከለ ነበር። በወቅቱ ከተማዋ ምግብ የምታገኘው ከኮረም እንደነበርና ይህ የፈጠረውን ችግር የተባበሩት መንግስታት የዕርዳታ ሃላፊ በኢትዮጵያ፣ ከርት ጆንሰንዘግቦት ይገኛል [9]።
[ለማስተካከል]ሰቆጣ፣ ከተማው
ሰቆጣ፣ ከሌሎች ከተሞች ለየት ባለ መልኩ ክብና ሁለት ፎቅ ባላቸው ቤቶች የተመላ ነው። እንዲሁም አብዛኛዎቹ ቤቶች ሁለት ግድግዳ ሲኖራቸው በኒህ ሁለት ግድግዳዎች መካከል ወደ ፎቁ የሚያወጡ ደረጃዎች ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት ወደሰቆጣ የሚሄዱ ሁለት መንገዶች ይገኛሉ። አንዱ ከኮረም ሲሆን ሁለተኛው ከወልደያ ተነስቶ በላሊብላ አድርጎ ሰቆጣ የሚደርስ ነው።
[ለማስተካከል]የህዝብ ብዛት
እንደ 1997 ህዝብ ቆጠራ፣ ሰቆጣ ውስጥ 13፣700 ሰዎች ይኖራሉ [10]።
[ለማስተካከል]ማጣቀሻ
- ^ Philip Briggs, Ethiopia: the Bradt Travel Guide, third edition (London: Bradt, 2002), p. 302. The problem of Ku'bar is discussed by Taddesse Tamrat, Church and State in Ethiopia (Oxford: Clarendon Press, 1972), p. 37.
- ^ የዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ዜና መዋዕል፣ ገጽ
- ^ [7th Int. Conf. of Ethiopian Studies 1984 p 224-225]
- ^ [7th Int. Conf. of Ethiopian Studies 1984 p 219]
- ^ Augustus B. Wylde, Modern Abyssinia (London: Methuen, 1901), p. 494
- ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/s/ORTSEK05.pdf
- ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/s/ORTSEK05.pdf
- ^ [12th Int. Conf. of Ethiopian Studies 1994]
- ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/s/ORTSEK05.pdf
- ^ CSA 2005 National Statistics, Table B.3
No comments:
Post a Comment