Wednesday, May 8, 2013


ለቲዩመር ዳግም መመለስ ምክንያቱ ታወቀ
የጤና ተመራማሪዎች ከቲዩመር መከሰት በኋላ እና ከህክምና በኋላ በዕጢ መልሶ ማደግ ምክንያት ነው ያሉትን የስቲም ሴል መለየት መቻላቸው ታወቀ፡፡
በአይጦች ላይ ተደረገ የተባለው 3 የተለያዩ ጥናቶችን መሰረት አድርገው ባለሙያዎቹ እንደሚናገሩት ለቲዩመሩ መልሶ ማደግ ምክንያት የሚሆነው ‹Cancer Stem ceus› ናቸው፡፡ ጥናቱ ‹‹ኔቸር ኤንድ ሳይንስ›› በተባለ ጆርናል ላይ የታተመ ሲሆን በካንሰር ህክምና ረገድ ለረጅም ጊዜ ሚስጥር ሆኖ የቆየውን ችግር ለመቅረፍ እንደሚረዳም ተነግሯል፡፡
ለዓይን እድገት በእርግዝና ወቅት ብርሃን ያስፈልጋል ተባለ
በእርግዝና ወራት ብርሃን ማግኘት ፅንሱ በሚኖረው የአይን እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና እንደሚኖረው አንድ ጥናት አመለከተ፡፡ ኔቸር በተሰኘ ጆርናል ላይ የታተመው ጥናት እንደሚያመለክተው የእርግዝና ጊዜያቸውን በጨለማ ውስጥ እንዲያሳልፉ የተደረጉ አይጦች የወለዷቸው ግልገሎች ከሌሎቹ ጋር ሲነፃፀር የማየት አቅማቸው ደካማ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ጥናቱ እንደሚጠቁመው ከዚህ ግኝት በመነሳት ዓይን ውስጥ ለሚገኙ የደምስሮች ዕድገት ብርሃን አስፈላጊ እንደሆነ አመላካች ነው ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የወባ ትንኝ መድሃኒቱን መቋቋም በመጀመሯ ኢትዮጵያ ዲዲቲን መጠቀም አቆመች ፡፡ ደቡብ አፍሪቃ ዛሬም ጥቅም ላይ ማዋሏን እንደቀጠለች ነው፡፡ኢትዮጵያ ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ ይህን መድሃኒት መጠቀም ማቆሟን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። ዲዲቲ መጠቀም እንዲቀር ለዉሳኔ ካደረሱ ምክንያቶች አንዱ የወባ ትንኝ መድሃኒቱን መቋቋም መጀመሯ ነዉ።
የተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት UNICEF በኢትዮጵያ የወባ በሽታ በሚያሰጋዉ አካባቢ የሚኖረዉን ህዝብ ቁጥር ወደ 50 ሚሊዮን እንደሚጠጋ ይገልፃል። በየዓመቱም እስከ ዘጠኝ ሚሊዮን የሚጠጋ ሰዉ በበሽታዉ እንደሚጠቃ ድርጅቱ በድረ ገፁ አስፍሯል። በሀገሪቱ በህፃናት ላይ ከሚደርሰዉ ሞት 2o በመቶዉ በወባ ምክንያት እንደሆነ UNICEF ያትታል።


በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ መጨረሻ 10 ሺ ሜጋ ዋት ኃይል ለማመንጨት በተያዘው ግብ መሰረት እየተገደቡ ካሉት ግድቦች ውስጥ ግዙፍ የሆነው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እስከአሁን 19 ነጥብ 6 በመቶ ተጠናቋል፣ በዚህ ዓመት መጨረሻም ወደ 26 በመቶ ግንባታው ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡ የግልገል ግቤ 3 አጠቃላይ የፕሮጀክት አፈፃፀምም 71 በመቶ መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገልፀዋል፡፡