Saturday, September 10, 2011

“ኢቲቪ አቋሙን ይለይልን! “ የህዝብ ነው? ወይስ .. በህዝብ ስም የሚነግድ ፖርቲ


ኢቲቪ አቋሙን ይለይልን! “ የህዝብ ነው? ወይስ ..
በህዝብ ስም የሚነግድ ፖርቲ
BY DR,. ZERHUN BERHANU 
ኢቲቪ በልማታዊ ጋዜጠኝነት ሰበብ፣ በዕውቀት አጠር ጋዜጠኞቹ የፖርቲ አባልነት ሽፋን መረጃዎችን የመድፈቅ የማስተባበል ስራ የሚሰራ ሆኗል፡፡
እንደ መገናኛ ብዙሃን፤ አንገት የሚያስደፋ  የፖርቲ ልሳንነቴን የሚያረጋግጥ ተራ እየሆነብን ተቸግረናል፡፡
ልማታዊ ጋዜጠኝነትን ከታትለሁ  የሚለው ኢቲቪ ፤ አይዞህ ባይ ካላገኘ የማይናገር፣ የሚመራው  ካላኘ የማይሄድ፤ በርታ ካላሉት አሻግሮ የሚያያ ሆኖብናል፡፡ ይህንን ያስባለኝ በቀን 03/12/2003 ዓ.ም BBC ባሰራጨው  አርሶ አደሩ ግብአቶችን በፖርቲ አባልነት አላገኘም የሚል ዜና ተከታትሎ  የተሰራ ዜና ነው፡፡
ሰሞኑን የተቃዋሚ ፖርቲዎች  የሰጡት መግለጫ ራሱን ያሳመመው ኢህአዴግ / ኢቲቪ / በመረጃው ላይ የተጨፈነ  የትንታኔ ቅኝት በአድር ባይ ያልበሰሉ ሪፖርቶች አቀራረብ ሰልችቶናል፡፡
ዘገምተኛ በሚመሰል ጋዜጠኛ የሚተንተኑ ተረት አውጊ፣ የፖርቲ ልሳን ያልተገራ ግብር በምንከፍልበት ቴሌቪዥን ሲመጣ  እራሳችንን ያመናል፡፡
ቢያንስ እንኳ እንደ ጋዜጠኛ መረጃውን ሚዛናዊ ማድረግ ምን ይከብዳል BBC እንኳን የቀረበዉን ሃሳብ ከሁሉም የመንግስት አካላት አካቶ የሰራውን ዜና ቡራ ከርዩ ብሎ በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ልሳንነቱ የአንድን ጥግ ይዞ መነሳት አሳፋሪ ነው፡፡
በእርግጥ መሰረቁ እራሱን አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ቴሌቪዥን ሲል ቢሰይም የሚሻለውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነኝ ብሎ ሚነግድብን ምን አረግን ነው፡፡ የት ለይ እንተንፋስ ? ማንን እንመን ?
ደስ ሲለው እነ አሞራውን የታሪካቸው አካል አድርጉ እያሉ የሚያስገድድ፣ የአንድ ፖርቲ አቋም በውስጣችን  እንድናሰርፅ የሚጫነን  ምርግ ሆነ፡፡
መቼ ነው ከሚነፍስበት ንፋስ ነፃ የሚወጣው? “ነፃ  አስተሳሰብ ለተሻለ ህይወት” አለ ራዲዮ ፋና
በመረጃ ዘመን የተቆለፈ የግብርና ነፃነታችን የበለጠ መታገዝ የሚ¯ምረው፡፡ እኔ ላስብላችሁ … እኔ ልናግራላችሁ … እኔ ልፈፅምላችሁ ከማለት መላቀቅ የሚቻለው እንዴት ነው?
እውነታውን በውሸት ልማት ፣ መሸፈን የሚቀርበት ዘዴ ብንፈልግስ ሠሞኑን ኢህአዴግ ኪራይ ሰብሳቢው መቆረጥ አለበት ብሎ ሲል መድረክ ፈጠረ፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ እንዴት አድርገው  እንደበዘበዙን ተናዘዙ፣ ለውጥ ባይኖረውም፣ እየተፈራራ የተሸፋፈነውን ሳይጨምር ታዲያ ልሳኖች ተናዘዙ፡፡ በዚህ ሰዓት ሚዲያውን ያማረሩ የባህር ዳር  ከተማ ኗሪዎች ተጠቃሺ ናቸው፡፡ በውሸት ሀብታም ናቸው ተባልን፡፡ አመራሩ የሌለንን አላቸሁ፣ ሚሊኒየር ሁናችኋል እያለ ሲያውጅብን ምን እናድርግ፣ ተደራጅተው… ከድህነት ወጥተዋል እያሉ  ያነበንባሉ እኛ ግን አሁንም በድህነት ውስጥ ነን ሲሉ መሰከሩ፡፡
ኧረ ይህንስ አላወቅንም፤ ኧረ ይህንስ አልሰማንም በሚል መሪ ብንታጅብም፡፡
ለማንኛውም  መንግሥትን በሃሳብ  በልፅገዋል አትበሉን ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ውስጣችን አሁንም ድሃ ድሃ የሚሸት ውኃ ነነ ብለዋል፡፡ ከሚኖሩት በላይ ምን መስካሪ አለ፡፡ ካለፈበት በላይ  ማን ተናጋሪ አለ፡፡
ሌላው የኢቲቪ መረጃ የቃለ መጠይቅ አደረጀጀት ሁሌም ባጭሩ ሪፖርተሩ የሚፈልገውን ነግZህ እን­ትነግረው መደረጉ ለየት የሚያደርገው ባህሪ ነው፡፡

አንዱ የሀገራችን  ታሪክ አለ: አፄ ቴዎድሮስ ልጃቸውን አለማየሁን ይዘው  ይንጎራደዳሉ፡፡ ታዲያ ልፁል አለማየሁ የደላው ነው፡፡ ምንም አልቸገረውም እንደ አሁኖቹ የነገስታታ ልጆች  ቤተ መንግሥት ገብቶ ድሎቱ  ባያስጨንቀውም  በአቅሙ የንጉስ ልጅ አደል ሰባት አጫዋች ነበረው፡፡ የአንዷ ጀርባ አልመቸው  ሲል ሌላዋ ጀርባ ላይ እያለ  ይንደላቀቃል፡፡
ታዲያ ከአባቱ ጎን ቁሞ ” አባየ ሺፍታ ነህ ይሉሃል” ይለዋል “ሺፍታ አሉኝ ልጄ አዎ ለነፃነት፣ ለሀገር ዕድገት፣ ጫካ  ዱሩን ሳማትር ማድር የሃገርን ልዕልና፤ የምናፍቅ ሺፍታ ነኝ…” ይመልሳል አባዬ ድሃ ነህ ይሉሃል?”ይጠይቀዋል፡፡ “ይህንም ነገሩህ ልጄ አዎ የኮሶ ሻጭ ልጅ ድሃ ነኝ” ድሀ ስትሆን ልጄ ስትናገር የሚሰማህ፤ እንዳትስብ የሚያስርህ፤ ተናግረህ የሚያዳምጥህ ታጣለህ፤ ድህነት፤ የመንፈስ የቁስ ረሃብ ነው፡፡ እንዴት አድርጌ ላስረዳህ ተወው… ልዑል ድህነት ባፍ አይገባም ስትኖረው ስትኖርበት ብቻ ነው የ ሚገባህ “አዎ ሀብታምነትም በአፍ አይገባም፡፡ ባልኖርንበት  ባለፀግነት፤ ኢቲቪ የሚሰጠን ስያሜ አስከፍቶኛል ነው ጥያቄው፡፡እየኖርንበት ያለውን ድህነት ለማጥፋት ድሃውን ድሃ ማለት ካልተጀመረ በጣም ያስቸግራል፡፡ ምናልባት ልማታዊ ጋዜጠኝነትም የራሱ ነፃነት ቢኖረውም ለአፋኝና ጨቋኞቹ ተነቦ የሚተረጉም የፍላጎት መጠመዘዣ የጋዜጠኝነት የእስያ ፍልስፍና ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ለሃገራችን፣ የድህነት ወለል ጋዜጠኝነት /Poverty Land reporting/ ቢኖረን ሚሻል ይመስለኛል፡፡ ህይወት ህይወት በሚሸት ዘገባ ድህነትን እያሳየን እንድንሸሸው  ብናስተምር በነፃነቱ ቀይጠን የታፈነበትን የፖለቲካ ድህነት ብንዘግብ አማራጭ አይሆንም ትላላችሁ፡፡
ወደ ቀድሞ ነገሬ ልመለስ፥
አሁንም ቢቢሲ ስላለ ብቻ ሣይሆን ተርበናል፤ ተጠምተናል፣ ማየት ተስኖናል፡፡ ችግራችንን የሚያያ መሪ፤ የተራበን ህዝብ ደጀን የሚሆን አካል እንፈልጋለን፡፡
የአሁኑ ርሃብ የተጋረጠብን ችግር ሂደቶች ሲታዩ  ከኃይለስላሴ  የክፉ ቀን ረሃብ በምን ይለያል ? ተብሉ  ተብሎ ራሳቸው የከበዳቸው ወገኖቻንን ፎቶ ሲወጣ የሚባንን መንግስት ለኔ ሁሌም ጥያቄ ያጭርብኛል፡፡
ምሣሌ የምናገራቸው ምዕራባዊያን በሚዘዋወሩት የሚዲያ ዓለም እነሱ ካላዩን እኛ እራሳችንን እንዳናይ ተረግመናል፡፡ ሂውማን ራይትስዎች ኤርትራን ከወቀሰ ኢቲቪ በደስታ ፈንጥዞ ሪፖርቱን በቀን አስሪ ያቀርበዋል፡፡ ኢትዮጵያንን የተመለከተ መረጃ ያወጣ ሰሞን ደግሞ "ምንነቱ ያልተወቀ ድርጅት እየተባለ ስሙ  ይብጠለጠላል"፡፡ ሃገሪቱን ሲያሞገስ  ደግሞ ሲምገሳ ይከርማል፡፡  ኢቲቪ የኢህአዴግ ግንባር ነው ወይስ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን፡፡
ያለውድ በግድም ስንደሰት  ምናመሰግነው፤ ሲከፋን ብሶታችንን የምንገልጽበት የግል ሚዲያ ዘርፍ ይከፈትልን፡፡ ብሶታችንን የፖርቲ ልሣን ጋዜጠኞች ግን ልንለቅ ስለምንችል መፍትሄ እንሻለን፡፡ ኢቲቪ ግን አቋሙን ይለይልን

የህዝብ ነው ወይስ ?
በህዝብ ስም የሚነግድ ፖርቲ!

No comments:

Post a Comment