ምዕራፍ
አራት፡- የውጤት
ትንተናና ማብራሪያ
ጥናቱ ዓላማ አድርጐ የተነሳው በተማሪዎች
የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ ለመመርመር
ነው፡፡ ለዚህም እንዲረዳ በመጠይቅ አማካኝነት
የተማሪዎች
የማንበብ አመለካከት፣
በአንብቦ የመረዳት ፈተና ደግሞ የተማሪዎች
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ውጤት በመረጃነት
ተሰብስቧል፡፡
ስለዚህ የጥናቱ ትኩረት የተማሪዎችን የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ በመፈተሽ የተማሪዎችን
የማንበብ አመለካከት አቅጣጫ ለማመልከት ነው፡፡
በዚህ ላይ የተመሰረቱት
የጥናቱ ውጤት ትንተናና የውጤቱ ማብራሪያ በቅደም ተከተል እንደሚከተለው
ቀርበዋል::
4.1.የውጤት ትንተና
የጥናቱ የመጀመሪያው መሪ ጥያቄ "በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ተዛምዶ አለ?" የሚል
ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የተማሪዎቹ የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ በፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ
ቀመር ተሰልቷል፡፡ ውጤቱም ቀጥሎ በሰንጠረዥ 1 ተመልክቷል፡፡
ሠንጠረዥ 1፣የማንበብ አመለለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ በፒርሰን የተዛምዶ መወሰኛ ቀመር፡፡
ተላውጦ
|
የናሙና
ብዛት
|
አማካይ ውጤት
|
መደበኛ ልይይት
|
ተዛምዶ
|
|
1
|
2
|
||||
1. የማንበብ አመለካከት
2. የአንብቦ መረዳት
ችሎታ
|
270
|
85.49
59.30
|
11.86
14.50
|
1.00
0.053*
|
1.00
|
የጉልሕነት ደረጃ P>0.05*
በሠንጠረዥ 1 ላይ ለማየት እንደሚቻለው የተማሪዎቹ የማንበብ አመለካከት አማካይ ውጤት ከሚጠበቀው ውጤት (72) ከፍ ያለ
(85.49) ሆኖ ተገኝቷል፡፡ የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውም ከሚጠበቀው አማካይ ውጤት (50) በላይ (59.30) ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
ነገር ግን በማንበብ አመለካከትና በአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል የታየው ተዛምዶ (r=0.053,P>0.05) ቢሆንም ጉልህ
ግን አይደለም፡፡ በተላውጦዎቹ መካከል የታየው የተዛምዶ መጠን የጋራ ባሕሪ በመቶኛ ሲሰላ ከአንድ በታች (0.28%) ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ከዚህ በመነሳት በሁለቱ ተላውጦዎች
መካከል ያለው ተዛምዶ በጣም ዝቅተኛ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ይህም የማንበብ አመለካከት መኖር ወይም አለመኖር ከአንብቦ መረዳት
ችሎታ ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም፤ ቢኖርም በጣም አነስተኛ ነው ለማለት የሚያስችል ይመስላል፡፡
በመቀጠልም
የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ጉልህ ድርሻ ይኖረው ወይም አይኖረው እንደሆን ለመለየት
ትንተና ተደርጓል፡፡ ለዚህም የጥናቱ መሠረታዊ ጥያቄ "የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ
ድርሻው ምን ያህል ነው?" የሚል ሲሆን፣ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የቀላል ድኅረት ትንተና (Simple Regression) ተደርጓል፡፡ ውጤቱም በሰንጠረዥ 2 ላይ እንደሚከተለው ተመልክቷል፡፡
ሠንጠረዥ 2፣ የማንበብ አመለካከት
አንብቦ የመረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻ በቀላል ድኅረት ትንተና (Simple Regression)
ተላውጦ
|
የተጋርቶ
መጠን
R²
|
ድኅረታዊ መጣኝ
Coefficient
|
መደበኛ
ድኀረታዊ መጣኝ
Beta (β)
|
የቲ- ዋጋ
T-
Statstics
|
የስሕተት
ይሁንታ
Significance
|
የማንበብ አመለካከት
|
0.003
|
0.065
|
0.053
|
0.873
|
0.383
|
ጥገኛ ተላጦ = የአንብቦ
መረዳት ችሎታ ውጤት
የሠንጠረዥ 2
የቀላል ድኅረት ትንተና (Simple Regression)
ውጤት እንደሚያመለክተው የማንበብ አመለካከት በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ ያለው ድርሻ (R² = 0.003፣ F=0.762፣ P>0.05) ጉልህ ሆኖ አልተገኘም፡፡ ይህም ተላውጦው በተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ጉልህ ድርሻ ወይም አስተዋፅኦ እንደሌለው
ያመለክታል፡፡ ወይም ደግሞ የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት መኖር ወይም አለመኖር በአንብቦ መረዳት ውጤታቸው ላይ የሚያመጣው
ተፅዕኖ አይኖርም ማለት ነው፡፡
ተላውጦው
በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ ያለው ቀጥተኛ ተፅዕኖ ወይም ድርሻ ምን ያህል እንደሆነ ለማወቅ በመደበኛ ድህረታዊ መጣኝ (Beta Coefficient) ተሰልቷል፡፡ በዚሁ መሰረት የማንበብ አመለካከት በአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ
ያለው ተፅዕኖ (β = 0.053፣ t = 0.873፣ P>0.05) ሲሆን፣ ይህም የማንበብ
አመለካከት በአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ጉልህ ድርሻ እንደሌለው ያመለክታል፡፡ ከዚህም በመነሳት የማንበብ አመለካከት በአንብቦ መረዳት
ችሎታ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በጣም አነስተኛ ነው ወይም ጭራሹኑ የለም ለማለት ይቻላል፡፡
ከሠንጠረዥ 2 ለመረዳት እንደሚቻለው በዚህ የተማሪዎች
የማንበብ አመለካከት ድርሻ በአንብቦ መረዳት ላይ የተጋርቶ መጠን መለኪያ R² (Coefficient of
Detrmination) R²=0.003 ነው፡፡
ከዚህ በመነሳት የማንበብ አመለካከት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር 0.3% የልይይት መጠን
ይጋራሉ ወይም የማንበብ አመለካከት በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ውጤት ላይ በዚህ ልክ ተፅዕኖ አሳድሯል ለማለት ይቻላል፡፡
የዚህ ጥናት ሶስተኛ መሠረታዊ ጥያቄ "በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት ያሳያል?" የሚል ሲሆን፣ ይህንን ለመመለስ ባለሁለት ናሙና ቲ-ቴስት ተግባራዊ ሆኗል፡፡
ውጤቱም እንደሚከተለው በሰንጠረዥ 3 ቀርቧል፡፡
ሠንጠረዥ 3፣ የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ በፆታ (በባለሁለት ናሙና ቲ-ቴስት)
ተላውጦ
|
ፆታ
|
የተሳታፊ ብዛት
270
|
አማካይ ውጤት
|
መደበኛ ልይይት
(SD)
|
የነፃነት ደረጃ
(df)
|
የቲ-ዋጋ
(t-test)
|
የይሁንታ
ስህተት
(Sig.)
|
የማንበብ አመለካከት
|
ወንድ
|
129
|
84.75
|
12.32
|
268
|
-1.011
|
0.313
|
አንብቦ መረዳት
|
58.84
|
14.48
|
- 0.496
|
0.620
|
|||
የማንበብ አመለካከት
|
ሴት
|
141
|
86.22
|
11.50
|
-1.011
|
0.313
|
|
አንብቦ መረዳት
|
59.72
|
14.62
|
-0.496
|
0.620
|
ሰንጠረዥ 3
እንደሚያመለክተው የወንድ ተማሪዎች የማንበብ አመለካከት አማካይ ውጤት (84.75) ከሴቶቹ አማካይ የማንበብ አመለካከት ውጤት (86.22) ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የወንዶች መደበኛ ልይይት (12.32) ከሴቶች መደበኛ ልይይት (14.48) ዝቅ ያለ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ይህም ሴት ተማሪዎች ከወንድ
ተማሪዎች የተሻለ የማንበብ
አመለካከት ቢያሳዩም (t = -1.011፣ df = 268፣ P=0.313) ልዩነቱ የቲ-ዋጋ
ግን ጉልህ ባለመሆኑ ልዩነት አላቸው ለማለት አያስደፍርም፡፡
በተጨማሪም የተማሪዎቹን የአንብቦ መረዳት ችሎታ (ከሰንጠረዥ 3 ለመገንዘብ እንደሚቻለው) የወንድ ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት
ችሎታ አማካይ ውጤት ከሴቶቹ ዝቅ ብሎ (58.84) የተገኘ
ሲሆን፣ የሴቶቹ ተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ከወንዶቹ በልጦ (59.72)
ተገኝቷል፡፡ መደበኛ የልይይት መጠናቸው የወንዶቹ (11.50) ሲሆን፣
የሴቶቹ ደግሞ (14.62) መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህም በአንብቦ መረዳት ችሎታ ከወንዶቹ ይልቅ ሴቶቹ ተማሪዎች
(t= -0.496 df = 268፣ P= 0.620) የተሻለ ልዩት እንዳላቸው ቢያመለክትም ልዩነቱ የቲ-ዋጋ ጉልህ ባለመሆኑ የጎላ
ልዩነት አላቸው ለማለት አያስችልም፡፡
በአጠቃላይ የውጤት ትንተናው እንዳመለከተው የጥናቱን ዓላማ ከግቡ ለማድረስ
በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ ለመመርመር
ተችሏል፡፡ በጥናቱ ለተነሱት ሶስት ጥያቄዎችም
መልስ ተገኝቷል፡፡ በዚህም በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ተዛምዶ የለም፡፡ የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ድርሻ
የለውም፡፡ እንዲሁም በማንበብ አመለካከትና በአንብቦ መረዳት ችሎታ ከወንድ ተማሪዎች ይልቅ ሴት ተማሪዎች የተሻሉ ቢሆንም ልዩነቱ
ጉልህ አለመሆኑ በስታስቲክስ ተገልጧል፡፡
4.2.
የውጤት ማብራሪያ
የዚህ ጥናት ትኩረት በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና
አንብቦ የመረዳት ችሎታ መካከል ያለውን ተዛምዶ ይመለከታል፡፡ ስለዚህም በመጠይቅና በፈተና በተሰበሰቡ መረጃዎች አማካኝነት
የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት አንብቦ ከመረዳት ችሎታቸው ጋር ያላቸው ተዛምዶ በንፅፅር
ታይቷል፡፡ የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ጉልህ ድርሻ በፆታ ልዩነት ያሳይ ወይም አያሳይ እንደሆን
ለመፈተሽ በተለያዩ ገላጭና ተንባይ ስታትስቲክሶች ተተንትኗል፡፡
በሰንጠረዥ 1 ላይ
እንደሚታየው ይህ የተማሪዎቹ አማካይ የማንበብ አመለካከት አማካይ ውጤት መጠን (85.49) ከአንበቦ መረዳት ውጤታቸው አማካይ ውጤት
(59.30) አንፃር ሲታይ (r=0.053፣ P>0.05) ተለዋዋጮቹ የሚጋሩት የጋራ ባሕሪ (0.28%) በጣም ዝቅተኛ በመሆኑ
በማንበብ አመለካከትና በአንብቦ መረዳት መካከል ተዛምዶ አልታየም፡፡ ከዚህ በመነሳት ተማሪዎቹ ከፍተኛ የሆነ የማንበብ አመለካከት
ቢኖራቸውም የአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ግን አነስተኛ ነው ለማለት ይቻላል፡፡ ተማሪዎቹ ከፍተኛ የሆነ የማንበብ አመለካከት
እያላቸው በአንብቦ መረዳት ችሎታቸው ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘገቡበት ምክንያት ምናልባት ተማሪዎቹ የቀረበላቸውን ንባብ በግልፅና
በትክክል አለመረዳት ሊሆን ይችላል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎቹ የንባቡን ይዘት፣ መዋቅርና ቴክስት የመተቸት ብቃታቸው አናሳ በመሆኑ
ሳይሆን አይቀርም፡፡ ይህም ምክንያት በሳላበስ
(2008)፣ በፒትስቸር
(2010)፣
በናንሲ
(1989) ጥናት ከተገለጠው
ሐሳብ ጋር የሚስማማ ይመስላል፡፡ በሌላ በኩል ግን የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት ከአንብቦ የመረዳት ችሎታ ጋር ተዛምዶ
አለመኖር አቡ-ራቢያ (1996) የቴክስቱ ይዘት ሳይሆን የቴክስቱ ቋንቋ አንብቦ ለመረዳት
ተፅዕኖ አሳድሯል፤ ግሪአኒ (1987) የመኖሪያ አካባቢና
የማንበቢያ ትርፍ ጊዜ ተዛምዶ አላቸው፤
ቡክሆረስት-ሄንግና ፔሪራ (2008) ትርፍ ጊዜን በንባብ
ተግባር ላይ አለማዋል በማንበብ አመለካከት ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል በሚል ከደረሱበት ድምዳሜ ጋር ተደጋጋፊ አይደለም፡፡ በተጨማሪም
የምርምሮቹ ውጤቶች ያልተደጋገፉበት ምክንያት ምርምሮቹ የተካሄዱት በተለያዩ አካባቢዎችና የተለያዩ ባሕላዊ ዳራ ባላቸው ተማሪዎች
በመሆኑ ሊሆን እንደሚችል መገመት ይቻላል፡፡
በትንተናው ለማሳየት
እንደተሞከረው ጥናቱ ትኩረት ያደረገበት ሌላው ጉዳይ የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታን በመተንበይ ረገድ የሚኖረውን ጉልህ ድርሻ ይመለከታል፡፡ በሰንጠረዥ 2 ላይ
እንደተመለከተው የማንበብ አመለካከት በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ ያለው ድርሻ (R² = 0.003፣ F = 0.762፣ P>0.05) ሲሆን፣ ይህም ተለዋዋጩ በተማሪዎች የአንብቦ መረዳት
ችሎታ ላይ ጉልህ ድርሻ ወይም አስተዋፅኦ እንደሌለው ያመለክታል፡፡ ከዚህ ባሻገር የማንበብ አመለካከት በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ ያለው ድርሻ (β = 0.053፣ t = 0.873፣ P>0.05) ሲሆን፣ ይህም የማንበብ አመለካከት አንብቦ የመረዳት ችሎታ ድርሻ
እንደሌለው ያመለክታል፡፡ በተጨማሪም በማንበብ አመለካከትነ አንብቦ የመረዳት ችሎታ የተጋርቶ መጠን
መለኪያ R² (Coefficient of Detrmination) R² = 0.003
ወይም 0.3% ሆኖ
ተገኝቷል፡፡ ከዚህ በመነሳት የማንበብ አመለካከት ከአንብቦ የመረዳት ችሎታ ጋር 0.3% የልይይት መጠን ይጋራሉ ወይም በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ በዚህ ልክ ተፅዕኖ አሳድሯል ለማለት ይቻላል፡፡
ከጥናቱ ውጤት ለመረዳት እንደሚቻለው የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታን ለመተንበይ ያልቻለበት ምክንያት ተለዋዋጮቹ
ተዛምዶ ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ የዚህ ጥናት ውጤት የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታን
የመተበይ ጉልህ ድርሻ አለው ከሚለው ከዴይና ባምፎርድ (1982)፣ ከኮንሊ (1992)፣ ከአሌክሳንደርና ፊለር (1992)፣ ከሮኢና ስሚዝ
(2005)
የምርምር
ግኝቶች
ጋር
ሲቃረን፤ የማንበብ
አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻው የጎላ አይደለም ከሚሉት
ከራንስበሪ
(1973)፣
ከሒዚግነቶንና
አሌክሳንደር
(1984)፣
ከማና
እና
ማይሽፍ
(1987)፣
ከሞሪሰን፣
ጃኮብስና
ስዊንያርድ
(1999)፣
ከአፕሊጌትና
አፕሊጌት
(2004)፣
ከስችማይት
(2009)
የምርምር
ግኝቶች
ጋር
ተደጋገፊነት
አሳይቷል፡፡
በሠንጠረዥ
3 ላይ እንደተመለከተው የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት
ችሎታ በፆታ ልዩነት እንዳለውና እንደሌለው የተደረገው የጥናት ውጤት ትንተና እንዳመለከተው በማንበብ አመለካከት ሴት ተማሪዎች ከወንድ ተማሪዎች የተሻለ
አመለካከት ቢታይባቸውም የቲ- ዋጋ ግን ጉልህ ሆኖ አልተገኘም፡፡ በተመሳሳይም የሴት ተማሪዎች አንብቦ መረዳት ችሎታ ከወንድ
አቻዎቻቸው በልጠው ቢገኙም የቲ- ዋጋ ልዩነቱ ጉልህ እንዳልሆነ ያመለክታል፡፡ በመጠይቅና በፈተና የተገኘው የጥናት ውጤት
ከሊናና ካሪም (2007)፣ ከክሪስቲናና ጆናታን (2011)፣ ከዊዊ (2009)፣ ጥናት ጋር ሲደጋገፍ፤
ከናንሲ
(1989) ጥናት ጋር በከፊል ይስማማል፡፡ ነገር ግን
የጥናቱ ውጤት ከሳላበስ (2008)፣ ከባስ (2012)ና ከተራቪስ (2010)፣ የጥናት ውጤት ጋር
አይደጋገፍም፡፡
ከጥናቱ ውጤትና
ከክለሳ ድርሳን የተገኙት መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት
ችሎታ እንዳይጎለብት የሚያደርጉት ምክንያቶች አዎንታዊ የማንበብ አመለካከት እንዲዳብር ትኩረት ባለመሰጠቱ፣ መምህራን የበርካታ
ተማሪዎቻቸውን የማንበብ አመለካከት ዝንባሌ ግምት ውስጥ ሳያስገቡ የዕለት ተዕለት ተግባራቸውን ማከናዎናቸው እንዲሁም ወላጆች
ማንበብን የትርፍ ጊዜ ተግባር አድርገው መቁጠራቸው ናቸው፡፡
በአጠቃላይ ከጥናቱ
ውጤት ለመረዳት እንደሚቻለው የማንበብ አመለካከትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ተዛምዶ የላቸውም፡፡ የተማሪዎች
የማንበብ አመለካከት አንብቦ የመረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ጉልህ ድርሻ የለውም፡፡ በማንበብ አመለካከት ሴት ተማሪዎች ከወንድ
ተማሪዎች የተሻለ አመለካከት ታይቶባቸዋል፡፡ ልዩነቱ ጉልህ ባይሆንም የሴት ተማሪዎች አንብቦ የመረዳት ችሎታ ከወንድ አቻዎቻቸው
ጋር ሲነፃፀር ብልጫ አለው፡፡ በአሌክሳንደርና ፊለር (1976)፣
ዊየርና ዊየር (1994)፣ በብሮምፊ (2004)፣ በማክኪና፣ ኪአርና ኢልስዋርዝ (1995)፣ በራሲኒስኪና ፓዳክ (2000) እንደተጠቆመው
ለነዚህ የጥናት ውጤቶች ግኝት እንደ አሉታዊ ምክንያት የሚጠቀሱት የተማሪዎች የማንበብ
አመለካከቶች ብቻ ሳይሆኑ መምህራን በትምህርት ቤት፣ ወላጆች በመኖሪያ ቤት እንዲሁም በአካባቢያቸው በማንበብ አመለካከታቸው ላይ
ተፅዕኖ ስለሚያደርሱባቸው ሊሆን ይችላል፡፡
ምዕራፍ
አምስት፡- ማጠቃለያ፣ መደምደሚያና መፍትሔ
የጥናቱ
መግቢያ፣ ከጥናቱ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ክለሳ ድርሳናት፣ የአጠናን ዘዴና የጥናቱ ውጤት ትንተናና ማብራሪያ በቅደም ተከተላቸው
መሠረት ያለፉት ምዕራፎች የትኩረት ነጥቦች ነበሩ፡፡ በዚህ ምዕራፍ ደግሞ ማጠቃለያ፣ መደምደሚያና የመፍትሔ ሐሳቦች ይቀርባሉ፡፡
5.1.
ማጠቃለያ
የጥናቱ
ዋና ዓላማ የተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶን መመርመር መሆኑ በቀዳሚዎቹ ምዕራፎች ተገልጧል፡፡
በዚህም መሠረት በጥናቱ መልስ እንዲገኝባቸው የተነሱት መሠረታዊ ጥያቄዎች የሚከተሉት ነበሩ፡፡ በፋሲሎ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ
ትምህርት ቤት የሚማሩ የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች፡-
1. በማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት
ችሎታ መካከል ተዛምዶ አለ?
2. የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት
ችሎታቸውን የመተንበይ ድርሻው ምን ያህል ነው?
3. በማንበብ አመለካከትና በአንብቦ መረዳት
ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት ያሳያል? የሚሉ ናቸው፡፡
ከላይ የቀረቡትን መሠረታዊ ጥያቄዎች
በአስተማማኝነት ምላሽ ለመስጠት እንዲቻልም መጠይቅና ፈተና በመረጃ መሰብሰቢያነት ተመርጠዋል፡፡ ለጥናቱ በሚመች መልኩም ተዘጋጅተዋል፡፡
የጥናቱ ተሳታፊዎች በባሕር ዳር ከተማ በፋሲሎ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2004 ዓ.ም. የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን
በመከታተል ላይ ያሉ ተማሪዎች ናቸው፡፡ ተማሪዎቹ የተመረጡት ከዕድል ሰጭ የንሞና ዘዴ ውስጥ በቀላል የዕጣ
ንሞና አመራረጥ ዘዴ (simple random Sampling) ነው፡፡
ብዛታቸውም 270 ነበር፡፡ በጥናቱ ዋነኛው የመረጃ መሰብሰቢያ መሣሪያ መጠይቅ ሲሆን የተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ ውጤትም
በፈተና አማካኝነት ተገኝቷል፡፡ በመጠይቁ የተካተቱት 25 ጥያቄዎች ናቸው፡፡ እነዚህም በመስኩ በተለያዩ ጊዚያት ምርምሮችን
ያካሄዱት ሮዲና አሌክሳንደር (1980) ካዘጋጁት መጠይቅ የተውጣጡ
ናቸው፡፡ ጥያቄዎቹን ለጥናቱ በሚያመች መልኩ ወደ አማርኛ አሻሽሎ በመተርጎም የማንበብ አመለካከትን እንዲለኩ ተዘጋጅተው ሥራ
ላይ ውለዋል፡፡
የፅሁፍ
መጠይቁ የአማካሪ ማስተካከያ ታክሎበትና በሙከራ ጥናት ተፈትሾ አስተማማኝ ሆኖ በመገኘቱ ለጥናቱ የሚፈለጉት መረጃዎች
ተሰብስበውበታል፡፡ የአንብቦ መረዳት ፈተና ጥያቄዎቹም በአማካሪውና በአማርኛ መምህር ማስተካከያ ተደርጎባቸው በሙከራ ጥናት
ተፈትሸው አስተማማኝ ሆነው በመገኘታቸው የጥናቱ ተሳታፊ ተማሪዎችን የአንብቦ መረዳት ችሎታ ለመለካት ተግባራዊ ተደርገዋል፡፡
በመጠይቅና በፈተና የተሰበሰቡት መረጃዎችም የተለያዩ ገላጭና ተንባይ ስታስቲካዊ ዘዴዎችን በመጠቀም ተተንትነዋል፡፡
በመጠይቅ
አማካኝነት የተሰበሰበውን መረጃ መሠረት በማድረግ የመጀመሪያው መሪ ጥያቄ
በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ተዛምዶ አለ? የሚለው ነበር፡፡ ከዚህ አንፃር የማንበብ አመለካከት ከአንብቦ መረዳት ችሎታ ጋር
ተዛምዶ እንደሌለው የትንተናው ውጤት አመልክቷል፡፡
በሁለተኛ ደረጃም የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ድርሻው ምን ያህል ነው? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ በተደረገው
ጥረት ቀላል የድኅረት ትንተና ተግባራዊ ሆኗል፡፡ በትንተናው መሠረትም የማንበብ አመለካከት በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ላይ ያለው
ድርሻ (R² = 0.003፣ F = 0.762፣ P>0.05) ሲሆን፣ ይህም ተለዋዋጩ በተማሪዎች የአንብቦ መረዳት
ችሎታ ላይ ጉልህ ድርሻ ወይም አስተዋፅኦ እንደሌለው አመልክቷል፡፡ በ
(Beta Coefficient) ተሰልቶ የተገኘው ውጤት እንዳመለከተው ደግሞ የማንበብ አመለካከት በአንብቦ
የመረዳት ችሎታ ላይ ያለው ድርሻ ተንባይ አለመሆኑን ነው፡፡ በተጨማሪም የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታ
ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ በስታትስቲክስ ጉልህ ድርሻ የለውም፡፡
በሦስተኛ ደረጃ የተመረመረው መሠረታዊ ጥያቄ በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ
ልዩነት ያሳያል? የሚለው ነበር፡፡ በዚህ ረገድ ሴት
ተማሪዎች ለማንበብ ያላቸው አመለካከት በአማካይ ውጤት ከወንድ ተማሪዎች አማካይ ውጤት በስታትስቲክስ ጉልህ ብልጫ ቢያሳይም ልዩነቱ
ጉልህ ባለመሆኑ የጎላ ልዩነት አለ ለማለት አያስደፍርም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሴቶቹ አንብቦ የመረዳት ችሎታ ከወንዶቹ በስታትስቲክስ
ጉልህ ብልጫ ቢያሳይም ልዩነቱ ጉልህ ባለመሆኑ ልዩነት አለ ለማለት አይቻልም፡፡
በአጠቃላይ የጥናቱ ትንተና ውጤት እንዳመለከተው የተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ የላቸውም፡፡
የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታን የመተንበይ ድርሻው ጉልህ አይደለም፡፡ በተጨማሪም የሴቶች የማንበብ አመለካከትና አንብቦ
የመረዳት ችሎታ በስታትስቲክስ ከወንዶቹ ተማሪዎች ብልጫ እንዳለው ቢያሳይም ልዩነቱ ጉልህ ባለመሆኑ ልዩነት አለው ለማለት አያስደፍርም
፡፡
5.2.
መደምደሚያ
የጥናቱን
ትንተናና ማብራሪያ መሠረት በማድረግ ከሚከተሉት መደምደሚያዎች ላይ ተደርሷል፡፡
1. በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና
የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ተዛምዶ የለም፡፡
2. የተማሪዎች የማንበብ አመለካከት የአንብቦ
መረዳት ችሎታቸውን የመተንበይ ጉልህ ድርሻው ወይም አስተዋፅኦ የለውም፡፡
3. የማንበብ አመለካከት የአንብቦ መረዳት ችሎታ ላይ ቀጥተኛ
ተፅዕኖ በስታትስቲክስ
ጉልህ ድርሻ የለውም፡፡
4. በተማሪዎች የማንበብ አመለካከትና የአንብቦ መረዳት
ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት ቢያሳያይም ልዩነቱ ጉልህ ባለመሆኑ ልዩነት አለ ለማለት አያስችልም፡፡
5.3.መፍትሔ
በዚህ
ጥናት የተደረሰባቸውን ግኝቶችና ውጤቶች ተግባራዊ ለማድረግ እንዲሁም የተማሪዎችን የማንበብ አመለካከት ለማጐልበት እንዲቻል
የሚከተሉት መፍትሔዎች ተጠቁመዋል፡-
- በጥናቱ የተማሪዎች የማንበብ
አመለካከት በአንብቦ የመረዳት ችሎታ ያለውን የትንበያ መጠን መገንዘብ ስለተቻለ መምህራኑ ይህንኑ በመረዳት የመማሪያ ክፍል
የትምህርት አቀራረባቸው የማንበብ አመለካከትን የሚያሳድግ ብቻ
ሳይሆን ሌሎችንም ዘዴዎች በአማራጭነት ቢጠቀሙ፡፡
- ጥናቱ በተማሪዎች የማንበብ
አመለካከትና የአንብቦ መረዳት ችሎታ መካከል ያለው ተዛምዶ በፆታ ልዩነት እንዳለው ስለሚያሳይ ወላጆች የልጆቻቸውን የማንበብ
አመለካከትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ በመገንዘብ ለችግሮቻቸው ከመምህራን ጋር በመተባበር መፍትሄ ቢፈልጉ፡፡
3. የትምህርት ባለሙያዎች
በጥናቱ ግኝቶች መረጃ መሠረት የተማሪዎችን የማንበብ አመለካከትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ በመገንዘብ መምህራን የትምህርት ዕቅድ፣
መርሐ ትምህርትና የንባብ ትምህርት መርሐ ግብር ሲያዘጋጁ የተማሪዎቹን የማንበብ አመለካከትና አንብቦ የመረዳት ችሎታ ከማጎልበት
አንፃር እንዲመለከቱት ቢጠቁሙ፡፡
4. በርዕሱ ዙሪያ
ተጨማሪ ጥናት የሚያደርጉ ተመራማሪዎች ይህንን ጥናት እንደ መነሻ በማድረግ ከዚህ የተሻለ ጥናት ለማካሄድ ጥረት ቢያደርጉ፡፡ የሚሉት በአጥኝው የቀረቡ
የመፍትሄ ሐሳቦች ናቸው፡፡
ዋቢዎች
መሐመድ ዓሊ፡፡ (1992 ዓ.ም)፡፡ ‘‘በባሕር ዳር ከተማ የግዩን ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ
ክፍል ተማሪዎች የአማርኛ ቋንቋን ለመማር ያላቸው አመለካከት፡፡'' ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ)፡፡
መስፍን ኃብተማሪያም፡፡ (2001) የቡና ቤት ስዕሎችና ሌሎችም ወጐች (1976-1999)፡፡ ኤማይ ፕሪንተርስ ኃ.የተ.የግ.ማ፡፡ አዲስ
አበባ፡፡
በዓሉ ግርማ፡፡ (2001)፡፡ የሕሊና ደወል፡፡ (2ኛ ዕትም)፡፡ ፋር ኢስት ትሬዲንግ፡፡ አዲስ አበባ፡፡
ባሕሩ ዘወዴ፡፡ (2001)፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983፡፡ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፕሬስ፡፡ አዲስ አበባ፡፡
ታፈረ ወርቁ፡፡ (2000)፡፡ ‘‘በዳንግላ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች የንባብ
ዳራና የአንብቦ መረዳት ችሎታ ተዛምዶ፡፡'' ለሁለተኛ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ)፡፡
ታዛሽ ሰይፉ፡፡ (1992 ዓ.ም)፡፡ ‘‘የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች የአንብቦ መረዳት ችሎታ፡፡'' ለመጀመሪያ ዲግሪ
ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ)፡፡
ደምሰው አሰፋ፡፡ (1995)፡፡ ‘‘በ10ኛ ክፍል የአማርኛ መማሪያ መፀሐፍ ውስጥ የሚገኙ ምንባቦች የተማሪዎችን
የማንበብ ፍላጎት ለመያዝ ያላቸው ብቃት፡፡'' ለመጀመሪያ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ)፡፡
ገደፋው አምሳሉ፡፡ (1993)፡፡ ‘‘የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች አማርኛ ቋንቋን ለመማር ያላቸው ተነሳሽነትና የትምህርት
ውጤት ተዛምዶ፡፡'' ለመጀመሪያ ዲግሪ ማሟያ የቀረበ ፅሁፍ፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፡፡ (ያልታተመ)፡፡
Abu-Rabia, S. (1996). Attitudes and cultural
background and their relationship to reading comprehension in a second
language: a comparison of three different social contexts. International
Journal of Applied Linguistics, 6: 81–105.
Doi: 10.1111/j.1473-4192.1996.tb00090.x
Aebersold, J.A., and Field, M.A. (1997).
From Reader to Reading Teacher: Issues
and strategies for second language classrooms. Cambridge Universty Press.
Alexander, J.E., and Filler, R.C.
(1976). Attitudes and Reading.
Newark., DE. International Reading Association.
Appllegate, A.J. and Appllegate, M.D.
(2004). The Peter Effect: Reading Habits and Attitudes of Preservice Teachers.
The Reading teacher, 57, 554-563.
Bas, G. (2012). Correlation
between elementary students’ reading attitudes and their writing dispositions. IJGE:
International Journal of Global Education - 2012, volume 1 issue 2. Konya University. Graduate School of
Education Sciences. Konya, Turkey
Blackb, A.
(2006). Attitudes to Reading: An Investigation across the Primary Years.
Thesis.Master of Education, School of Education, Australian Catholic Universty.
Block, C.C. (1997). Teaching the Language Arts: Expanding Thinking through Student Centered
Instruction .Boston: Allyn and Bacon.
Bokhorst-Heng,
W. and Pereira, D. (2008), Non-at-risk adolescents' attitudes towards reading
in a Singapore secondary school. Journal of Research in Reading,
31: 285–301. Doi: 10.1111/j.1467-9817.2008.00369.x
Christina, C. and
Jonathan D. (2011). Young People's Reading and Writing: An In-Depth Study Focusing on
Enjoyment, Behavior, Attitudes and Attainment. 2011-00-00.
Cramer, M. (1994). Fosternig the Love of reading: The Affective Domain in Reading
Education (PP.74-87).Newyork, DE: International reading Association.
Day, R. and Bamford. (1998). Extensive Readng and In The Second Language
Classroom. U.S.A : Cambridge Universty Press.
Dornyei, Z. (2001). Motivational Strategies in the Language Classroom. Cambridge:
Cambridge Universty Press.
Dubin, B.V, and Zorkaia, N.A (2010). The changes in the attitude of Russia's
Reading public interms of frequency and intensiveness. Russian Education
and Society, v52n7 P16-51 Jul. 2010.
Eiser, J. R., (1994). Social Psychology. Attitudes, cognition and
social behavior. Cambridge University Press.
Estes, T. H. (1971). A Scale to Measure
Attitudes Toward Reading. Journal of reading. 15, 135-138.
Evans, K.M., (1965). Attitudes and Interests in Education.
Routlege and Kegan private limited.
Feldman,R.S.,(1996). Understanding Psychology. (4th Ed). McGraw-Hill,
Inc.
Feldman,R.S (1999). Understanding Psychology. (5th Ed). McGraw-Hill, Inc.
Frankel, J.R., and Wallen. (2000). How to design and Evaluate Research in
education. (4th Ed). Mcgraw Hill.
Flood J., and. Lapp, D., (1983). Teaching Reading to Every Child. (2nd
Ed.). Macmillan publishing Co., Inc.
Gambrell, L.B.,(1996). Creating
Classroom Cultures That Foster Reading Motivation. The Reading Teacher, 50,
14-25.
Graves, M.F., Laberge, M.J. and Cooke
C. (1983). Efects of previewing difficult
short stories on low ability junior high school students comprehension, recall
and attitudes. Reading Research
Quarterly. Vol. 18, No. 3, spring, 1983
Greaney, V. and Hegarty, M. (1987). Correlates of leisure-time reading. Journal of Research in Reading, 10: 3–20. Doi: 10.1111/j.1467-9817.1987.tb00278.x
Kulik, A.J. and Kulik C.C. (1982). Effects of Ability Grouping on
Secondary School Students: A
Meta-analysis of Evaluation Findings. American
Educational Research Journalaer.sagepub.com. Doi: 10.3102/00028312019003415. Am Educ Res J September 21, 1982 vol. 19 no.
3 415-428 University of Michigan.
Kush, J.C, and Watkins, M.W. (1996).
Long –Term Stability of Children's Attitudes Toward Reading. [Eelectronic
Version]. The Journal of Educational Reserch.
Heathington, B.S. and Alexander, J.E.
(1984). Do Classroom Teachers Emphasize Attitudes Toward Reading?.The Reading Teacher, 37, 484-488.
Heaton, J.B. (1990). Writing English Language Test. London:
Longman.
Heilman, A.W. Blair,T.R.,and Ruphley
W.H. (1998). Principles and Practices of
Teacing Reading. (9th Ed.).New Jersy prints Hall Inc.
Lena S.and, Karin T. ( 2007). Influences of Family Based Prerequisites, Reading Attitudes,
and Self-Regulation onReading Ability.Contemporary Educational Psychology, v32
n2 p206-230 Apr 2007 Journal of Atricles; Reports – Research.
Logna, S., and Johnston, R. (2009). Gender
Differences in Reading Ability and Attitudes: Examining where these differences
Lie. Jornal of Research in Reading,
V32 n2 P199-214 May 2009.
Lorene, W.C., (2010). ‘‘Secondary
Students' Reading Attitudes and Achievement in a scaffold Silent Reading
Program Versus Traditional Sustained Silent Reading.’’ ProQuest LLC,
Ph.D.Dsessertaion, Auburn University.
Lynn, H.W. (2010). Difference between
third, forth, and fifth Grade students' attitudes to ward reading in relation
to community size. Master of education (MED), Bowling Green state Universty,
reading 2010.
Madsons, H.S. (1983).Teachniques In Testing. Newyork: Oxford
Universty Press.
Martinez, R.S., Tolga, A.o, and Jermy,
J. (2008). Influence of Reading Attitude on Reading Achievement: A Test of the
Temporal Interaction Model. Psychology in the schools, v45 n10 P1010-1022.
Dec.2008.
May, B.F. (1990). Reading as Communication: An Interactive Approach. (3rd
Ed.). U.S.A: Macmillan Publishing Company.
Mckenna, M.C., Kear, D.J., and
Ellsworth, R.A., (1995). Children’s attitudes to woard reading.A national
survey. Reading research quarterly. Retrieved on 01/08/2011 09:59. From http://
WWW.jstor. Org /stable/748205.
Muller, D.L., (1973). Teacher Attitude
Towards reading. Journal of Reading. 17, 202-205.
Myers, G.D. (1999). Social Psychology. (6th Ed). The McGraw-Hill Componies,
Inc.
Norton,D.E.(1997). The
Effective Teaching of Language Arts. (5th Ed.).New Jersy:
Prentice Hall Inc.
Nancy,W.(1989).‘‘ Developmental
relationships between Students’ attitudes Toward reading and Reading Achivement
In Grades 1 through 8’’. Page 95, Education Specialist Thesis, Universty of
Northen Iowa.
Ransbury, M.K. (1973). An Assesment of
Reading Attitude. Journal of Reading, 17,25-28.
Rasinski, T., and Padak, N, (1996). Holistic Reading Strategies Teaching
Children who Find Reading Difficult.
Prentice Hall, Inc.
Roe, B.D., and Smith, S.H., (2005). Teaching reading in today's middle schools,
Houghton Mifflin Company.
Rrowell, G.C., (1972). An Investigation
of Factors Related to Change in Attitude Toward Reading. 972-73*
Vol.5,No.4,Fall.
Sallabas, M.E., (2008). Relationship between 8th Grade
Secondary School Students' Reading Attitudes and Reading Comprehension skills.
Journal of the Faculty of Education. V01, 9, Issue.16 (fall 2008). 141-155.
Retrived on http://WWW.web. Inonu. Edu.tr/ efdergi/ sayi 16/08-Rn.pdf.
Schmitt,E.(2009). ‘‘Four Case
studies:The reading Attituds and Practices of Teachers and students Grade’’.Thesis,Master
of Education in Reading,The graduate College of Bowling Green State Universty.
Skinner, C.E.,(1998). Educational Psychology. (4th
Ed). Prentice-Hall, Inc.
Spiegel, D.L. (1994).
A Portrait of Parents of successful readers. In E.H.NewYork ,DE: International
Reading association.
Thraves, P., (2010). "An Investigation into
Students' Reading Attitudes and Habits Using a Children's Literature
Intervention Programme" CPUT Thesis and Dissertations. Paper 296.
http://dk.cput.ac.za/td_cput/296
Theodore S.K. (2010). Reading Achievement, Attitudes
towards, Reading and Reading Self-Esteem of Historically Low Achieving Students Journal of Instructional Psychology, v37 n2 p184-188 Jun 2010.Journal
Articls; Reports – Research.
Vacca, R.T.And Vacca, J.L.,(1999). Content Area Reading Literacy and Learning
across the Curriculum. (6th Ed). Long Man.
Webb, H.L., (2009). ‘‘The Relationship
between African American Middle School Students' attitudes toward Reading and
their Reading Comprehension Level’’.
Proquest LLC, Ed.D. Unpublished Dissertation, the University of Memphis.
Wie (Veronica) (2009). ‘‘Gender
Difference in Reading Comprehension for Chinese Secondary School Students.’’ A
Seminar Paper Research. Master of Science in Education. Unpublished Thesis. The
Graduate Faculty Universty of Wisconsin-Platteville.
Yaacov, P. (2010). A Meta- Analysis of the
Relationship between Student Attitudes towards Reading and Achievement in
Reading. Journal of Research in
Reading, v33 n4 P335-355 Nov 2010.
Zelalem Berhanu. (2010). ‘‘The Reading Attitudes Preferences and
Habits of First Year Bahir Dar Universty Studentes with Particular Reference To
The faculty of Humanities.’’ Unpublished
Master’s Thesis. Humanities Faculty, Bahir Dar Universty.
Thanks nice ideas
ReplyDeleteGüvenlik filesi
Güvenlik ağı
I love you site site I want everyone to follow this site.
ReplyDeleteOto Servis
Esenyurt oto servis
Avcılar oto servis
Bahcesehir oto servis
Thanks for information.
ReplyDeleteNeon Tabela
Thank you for your valuable information.
ReplyDeleteAdwords Reklamı
Google reklamı
This comment has been removed by the author.
ReplyDeleteThis comment has been removed by the author.
ReplyDelete
ReplyDeleteWe follow you as Gusto informatics.
Avcılar web site
We are happy to follow you as Gusto Computer.
ReplyDeleteLed ekran
İç Mekan Led Ekran
Dış Mekan Led Ekran
Visit Büyükçekmece for a wonderful hall wedding
ReplyDeletehttp://goo.gl/R88amj
ReplyDeleteCountryside wedding is waiting for you
Beylikduzu Kır dugunu
Thanks for your nice information
ReplyDeleteLed ekran
led display
Dıs mekan Led ekran
İç Mekan Led ekran
Thanks for the beautiful aesthetic knowledge.
ReplyDeleteAvcılar oto servis