Sunday, September 26, 2010

መስቀሉ የት ነው ያለው?

2 comments:

  1. ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ለመወለድ ጊዜ አለው ለመሞትም ጊዜ አለው፡፡›› እንዳለ፡፡(መክ 3፥2)
    ‹‹ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና፡፡›› ማቴ 5፥10 ስደት፡- በቁሙ መስደድ ፣መሰደድ ፣መለየት፣ ቦታን መልቀቅ፣ ከሀገር ከዘመድ መራቅ፣ መፍለስ፣ መነቀል ማለት ነው፡፡ (አ.ኪ.ወ.ክ) ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ የተባሉት እውነትንና ጽድቅን ለማወቅ ወይም ለማስተማር ወይም በምናኔ ምክንያት ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱ፣ እውነትን በመናገራቸው ስለ እውነተኛይቱ ሃይማኖት በመቆማቸው፣ በእግዚአብሔርና በምዕመናን ፊት ሞገስንና መወደድን በማግኘታቸው ምክንያት በመናፍቃን፣ የራሳቸውን ክብር በሚፈልጉ ቀናተኞች ወይም በአላውያን...

    ReplyDelete
  2. ነገሥታት የተሰደዱትን ነፍሳቸውንና ሥጋቸውን ሊያጠፉ ከተነሱት አካላት የሸሹትን፣ ከምንፍቅናና ከስህተት አስተሳሰቦች ራሳቸውን የለዩና ያሸሹትን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡





    በዚህች ጽሑፍ ስለ እውነት በመቆማቸው፣ የእውነተኛይቱ ሃይማኖት ጠበቃ በመሆናቸው ምክንያት ሊገድሏቸውና ሊያጠፏአቸው ከሚፈልጉ መናፍቃንና ምድራዊ ክብርን ከሚፈልጉ ቀናተኞች ስለሚሸሹ እውነተኞች ክርስቲያኖች እንመለከታለን፡፡



    ስለምን መሰደድ ያስፈልጋል? (የስደት ዓላማው ምንድን ነው?)



    1. ለእያንዳንዱ ሰው የተወሰነ ጊዜና ሰዓት አለው

    ለክረምትና ለበጋ፣ ለሀጋይና ለፀደይ ጊዜ እንዳላቸው ሁሉ ለእያንዳንዱ ሰው ለመኖርም ሆነ ለመሞት የተወሰነለት ጊዜ አለው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ‹‹ለመወለድ ጊዜ አለው ለመሞትም ጊዜ አለው፡፡›› እንዳለ፡፡(መክ 3፥2)



    ጌታችን የእኛን ሥጋ የተዋሐደና ከኃጢአት በቀር የሰውን ድካም የገለጠ ስለሆነ እንደሰውነቱ የሠራቸውን ሥራዎች ሁሉ እንድናደርግ ምሳሌውን ትቶልናል፡፡ ቅዱስ አትናቴዮስ እንዳለ እርሱ(ጌታችን) እግዚአብሔር እንደመሆኑ መጠን ለርሱ ጊዜ የሌለውና ጊዜንም የፈጠረ ራሱ ሲሆን ሰው ሆኖ እያንዳንዱ ሰው የተወሰነለት ጊዜ እንዳለው አስተማረን፡፡ ስለዚህም ‹‹ሊይዙት ይፈልጉ ነበር፤ ነገር ግን ጊዜው ገና ስላልደረሰ ማንም እጁን አልጫነበትም›› ተባለለት፡፡ (ዮሐ 7፥30) ራሱም ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም፡፡›› ብሎ ተናገረ፡፡ (ዮሐ 7፥6) (ዮሐ 2፥4) እደገናም ጊዜው በደረሰ ጊዜ ‹‹እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፣ እነሆ ሰዓቲቱ ቀርባለች፣ የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል›› ብሎ ተናገረ፡፡(ዮሐ 26፥45)



    ይህ ለእያንዳንዱ ሰው ለመኖርም ለመሞትም የተወሰነለት ጊዜና እንዴት እንደተወሰነለት ለማንም ሰው የማይታወቅና የተሰወረ ነው፡፡ ይህም ነገር ከቅዱሳን አነጋገር በግልጽ ታውቋል፡፡ ቅዱስ ዳዊት ‹‹የዘመኔን አነስተኛነት ንገረኝ›› በማለት የማያውቀውን ነገር ያውቅ ዘንድ ጠየቀ በሉቃስ 12፥20 ላይ የተጠቀሰው ባለጸጋ ብዙ ዘመን እኖራለሁ ብሎ ሲያስብ ‹‹አንተ ሰነፍ፣ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዷት ይፈልጓታል፣ ይህ ያከማቸኸው ለማን ይሆናል?›› ተባለ፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞንም በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ‹‹ሰውም ጊዜውን አያውቅም›› አለ፡፡ (መክ 9፥12) ይስሐቅም ለልጁ ለኤሳው ‹‹እኔ አረጀሁ፣ የምሞትበትን ቀን አላውቅም›› አለ፡፡ (ዘፍ 27፥2)



    እውነተኛው መምህር መድኅነ ዓለም ክርስቶስ ክርስቲያኖች ጊዜያቸው ሳይደርስ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው እንዳይሰጡ በቃልም በተግባርም አስተማረ፡፡ በቃል ‹‹በአንዲቱ ከተማ መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ›› እንዲሁም ‹‹በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ሥፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል፤ በዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉት ወደ ተራራዎች ይሽሹ፣ በሰገነትም ያለ በቤቱ ያለውን ሊወስድ አይውረድ፣ በእርሻም ያለ ልብሱን ይወስድ ዘንድ ወደ ኋላው አይመለስ፡፡›› ሲል አስተማረ፡፡ (ማቴ 10፥23፣ ማቴ 24፥15-18) በተግባር ደግሞ ገና ትንሽ ሕፃን ሳለ ሄሮድስ ሊገድለው በፈለገ ጊዜ በራሱ መልአክ ዮሴፍን ‹‹ተነሣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ ሽሽ ሄሮድስ ሕጻኑን ሊገድለው ይፈልገዋልና›› ብሎ አዘዘው፡፡ (ማቴ 2.፥13) ወደ ግብጽም ተሰደደ፡፡ ሄሮድስ ሲሞት ደግሞ በአባቱ ፋንታ የነገሠውን ልጁን አርኬላዎስን ከመፍራት የተነሣ ወደ ናዝሬት ሔደ፡፡ (ሉቃ 2፥51) ኋላም አምላክነቱን በሥራው እየገለጠ ሲመጣ ህሙማንን በመፈወሱ፣ እንደነ አልዓዛር ያሉ ሙታንን በማስነሳቱ አይሁድ በቅናት ሊገድሉት በፈለጉ ጊዜ የሰውን ልጅ ሊያድንበት የቆረጠው ጊዜ አልደረሰምና ራሱን አሳልፎ አልሰጠም፡፡



    ቅዱሳን ከመድኃኒታቸው ከኢየሱስ ክርስቶስ በመማር ሁሉን በአግባቡ አደረጉ፡፡ የመሞት ጊዜያቸውን ሳያሳውቃቸው ሊገድሏቸው ለሚፈልጉ ጠላቶቻቸው እጃቸውን አልሰጡም፡፡ ከጌታችን መገለጥ በፊት የነበሩ ቅዱሳን ነቢያት በጌታ ትምህርት ውስጥ ነበሩና ከአሳዳጆቻቸው ሸሹ፤ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ እነርሱ ሲናገር ‹‹ሁሉን እያጡና መከራን እየተቀበሉ እየተጨነቁ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ፣…… በምድረ በዳና በተራራ፣ በዋሻና በምድር ጉድጓድ ተቅበዘበዙ›› አለ፡፡ (ዕብ 11፥37-38) ነቢዩ ኤልያስ ኤልዛቤል ‹‹ነፍስህን ከእነዚህ እንደ አንዲቱ ነፍስ ባላደርጋት…..›› ብላ መልእክት በላከችበት ጊዜ ነፍሱን ሊያድን ሸሸ፡፡ (1ኛ ነገ 19፥2-3) የጌታ ደቀመዛሙርት አይሁድን ከመፍራታቸው የተነሣ ራሳቸውን ደብቀዋል፤ ቅዱስ ጳውሎስም የደማስቆ ገዢ በፈለገው ጊዜ በቅጥሩ ባለ መስኮት በቅርጫት አውርደውት ከእጁ አምልጧል፡፡ (2ኛ ቆሮ 11፥32)



    ስለዚህ ክርስቲያኖች ሁሉ ሰው እንደመሆናቸው ፈቃደ እግዚአብሔር የወሰነላቸውን ጊዜ ስለማያውቁ ሊገድሏቸውና ሊያጠፏቸው ከሚሸምቁባቸው ይሸሻሉ፤ ይሰደዳሉ፡፡



    2. እግዚአብሔርን መፈታተን አይገባም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእያንዳንዱ ሰው የተወሰነለት ጊዜ እንዳለው እንዳስተማረን ሁሉ ክርስቲያኖች ‹‹እግዚአብሔር ያድነኛል፣ እግዚአብሔር ይረዳኛል፡፡›› ብለው ወደ ፈተና ራሳቸውን እንዳይከቱ አስተምሮናል፡፡ በሊቀ ነቢያት ሙሴ አድሮ ‹‹አምላካችሁን እግዚአብሔርን አትፈታተኑት›› አለን፡፡ (ዘዳ 6፥16) በዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ‹‹ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ ራሱ ሄደ አልተባለም፡፡(ማቴ 4፥1) ሐዋርያትን ሲያስተምር ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ›› አለ፡፡ (ማቴ 26፥41) በታላቁ ጸሎትም ‹‹ወደ ፈተና አታግባን›› ብለን እንድንጸልይ አስተማረን፡፡ (ማቴ 6፥13) ራሱም ለሞት ተላልፎ የሚሰጥበት ጊዜ ሲቀርብ ምንም እንኳ አስቀድሞ ሊያድነን የወሰነና ከአባቱ ጋር በፈቃድ አንድ ቢሆንም በፈተና ጊዜ ምን ማድረግ እንደሚገባን ሊያስተምረን ‹‹አባቴ ቢቻልስ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን፡፡›› አለ፡፡ (ማቴ 26፥39) በዚህም ቅዱሳን ራሳቸውን ወደ ፈተና እንዳያስገቡ ፈተናው የግድ ከሆነ ደግሞ ፈቃዳቸውን ለእግዚአብሔር ፈቃድ እንዲያስገዙ አስተማረ፡፡ ዳግመኛም በገዳመ ቆሮንቶስ ዲያብሎስ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ወደታች ራስህን ወርውር፡፡›› ባለው ጊዜ ‹‹ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል›› አለው፡፡ (ማቴ 4፥6-7) ዲያብሎስ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ›› የሚለውን ቀንሶ የተቀረውን በመጥቀስ ጌታን ‹‹ራስህን ወርውር›› አለው ቅዱሳን ‹‹በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ›› ተባለላቸው፤ መንገዳቸው ሁሉ በፈቃደ እግዚአብሔር የሚመራ ነውና፡፡ ፈተናን የሚያመጣ፣ ክርስቲያኖችን የሚያሳድድ ነፍሰ ገዳይ ፣ወርውሮ ለመጣል የሚሞክር ዲያብሎስ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ ራስን ለአሳዳጅ አሳልፎ መስጠት ከዲያብሎስ ጋር መተባበር እግዚአብሔርን መፈታተን ነው፡፡ ስለዚህ ጌታችን ‹‹ጌታን አምላክህን አትፈታተነው›› ብሎ አሳፈረው፡፡



    ቅዱሳን የመድኃኒታቸውን አርአያ ተከትለው መንፈስ ቅዱስ ካልመራቸውና ካላመለከታቸው በስተቀር ያለ አግባብ ራሳቸውን አሳልፈው እንዳይሰጡ ይህም ራሳቸው መግደልና በዚህም የነፍስ ገዳይነት ወንጀል ተሸካሚዎችና የዲያብሎስ ተባባሪዎች እንዳይሆኑ ይጸልያሉ፤ ከጠላቶቻቸውና ከአሳዳጆቻቸው ይሸሻሉ ይሰደዳሉ፡፡

    ReplyDelete