………..1.ያጠና ተማሪ በፈተና ሰሞን የማይታይበት ባሕሪ የትኛው ነው?
ሀ. የፈተናው ቀን ብሩህ ሆኖ ይታየዋል፡፡
ለ. የደብተሩ ንፅሕና አያሳስበውም፡፡
ሐ.የደመናው ሙዚቃ ያስፈነድቀዋል፡፡
መ. የውርጭና የጤዛው ቅዝቃዜ አይሰማውም
..………2.ያላጠና ተማሪ ካጠና ተማሪ የሚለይበት ባሕሪ ምንድን ነው?
ሀ. ዕድሉንና አስተማሪዎቹን ያመሰግናል፡፡
ለ.
ሌላው ቢቀር ነፋሱ ያስደስተዋል፡፡
ሐ. ባጠኑ ተማሪዎች ላይ ጥላቻ ያድርበታል፡፡
መ. ወደ ትምህርት ቤቱ ለመሄድ ይጓጓል፡፡
………….3. ደራሲው "ዓይኑን ቢደነቁሉት ፍንክች የማይለው" በማለት የገለፀው የትኛውን ተማሪ ነው?
ሀ. በመውደቅ ተስፋ ያልቆረጠውን
ለ.
ለጥያቄ የማይበረግገውን
ሐ. የሚመጣውን ለመቀበል የተዘጋጀውን
መ.
የመውደቅ ፍራቻ የሌለበትን
..……….4.በፈተና ሰሞን የተረጋጋ መንፈስ የማይኖረው ተፈታኝ የትኛው ተማሪ ነው?
ሀ. አስኮራጅ
ለ. ዓይን አፋር
ሐ. ዘወትር የሚያጠና
መ. የመውደቅ ፋራቻ ያለበት
.……….5.ከኩረጃ ቴክኒኮች ቀላል የሚባሉት የትኞቹ ናቸው?
ሀ. ላብ በመሐረብ መጥረግ፣ መሰላቸት፣ መንጠራራት፣ ማዛጋት
ለ. ዓይን ማቅነዝነዝ፣መቁነጥነጥ ማዛጋት፣ መንጠራራት፣ መሰላቸት
ሐ. ዓይን ማቅነዝነዝ፣ መቁነጥነጥ፣ መሰላቸት፣ መንጠራራት
መ. ሣቅ ሣቅ ማለት፣ ግንባር
መቋጠር፣ ከንፈር መንከስ
.……….6.የተረጋጋ መንፈስ ያለው ተፈታኝ የሚታይበት
ባሕሪ የትኛው ነው?
ሀ. ወደ ፈተና አዳራሽ ሲገባ እግሮቹ ይተሳሰራሉ፡፡
ለ. የት እንደሚቀመጥ አያውቀውም፡፡
ሐ. የጥያቄ ወረቀት ሲታደል ላብ ያጠምቀዋል፡፡
መ. እጁ አይንቀጠቀጥም፡፡
.……….7. አስመሳይ ተፈታኝ ራሱንና ሌሎቹን የማያታልለው በምንድን ነው?
ሀ. በወዛም ፈገግታ ጉራውን በመንዛት፡፡
ለ. በቀላል ፈተና የማለፊያ ውጤት በማግኘት፡፡
ሐ. ከሐምሳ በላይ ውጤት በማግኘት፡፡
መ. በአቦ ሰጡኝ(በግምት) መልስ በመስጠት፡፡
.……….8."ምንም አላጠናሁም፤ ዘንድሮ ወዳቂ ነኝ" የሚለው ተፈታኝ ከአስመሳይ ተፈታኝ በምን ይለያል?
ሀ. ራሱን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡
ለ. የትምህርት ውጤቱ ከመቶው
95 ነው፡፡
ሐ. አለባበሱና አቋሙ ያምራል፡፡
መ. ድምፁ ያልሰለለ ነው፡፡
.……….9. ለምንባቡ የሚስማማው ርዕስ የትኛው ቢሆን ይመረጣል?
ሀ. የኩረጃ ዘዴዎች ለ. የፈተና ሰሞን
ሐ. የኮራጅና አስኮራጅ ውሎ መ. የተፈታኞች የኩረጃ ቴክኒኮች
.……….10. ደራሲው “ለኩረጃ የሚውለው ጭንቅላት ለትምህርት ቢውል ምን ነበረበት” ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው?
ሀ. ኩረጃ ለትምህርት ተግባር ይዋል
ለ. ከመኮረጅ ይልቅ ማስኮረጅ ይገባል
ሐ. የመኮረጃው ጭንቅላት ለትምህርት ይዋል
መ. የሚኮረጅ ትምህርት ለመማር ይቀላል
መመሪያ ሁለት፡- ምንባቡን መሠረት በማድረግ በ“ሀ” ሥር ለተዘረዘሩት ፅንሰ ሐሳቦች ከ“ለ” ጋር በማዛመድ የመልሱን ፊደል
ብቻ በግራ በኩል በተሰጠው ክፍት ቦታ ላይ ፃፉ፡፡ (21 ነጥብ)፡፡
ሀ ለ
…..11. ሲኮርጅ የሚያዝ ተፈታኝ ሀ. ኩረጃ፡፡
…..12. ደፋር የሆነ የፈተና ጠላት
ለ. ዓይኑ ዕንባ ያቀራል፡፡
…..13. ዓይን ቀቅሎ የበላ ደረቅ ኮራጅ ሐ. ዓይኑን ተክሎ ያያል፡፡
…..14."አልኮርጅም፤ መልሱን አውቀዋለሁ" መ.ይስቃል፣ ግንባር ይቋጥራል፡፡
…..15. ቀላል የኩረጃ ዘዴ
ሠ. ማዛጋት፣ መንጠራራት…
...…16. አስተማሪ የሚያበግኑ ተፈታኞች
ረ. ፈታኙ እያያቸው ይኮርጃሉ፡፡
...…17. ከፈተና የማይቀሩ ተፈታኞች
ሸ. ዓይን አፋር ይሆናል፡፡
...…18.የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቀ.ፈገግታ ማብዛት፣ መሽኮርመም
በ. የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች
ተ.ወረቀት
መለዋወጥና ምልክት
መመሪያ አራት፡- የሚከተሉትን የተዘበራረቁ ዓረፍተነገሮችን በቅደም ተከተል በማስተካከል አንድ የተሟላና ተጠይቃዊ የሆነ አንቀፅ
በመልስ መስጫው ክፍት ቦታ ላይ ፃፉ፡፡ (14 ነጥብ)፡፡
§ ሐዲስ በአሥር ብር ከተከራያት ደሳሳ ጎጆው ታዛ
ሥር እግሮቹን አጣምሮ ተቀምጧል፡፡
§ መማር'ኮ በአንድ በኩል ጭንቀትን ማብዛት ሳይሆን
አይቀርም እያለ ያስባል፡፡
§ ጎጆዋን የተከራያት ቀን በሥራ የደከመውን ሰውነቱን
ለማዝናናት ነው፡፡
§ በአሳቡ፤ መዝናናት የሚችሉ የተባረኩ ናቸው ይላል
ደጋግሞ፡፡
§ ግን ለመዝናናት አልቻለም፡፡
§ አሳቡ ግን አንድ አቅጣጫ ይዞ አይጓዝም፡፡ ከ በዓሉ ግርማ (2002፣15)
20.-----------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
------------------------------------------------------------------------------፡፡
መመሪያ አምሰት፡- ምንባቡን መሠረት በማድረግ ቀጥሎ ለሚቀርቡት ጥያቄዎች አጭር መልስ በመስጠት በመልስ መስጫው ቦታ ላይ ፃፉ፡፡
(35 ነጥብ)፡፡
ምንባብ ሁለት
የመጀመሪያውን ምዕራፍ ተቃውሞ ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው በ 1928 ዓ.ም. ማለቂያ ላይ የተደረገው በቅጡ ያልተቀናጀው
አዲስ አበባን የማጥቃት እርምጃ ነው፡፡ በዕቅዱ መሰረት ከገጠር የአርበኞቹ ኃይል በተለያየ አቅጣጫ ሲያጠቃ፣ ከተማው ውስጥ ደግሞ
ሕዝባዊ አመፅ ተቀስቅሶ የኢጣሊያን አገዛዝ በአጭሩ ለመቅጨት ነበር፡፡ ከገጠር የሚያጠቁት በሰሜን በኩል አበራና አስፋው ወሰን ካሳ፣
በደቡብ ደጃች ባልቻ ሳፎ፣ በሰሜን ምእራብ ባላምባራስ አበበ አረጋይ፣ በምስራቅ ደግሞ ደጃች ፍቅረማሪያም ይናዱ ነበሩ፡፡ የአርበኞቹን
መንፈስ በማነቃቃት ከፍተኛ ሚና የተጫወተው የኢጣልን አገዛዝ በፅኑ የሚቃወመው የወሎው ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ ነበር፡፡ የሆነ ሆኖ
ይሕ ብዙ ኃይሎችን ያቀፈ ዕቅድ በሕብረት የጣሊያንን ጦር ማጥቃቱ ቀርቶ የተበታተኑ ጀብዱዎች የታዩበት ሆነና ተሰናክሎ
ቀረ፡፡
የኢጣልያ ፋሺዝም ፅልመታዊ ገፅታ ቁልጭ ብሎ የወጣው በየካቲት 12፤ 1929 ነው፡፡ አብርሀ ደቦጭና ሞገስ
አስገዶም የተባሉ ሁለት ወጣቶች በግራዚያኒ ላይ ቦምብ ጥለው ካቆሰሉት በኋላ አዲስ አበባ ላይ መዓት ወረደባት፡፡ “ጥቁር ሸሚዝ”
እየተባሉ የሚታወቁት የፋሺስት ደቀ መዛሙርት በፋሺስቱ አገዛዝ አይዞህ ባይነት አዲስ አበባን ቄራ አደረጓት፡፡ የጭፍቸፋው ተቀዳሚ
ኢላማ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ይህ የምሁራን ጭፍጨፋ አንድ ትውልድ እንዳለ ያጠፋ በመሆኑም በሐገሪቱ የፖለቲካና ምሁራዊ
ታሪክ ላይ የማይሽር ቁስል ጥሎ አለፈ፡፡ ይህ የፋሽስት ጭፍጨፋ በሌላ መልኩ በወራሪና ተወራሪ መካከል ያለውን ቅራኔ መካረር በማመልከት
የፀረ ኢጣልያ ተቃውሞውም ከመጀመሪያው ወደ ሁለተኛው ምዕራፍ፣ ከመደበኛ ወይም ከፊል መደበኛ ጦርነት ወደ ሽምቅ ውጊያ መሸጋገሩን
አረጋገጠ፡፡
ይህንን ሁለተኛ የተቃውሞ ምዕራፍ በተመለከተ ማለት የሚቻለው አንድ አብይ ነገር ሐገር አቀፍ መሆኑ ነው፡፡
ምንም እንኳ የአርበኞቹ እንቅስቃሴ ጎላ ብሎ የሚታየው በሸዋ፣ በጎጃምና በበጌምድር ቢሆንም ጣሊያኖች ያለተቃውሞ የገዙት ክፍለ ሀገር
አልነበረም፡፡ ሐገሪቱ በታደለችው ተፈጥሮ ምሽጎች እየተጠቀሙ ደፈጣ ተዋጊዎች ጣሊያኖችን ጤናና ፋታ ነሷቸው፡፡ እንደማንኛውም ደፈጣ
ተዋጊዎች ሁሉ ትልቁ የትግል መሳሪያቸው በፍጥነት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀሳቸውና እንደአስፈላጊነቱ ለመበታተንና ለመሰባሰብ መቻላቸው
ነበር፡፡ ምንም እንኳ አባዛኛዎቹ የአየር መቃወሚያ መሣሪያ ባይኖራቸውም በዚህ የትግል ስልታቸው አማካኝነት ጣሊያኖችን መጀመሪያ
በሁሉም ጦር ግንባር የነበራቸውን የበላይነት ነሷቸው፡፡
የአርበኞቹ አብይ ችግር የስንቅ እጥረት ነበር፡፡ ብዙውን ጊዜ ቀለባቸውን ማግኘት የሚችሉት መከረኛውን ባላገር
በማስጨነቅ ሆነ፡፡ በዚህም ረገድ በየገበሬው ቤት ፋኖ እስከ መምራት ተደርሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ሻል ያለ ሠራዊቱን የመቀለብ
ዘዴ መሞከሩ አልቀረም፡፡ ባንዳንድ ቦታዎች ሠራዊቱ በሁለት ተከፍሎ “ደረቅ ጦር” የተባለው ሙሉ በሙሉ በውጊያው ላይ ሲያተኩር
“መደዴ ጦር” የተባለው ግን ውጊያው ተግ ሲል በእርሻ ተግባር እንዲሰማራ
ተደርጓል፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ ከጠላት ጋር ያበሩ ሰዎችን እህል በመዝረፍ ሕሊናን ብዙ በማያውክ መንገድ የሰራዊቱን ቀለብ ማበራከት
ተችሏል፡፡ ሲከፋ ሲከፋ ደግሞ የዱር አራዊት ማደንና ፍራፍሬ እየለቀሙ መብላትም የተለመደ ነበር፡፡
በአጠቃላይ መልኩ ስናየው የአርበኞች የነፃነት ትግል በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ አኩሪ ምእራፍ
ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን ለአርነትና ለነፃነት ሲሉ ለመሞት ዝግጁ ለመሆናቸው አንድ ሌላ ማረጋገጫ ነው፡፡ ትግሉን የበለጠ ግምት የሚያሰጠው
የወራሪውን ኃይልና ጭካኔ በመገንዘብ አመች የሆኑ አዳዲስ ስልቶች ለመቀየስ መቻሉ ነው፡፡ አርበኞች በጠላት ላይ ያገኟቸው ድሎች
የወሳኝነት ባሕሪ ባኖራቸውም የኢጣልያ ሰራዊት በአርበኞች ጥቃት ተደናብሮና ተጎሳቅሎ በመጨረሻ እንግሊዞች አገሪቱን ነፃ ለማውጣት
ለከፈቱት ዘመቻ ክፉኛ ተጋለጠ፡፡ ከ ባሕሩ ዘውዴ (2002) የተወሰደ፡፡
21. በ1928 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ የተካሄደው የመጀመሪያው ምዕራፍ የአርበኞች ተቃውሞ የገጠርና የከተማ ዕቅድ ምንድን ነው? (5 ነጥብ)::
22. በከተማና በገጠር የተነደፈው ዕቅድ ለምን ሳይሳካ ቀረ? (5 ነጥብ)::
23. የምሁራኑ ጭፍጨፋ በሐገሪቱ የፖለቲካና ምሁራዊ ታሪክ
ላይ የማይሽር ቁስል ጥሎ አልፏል የተባለው ለምንድን ነው?(5 ነጥብ)::
24. በአርበኞች ተጋድሎ ወቅት ትልቁ የትግል መሣሪያቸው
ምንድን ነበር? (5 ነጥብ)::
25.የአርበ ኞቹን የስንቅ እጥረት ለማቃለል “የመደዴ ጦር”ና “የደረቅ ጦር” ተግባራት ምንምን ነበሩ? (5 ነጥብ)::26. እንደ ደራሲው ዕምነት “የአርበኞች የነፃነት ትግል በዘመናዊ የኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ አንድ አኩሪ ምዕራፍ ነው፡፡” የሚያስብለውን ምክንያት በአጭሩ ግለፁ?(5 ነጥብ)፡፡
ማረጋገጫ
ይህንን ጥናታዊ ፅሁፍ ያዘጋጀሁት እኔ መሆኔን እያረጋገጥኩ
ማንኛውንም ሐሳብ፣ ዕውነታና የመረጃ ምንጭ ማዛባት የፈጠራ ሥራ በመጨመር ሙያዊ ታማኝነትና ሐቀኝነትን ማጉደል በዩንቨርስቲው የሥነ
ምግባር እርምጃ እንደሚያስወስድና ምንጮችን በትክክል አለመጥቀስ እንደሚያስጠይቅ ጥብቅ ዕምነት አለኝ፤ በመሆኑም በዚህ ጥናት የተጠቀምኩባቸው
ድርሳናት ዋቢነታቸው በትክክል የተጠቀሰ መሆኑንም በፊርማየ አረጋግጣለሁ፡፡
ፊርማ፡-------------------------
የተማሪው ሥም፡---------------------
---------------
የዩንቨርስቲው መ.ቁ.-----------------
ቀን፡--------------/------------/2004
ዓ.ም.
ይህ ጥናታዊ ፅሁፍ የተጠናቀቀ በመሆኑ ለፈተና እንዲቀርብ
ተስማምቻለሁ
ፊርማ፡--------------------
የአማካሪ ሥም------------------- ------------------
ቀን፡--------------/------------/2004 ዓ.ም.
No comments:
Post a Comment