ስልጣኔዋን ከናይል ወንዝ የቀዳችው – ግብጽ
የጥንታዊ ስልጣኔ ባለቤት የሆነችው ግብጽ አፍሪካን፣ መካከለኛው ምሥራቅን እንዲሁም ምዕራባውያንን በባሕል፣ በፖለቲካና በኢኮኖሚ ትስስር እንዲኖራቸው በማስቻል ረገድ ግንባር ቀደም ናት። እ.ኤ.አ በ1869 ያስገነባችው የስዊዝ ቦይና የነበራት ጥንታዊ ስልጣኔ ትስ ስሩን በመፍጠር ረገድ የላቀ ሚና መጫወ ታቸው ይታመናል።
እኛ ኢትዮጵያውያን ግብጽ ብለን የምንጠራት አገር የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪ አገሮች በራሳቸው ቋንቋ ይጠሯታል። የእንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ አገሮች 'ኢጅብት' ሲሏት አረብኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ደግሞ 'ምስር' እያሉ ይጠሯታል።
የሰሜን አፍሪካዋ ግብጽ አህጉር ተሻጋሪ አገር ናት። አብዛኛው አካሏ በአፍሪካ አህጉር ቢገኝም የሲናይ ልሳነ ምድር ደግሞ ከደቡብ ምዕራብ እስያ ጋር ያስተሳስራታል። በአፍሪካ ኃያል ከሆኑ አገሮች መካከልም ግንባር ቀደም መሆን የቻለችው ግብጽ የስልጣኔዋ ምንጭ ተደርጐ የሚወሰደው የናይል ወንዝ ነው። የግብጽ ኃያልነት በአፍሪካ ብቻ ሳይሆን አህጉር ተሻጋሪ አገር እንደመሆኗ መጠን በሜደተ ራኒያን ሸለቆ በመካከለኛው ምሥራቅና በሙስሊሙ ዓለም የበላይነት አላት።
የ1ሚሊዮን 10ሺ ስኩዌር ኪሎ ሜትር የመሬት ይዞታ ያላት ግብጽ በሰሜን ከሜዲ ትራኒያን ባሕር፣ በሰሜን ምሥራቅ ከጋዛ ሰርጥና ከእሥራኤል፣ በምሥራቅ ከቀይ ባሕር፣ በደቡብ ከሱዳን እንዲሁም በምዕራብ ከሊቢያ ጋር ትዋሰናለች።
ግብጽ በአፍሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ በሕዝብ ብዛቷ ትታወቃለች። ከ80 ሚሊዮን በላይ ይሆናል ተብሎ የሚገመተው ሕዝቧ በአብዛኛው የሚኖረው የናይል ወንዝን ተከትሎ በወንዙ ዳርና ዳር ነው። የወንዙን ዳርቻ ተከትሎ የሚኖረው ሕዝብ 40ሺ ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለውን ቦታ ይዟል። ይህ ስፍራ በግብጽ ውስጥ ለእርሻ ሥራ የሚውለው ብቸኛ ስፍራ ነው።
የሰሐራ በረሃ የሚደርስበት አብዛኛው የግብጽ ምድር ላይ የሚኖረው ሕዝብ ቁጥር አነስተኛ ነው። 50 በመቶ የሚሆነው የግብጽ ሕዝብ ኑሮውን የመሠረተው በከተማ ውስጥ ሲሆን፤ ካይሮ፣ አሌክሳንድሪያና ሌሎች የናይል ዳርቻ ከተማዎች ይህንን ገሚስ የግብጽ ሕዝብ አቅፈው ይዘዋል።
በጥንታዊ ስልጣኔዋ የምትወሳው ግብጽ በጋዛ በሚገኙ የፒራሚድ ስብስቦቿ፣ በታላቁ ሲፊኒክስ (ፊቱ የሰው ሌላው አካሉ የአንበሳ የሆነ ሐውልት) ከፍተኛ እውቅና ከማግኘቷም በላይ በቱሪዝም የላቀ ገቢ እንድታገኝ አስችለዋታል። የጥንታዊ ከተማ ፍርስራሽ የሆኑት ሜምፊስ ቴብስና ካርናኮ እንዲሁም ከሉክሰር ውጪ የሚገኘው የነገሥታት ሸለቆ በመባል የሚታወቀው ስፍራ ለአርኪዎሎጂካዊ ምርምር በዓለም አቀፍ ደረጃ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ።
የግብጽ ጥንታዊ ስልጣኔ ቱሪስቶችን የመሣብ አቅሙ ከፍተኛ በመሆኑ የተነሣ ከዘርፉ የአገሪቱ ተጠቃሚነት የጐላ ነው። ከአገሪቱ አጠቃላይ የሠራተኛ ኃይል 12 በመቶ የሚሆነውም የተሠማራው በቱሪዝም ዘርፍ ነው።
በመካከለኛው ምሥራቅ የተለያዩ የሥራ ዘርፎች ካላቸው አገሮች ውስጥ ግብጽ ቀዳሚዋ ነች። በቱሪዝም፣ በእርሻ፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች በምታገኘው ገቢ ኢኮ ኖሚዋን በጠንካራ መሰረት ላይ ጥሏል።
በግብጽ የአንድነት መንግሥታዊ አስተዳደር የተመሠረተው ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ3ሺ150 ዓመተ ዓለም በፊት እንደሆነ ይታመናል። የመጀመሪያው ንጉሥም ሜነስ በመባል ይታወቃል። በሜነስ የተመሠረተው ስርወ መንግሥት ለሦስት ሺ ዓመታት ያህል የዘለቀ ተከታታይ ስርወ መንግሥት እንደነበረው የታሪክ ድርሳናት ይገልጻሉ።
በግብጽ መካከለኛ ዘመን የተጀመረው በሙሐማድ ዓሊ ስርወ መንግሥት እንደሆነ ይገለጻል። የፈረንሳዩ ናፖሊዮን ቦናፓርት እ. ኤ. አ በ1798 ግብጽን በይፋ ወረረ። ከዚያ በኋላ ለ3 ዓመታት ያህል በአገሪቱ መቆየት ቢችልም በኦቶማን፣ በማምሉክና በብሪታኒያ ኃይሎች ግፊት ተገዶ ከግብጽ ወጥቷል። ቀጥሎም በአራት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ኦቶማኖች ማምሉክችና አልባኒያዎች አገሪቱን የመምራት ስልጣኑን በበላይነት ለመያዝ ትግል ማድረግ መጀመራቸው አገሪቱን ወደሁከት መርቷት ነበር።
በሦስቱ ኃይሎች ፍትጊያ መካከል ኦቶማኖች የበላይነቱን መውሰድ መቻላቸው መሐመድ ዓሊን የግብጽ መሪ ፓሻ አድርግው ሾሙ። በአገሪቱም የመሐመድ ዓሊ ስርወ መንግሥት መሠረት ተጣለ።
መሐመድ ዓሊ የመሪነቱን ስልጣን ካገኘ በኋላ ወታደራዊ አቅሙን በማጠናከር ሰሜን ሱዳን፣ ሶሪያ፣ ከፊል አረቢያንና አናቶሊያን ያስተሳሰረ አስተዳደር ለመፍጠር ችሏል። የመሐመድ ዓሊ ቤተሰብ የመሪነቱን ስልጣን እ.ኤ.አ በ1805 ከያዘበት ጊዜ አንስቶ ስርወ መንግሥቱ እስከወደቀበት ጊዜ ድረስ የመሐ መድ ልጅ፣ የልጅ ልጆች ስልጣንን ሲወራረሱ ቆይተዋል።
የመሐመድ ዓሊ የልጅ ልጅ የሆነው ኢስማኤል እ. ኤ.አ በ1863 ስልጣን ከያዘ በኋላ በስድስት ዓመት ጊዜ ውስጥ የስዊስ ቦይን አስገንብቶ የአባቱ ስርወ መንግሥት ዘወትር የሚዘከርበትን ሥራ ሠርቷል። ይህም ቢሆን ግን የአባቱን ስርወ መንግሥት ማስቀጠል አልቻለም። የአባቱ ስርወ መንግሥት አበቃ። ከዚያም ዘመናዊ የግብጽ አስተዳደር ተጀመረ።
አውሮፓውያን ወደ ግብጽ እንዲገቡ የፈቀደው የኢስማኤል አስተዳደር ቀስ በቀስ በአገር ውስጥ ተቃዋሚዎች እንዲፈጠሩ አድርጓል። በዚህም ቀንደኛ የተቃውሞ አስተባባሪ የነበረው አህማዱ ኡራቢን ታሪክ ያነሣዋል። በኢስማኤል ላይ ተቃውሞ መበር ታቱን ተከትሎ የብሪታኒያና የፈረንሳይ ኃይሎች ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ቢያሣዩም የለወጡት ነገር አልነበረም።
የኢስማኤል ልጅ ተወፊቅ የብሪታኒያ ተሿሚ ቢሆንም ብዙ በስልጣን ላይ መቆየት አልቻለም። እ.ኤ.አ በ1914 ግብጽ በብሪታኒያ ሞግዚት አስተዳደር ስር መሆኗ ይፋ ሆነ። እ. ኤ. አ በ1922 የካቲት 22 ደግሞ ነፃ አገር መሆኗ ታወጀ። አዲስ መንግሥትም እንዲ መሠረት ተደረገ።
አዲሱ መንግሥት ከአንድ ዓመት በኋላ የሕገ መንግሥት ረቂቅ አዘጋጀ። አገሪቱም በፓርላማ ሥርዓት የምትተዳደር መሆኗ ተገለጸ። ሰአድ ዛግሉል የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ። በዚህ ጊዜ አገሪቱ ነፃ አገር መሆኗ ቢገለጽም የብሪታኒያ ተጽእኖ ይንፀባረቅ ነበር። እ. ኤ. አ በ1952 መፈንቅለ መንግሥት እስከተካሄደበት ጊዜ ድረስ የብሪታኒያ ጣልቃ ገብነት ከፍተኛ ነበር። መፈንቅለ መንግሥት በተካሄደ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የብሪታኒያ ወታደሮች ሙሉ በሙሉ የግብጽን ምድር ለቀው ወጥተዋል።
ከፍተኛ የጦር ጄኔራል የነበሩት መሐመድ ናጂብ የመጀመሪያ የግብጽ ሪፐብሊክ ፕሬ ዚዳንት ሆነው የተሾሙት እ. ኤ. አ በ1953 ሲሆን፤ ከአንድ ዓመት በኋላ በ1952 የተካሄደው ንቅናቄ ዋነኛ አስተባባሪ በነበሩት ገማል አብዱል ናስር ስልጣናቸውን በግድ አስረክበዋል። እ. ኤ. አ 1967 በተካሄደው የግብጽና የእሥራኤል የስድስት ቀን ጦርነት የሞቱት ናስር እ. ኤ. አ በ1970 በአንዋር ሳዳት ተተክተዋል።
አንዋር ሳዳት የግብጽና የእስራኤል ሁኔታን ወደ ሰላማዊ ሁኔታ በመቀየር ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል። እ. ኤ. አ በ1977 አንዋር ሳዳት ታሪካዊ የሆነ ጉብኝት በእስራኤል አካሄዱ። ይህም ጉብኝት ከሁለት ዓመት በኋላ ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ጉልህ ድርሻ ነበረው። በጂሚ ካርተር ጥረት ፕሬዚዳንት አንዋር ሳዳት ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜናቼም ቤኒን ጋር በካምፕ ዴቪድ ስምምነት መፈረማቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ሰላምን አንድ ርምጃ ወደፊት አራምዷል። የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኋላ እነዚህ ሦስት ግለሰቦች የሰላም የኖቤል ሽልማት ለመሸለም በቅተዋል።
የሳዳት ስምምነትን መፈረም በአረቡ ዓለም አነጋጋሪ ሆኖ ነበር። እንዲያውም ግብፅ ከአረብ ሊግ እንድትወጣ ተገድዳ ነበር። በግብጽ ላይ ይህን የመሰለ ጫና ቢደርስባትም በአብዛኛው የግብጽ ሕዝብ ዘንድ የሳዳት ርምጃ ድጋፍ አግኝቷል።
ግብጽን ከእሥራኤል ጋር ለማሰማማት የቻሉት ሳዳት እ. ኤ. አ በ1981 በካይሮ ወታደራዊ ትርኢት እየታየ ባለበት ሰአት ወግ አጥባቂ በሆነ ወታደር መገደላቸው በግብጽ ጽኑ ኀዘን አስከትሏል።
ለግብጽ ብዙ የደከሙት ሳዳት እንደተ ገደሉ ስልጣቻውን የተረከቡት በወቅቱ የአገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት ሆስኒ ሙባረክ ናቸው። ሙባረክ ለ30 ዓመታት በስልጣናቸው ላይ ቢቆዩም በዚህ ዓመት ጥር ወር ላይ በተነሳባቸው ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሣ የስልጣን ዘመናቸውን ሳይጨርሱ በኃይል ከስልጣን ተወግደዋል። በአሁኑ ወቅትም አገሪቱ በወታደራዊ አስተዳደር ሥርዓት ስር ስትሆን የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ የሕዝባዊ ተቃውሞ አስተባባሪ የነበሩትና የቀድሞ የትራንስፖርት ሚኒስትር ኢሻም ሻራፍ ይዘውታል።
የግብጽ እውነታዎች
ሙሉ ስም - የግብጽ አረብ ሪፐብሊክ
የቆዳ ስፋት -1 ሚሊዮን 10ሺ ስኩዌር ኪሎ ሜትር
የሕዝብ ብዛት- 80 ሚሊዮን 85 ሺ 862
ዓመታዊ ምርት - 497 ነጥብ 781 ቢሊዮን ዶላር
የነፍስ ወከፍ ገቢ- 6ሺ354 ዶላር
መገበያያ ገንዘብ - የግብጽ ፓውንድ
ዓለም አቀፍ የስልክ ጥሪ- +20

No comments:
Post a Comment