Saturday, September 10, 2011

የጦር ሠራዊት መለዮ ደንብ


የጦር ሠራዊት መለዮ ደንብ
http://addis1879.com/

ኒሻኖችና ሜዳዮች
የክብረ በዓልና የማታ ልብስ በተለበሰ ጊዜ በተለይ ሲታዘዝ ኒሻንና ሜዳይ በግራ ደረት ላይ ይደረጋል፡፡ ሜዳዮች እንደ ተመደቡት የጦርነት ቀን ተራ ይደረጋሉ፡፡ ሜዳዮች ቁጥራቸው የበዛ እንደሆነ ሊደራረቡ ስለማይገባ በሁለት ወይም በብዙ መስመር እንዲደረደሩ ማድረግ ይቻላል፡፡
ጥቃቅን ኒሻኖችና ሜዳዮች
በመንግስት ወይም በሕዝብ ልዩ በዓል ጊዜ በጥሪው ወረቀት ላይ የተመለከተ እንደሆነ የማታ ልብስ ሲለበስ በጥቃቃን የተሰሩ ኒሻኖችና ሜዳዮች  ይደረጋሉ፡፡
የኒሻንና የሜዳይ ማሰልጠኛ ጥብጣብ
የያንዳንዱ ኒሻን ወይም ሜዳይ የጥብጣቡ ወርድና ቁመት ሊያዘው ለኒሻኑ ወይም ለሜዳዩ በተወሰው መጠን ይደረጋል፡፡ ለሜዳዮች ማድረጊያ በግራ ደረት በኮት ላይ ወርዱ 3 .ሳሜ ርዝመቱ በሚያስፈልግ መጠን የሆነ ጥብጣብ ይሰፋል ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ቀጭንና ጠፍጣፋ የብረት ዘንግ ላይ ጥብጣቡ ሳይራራቅ ይደረጋል፡፡
ኒሻኖች የሚደረጉበት ጊዜ
በትልቅ ሰልፍ ጊዜና በማታ ልብስ ላይ በመንግስት በሕዝብ በኦፊሲዬል በዓል ጊዜ ኒሻኖች ይደረጋሉ፡፡ የውጭ አገር መንግስት ኒሻኖች በሸላሚው መንግስት ደንብ በተወሰነው መሠረት በቀኝ ወይም በግራ ደረት ይደረገሉ፡፡ የኢትዮጵያ የጦር መኮንኖች በውጭ አገር ሳሉ የዚያ አገር መኮንኖች ኒሻኖቻቸውን ባደረጉ ጊዜ እነርሱም ኒሻኖቻቸውን ያደርጋሉ፡፡
ጥብጣብና ኒሻን
በመንግስት በዓልና በትልቅ ሰልፍ ጊዜ ወይም የማታ ልብስ ለብሶ በትከሻ የሚነገት ኮርዶን ኒሻን የሚደረግ ሲሆን በቀኝ ትከሻ ላይ ይውልና ከቀበቶ ሥር ሆኖ ይነገታል፡፡ ኮማንደር ኒሻን ያላቸው በትልቅ ሰልፍ ጊዜ ወይም ከማታ ልብስ ጋር ኒሻናቸውን እንዲያደርጉ በተለይ በታወቃቸው ጊዜ የኒሻኑን ጥብጣብ ከኮት ብሳት ስር እንደሚውል አድርገው በአንገት ላይ ያጠልቁታል፡፡ ኒሻኑም እንደሚታይ ይደረጋል፡፡
የመንግስት ኦፊሴዬል ወይም የሕዝብ በዓላት
ሀ/ ግርማዊ ንጉሠ ነገስት ወይም የግርማዊ ንጉሥ ልዩ እንደራሴ ባሉበት የሚከበር በዓል ወይም በተለይ ታዞ ከንጉሠ ነገሥቱ ልጆች አንደኛው ባለበት ሰልፍ ሲደረግና ክበረ በዓል ሊከበር የቤተ መንግስት በዓል ይባላል፡፡
ለ/ በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት ወይም የመንግስት በሆነ ማኅበር ጥሪ (ግብዠ) ሲደረግ እንደ ኦፊሴዬል በዓል ይቆጠራል፡፡
ሐ/ በማንኛውም ዓይነት ማኅበር ጥሪ (ግብዣ) ሲደረግ እንደ ሕዘብ በዓል ይቆጠራል፡፡
የኒሻንና የሜዳይ አደራረግ ተራ
የኒሻንና የሜዳይ አደራረግ ተራ እንዲሁም ኒሻንና ሜዳይ በሚደረግበት ጊዜ የጥብጣቡ አደራረግ ለኒሻንና ለሜዳይ እንደተወሰነው ሆኖ ያደራረጉ ተራ ቀጥሎ ተመልክቷል፡፡
ሀ/ የኢትዮጵያ ኒሻኖችና ሜዳዮች
የሰሎሞን ኒሻን፤ የንግሥተ ሳባ ኒሻን፤የሥላሴ ኒሻን፤የዳግማዊ ምኒልክ ኒሻን፤የኢትዮጵያ ኮከብ ኒሻን፤የቅዱስ ጊዮርጊስ ጦር ሜዳይ፤የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የጦር ሜዳይ፤የዳግማዊ ምኒልክ የውትድርና አገልግሎት ሜዳይ፤የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የብሄራዊ አገልግሎት ሜዳይ፤የአርበኝነት ሜደይ፤የውስጥ አርበኝነት ሜዳይ፤የስደተኝነት ሜዳይ
ለ/ የውጭ አገር ኒሻኖች በየተሰጠበት ቀን ተራ
ሐ/ የውጭ አገር ሜዳዮች በየተሰጠበት ቀን ተራ፡፡
የውጭ አገር ኒሻኖችና ሜዳዮች
ሙሉ ፈቃዳ ለተሰጣቸው ለውጭ አገር ሽልማቶች የኢትዮጵያ ኒሻኖች ደንብ ይጸናባቸዋል፡፡
ኒሻኖቹ ወይም ሜዳዮቹ በደረት ላይ በተደረጉ ጊዜ የነዚህ ሽልማቶች ጥብጣቦች በደረት ላይ አይደረጉም፡፡
የውጭ አገር ሜዳዮች ከጦር ሜዳዮች በቀር ለውጭ አገር ኒሻኖች የተወሰነው ደንብ ይጸናባቸዋል፡፡ የውጭ አገር የጦር ሜዳይ በሁሉም አይነት መለዮ ላይ እንደ ኢትዮጵያ ሜዳይ በግርማዊ ንጉሠ ነገስት ፈቃድ ይደረጋል፡፡
ኮርዶን ኒሻን
በትከሻ የሚነገት ኮርዶን ኒሻን በትልቅ ሰልፍ ጊዜ ይደረጋል፡፡ ከአንድ ዓይነት ይበልጥ ኮርዶን ኒሻን ያላቸው ሰዎች የከፍተኛውን ተራ ያደርጋሉ፡፡ እንዲሁም የሌሎቹን ተራዎች ፕላኮች እንደማዕረጉ ተራ አንድ ወይም ይበልጥ ሊያደርጉ ይቻላል፡፡ወደ ጡረታ በተዛወሩ መኮንኖች ላይ ይህ ደንብ ይጸናል፡፡

የእምዬ ምኒልክ ምርጥ 10 ደብዳቤዎች


የእምዬ ምኒልክ ምርጥ 10 ደብዳቤዎች
http://addis1879.com/index.php?option=com_content&view=article&id=74:---10-&catid=36:dero-neye-zenedero&Itemid=57
‹የኢትዮጵያ አባት› የሚለውን ስም ያተረፉት እምዬ ምኒልክ በስልጣን ዘመናችው የሚያዳርጉአቸው አብዛኛዎቹ ነገሮች ላይ የየዋህነት፤ የደግነት፤ ባህርይ ይታይባቸው ነበር፡፡ ለዚህም በተለያዩ ጊዜያት የተጿጿፏቸው ደብደቤዎች ትልቅ ምስክር ናቸው፡፡ የሥልጣኔ መሠረት የሆኑት እምዬ ምኒልክን በተመለከተ የተለያዩ የባህር ማዶ ፀሐፊዎች ደግነትን ከርህራሄ ያቀናጁ መሪ ነበሩ ሲሉ ፅፈዋል፡፡ በእርግጥም በሃገራቸው ጉዳይ የሚመጣባቸውን ማናቸውንም ነገር በግንባር ቀደምትነት የሚመልሱት አጤ ምኒልክ ለወገኖቻቸው ግን አዛኝ፣ አንድ አዋጅ ሲያወጡ ‹ይሄ አዋጅ ሕዝቤ ይጎዳው ይሆን?› ብለው የሚጨነቁ ነበሩ፡፡ ለዚህም ሕዝቡ ‹እምዬ› የሚለውን ከስማቸው ፊት አስቀድሞ መጥራትን ጀመረ፡፡ ድሮ በዚያን ዘመን እምዬ ምኒልክ የተጿጿፏቸው ደብደቤዎች ዛሬም በዚህ ዘመን፤ ዘመን ተሻግረው ብዙ መልዕክት የሚያስተላልፉ ናቸውና ለዛሬ ምርጥ ናቸው ያልናቸውን 10 ደብዳቤዎቻቸውን እንዲህ አቅርበናቸዋል፡፡
1/ ይድረስ ከራስ ወልዴ
የእነ አዛዥ ወልደ ፃዲቅ ሰበሬ የሚባለውን ቦታ /የአፋር/ የራስ ወልዴ /ኦሮሞዎች/ መቱት፡፡ አምስት /የአፋር ሰዎች/ ሞቱ፡፡ አራት በረት ከብት ተዘረፈ፡፡ ከዚህ ቀደም ዳንዶ ላይ የጨረስነውም ነገር ሁለተኛ እንዲህ ተደረገ ብሎ ለካብኝ፡፡ ይህ ነገር አውነት እንደሆነ እጅግ ክፉ ነገር ነው፡፡ አሁንም የተዘረፈው ከብት ይመለስ፡፡ የሞተውንም /የአፋር ሰው/ ጉማውን አስከፍል፡፡ ከእንግዲህ የአንተ ሰው አገር አጠፋ፤ ሰው ገደለ፣ ከብት ዘረፈ ያሉኝ አንደሆነ አይሆንም፡፡ ከድሃው አልጣላም ካንተ ነው፡፡
ነሐሴ 13 ቀን 1898 ዓ/ም አዲስ አበባ ተፃፈ
2/ ይድረስ ከደጃዝማች ይልማ
የችሎትህን ነገር ጦም የሆነ እንደሆነ እስከአምስት ሰዓት ድረስ፤ ፍስክ የሆነ እንደሆነ እስከአራት ሰዓት ድረስ አስቻለህ ከዚያ በኋላ ግብር መግባት ነው፡፡ ከግብር በኋላ ሶስት ሰዓት አርፈህ ከሰባት ሰዓት ወዲያ እስከ አስር ሰዓት ድረስ የባለቆይታውን  የባለጉዳዩን ሥራ መፈፀም ነው፡፡ እስከ ስድስት ሰዓት፣ እስከ ሰባት ሰዓት ችሎት ማድረግማ ጀሮስ መቼ ይሰማል፤ ልቦናስ መቼ ይስተውላል፡፡ ነገሩስ መቼ ያምራል፡፡ ይህን ለምን አገኘኸው፡፡ እኔ ይህን ሕግ ሰርቼልሃለሁ፡፡ ከዚያ ወዲያ ቃሌን ባትሰማ አንተ ታውቃለህ፡፡ ሽማግሌም የሆኑት ሰዎት ችሎቱ አነሰ ቢሉም ይህን ደብዳቤ አሳያቸው፡፡ ደግሞ እንደራስ መኮንን እሆናለሁ ብለህ ደርቀህ ትቀራለህ፡፡ መበሳጨትም ያመጣል፡፡
ነሐሴ 28 ቀን 1898 ዓ/ም አዲስ አበባ ተፃፈ
3/ ይድረስ ከራስ ተሰማ
ክፉ ለምጄ ልቤ ዋለለብኝ ያልከው እውነትህን ነው፡፡ ከራስ ወልደጊዮርጊስ ጋር እለት እለት በስልክ እንነጋገራለን፡፡ ይህ ትልቅ ተስፋ ነው፡፡ ወደአንተ አገር የሄደውን ስልክ የት ላይ ይሆን የምታገኘው፡፡ ይኸው እስካሁን አልተነጋገርንም፡፡ ያን ትንሽ ልጅ ይዤ ሄድኩ  ያልከውም መልካም ነው፡፡ ፈንጣጣ ያልወጣለት ልጅና ያልተተኮሰ ሸክላ አንድ ነውና ፈንጣጣውን ተከትቦ በሌላ ጊዜ ይመጣል፡፡ ልጁ ግን አፍ እንዲለምድ ካንተ ጋር ይክረምና ኋላ ወደዚህ ይመጣል፡፡
ጳጉሜ 5 ቀን 1898 ዓ.ም አዲስ አበባ ተፃፊ
4/ ይድረስ ከአዛዥ ባደግ
የከተማውን ጉድባ የግቢው ካብ ጨርሼ ደግሞ የውጪውን ጀምሬአለሁ፡፡ ውሃውም ብዙ ምንጭ ተገኘ ብለህ ብትልክልኝ ደስ አለኝ፡፡ መልካም ሆነ፡፡ ዳናሚት ያልከውን ግን ለዚያ አገር ድንጋይ ባሩድ ይሻላል ብዬ ይኸው ሁለት ቁና ባሩድ ከነገመዱ ሰድጄልሃለሁ፡፡ የስልኩም ስራ ተከምባታ የሚጋጠመው ብቻ አይደለም፡፡ ደግሞ ወደ ሲዳማ የሚሄደውን በዱግና በኩል ከአባይ በላይ አድርገህ ከሲዳሞ ወሰን ድረስ የምታስተክል ነህና ለዚህም የሚሆን የስልክ እንጨት እንድታሰናዳ ይሁን፡፡
መስከረም 13ቀን 1899 ዓ.ም አዲስ አበባ ተፃፈ
5/ ይድረስ ለአቶ በሻህ
ለሆቴል ቤት የሚሆን አስር እንጨት ቁመቱ አስራ ሁለት ሜትር፤ ስፋቱ አስራ ሶስት ሳንቲ ውፍረቱ ዘጠኝ ሳንቲ፣ ስድስት እንጨት፤ ቁመቱ አስር ሜትር ስፋቱ አስራ ሶስት ሳንቲ ውፍረቱ ዘጠኝ ሳንቲ፣ አስራ አምስት እንጨት፤ ቁመቱ ስምንት ሜትር ተኩል ስፋቱ አስራ ሶስት ሳንቲ ውፍረቱ ዘጠኝ ሳንቲ፤ ይህን እፈልጋለሁና የቤተክርስቲያኑን እንጨት ሲያደርስልህ ይህንን እንድትሰራ፡፡ ነገሩን ታውቀው ብዬ ነው፡፡ ደግሞም ከዚህ ቀደም የተሰራ ለቤተክርስቲያኑ የማይሆን ለፃፍኩልህ የሚሆን እንጨት የተገኘ እንደሆነ ቁመቱና ስፋቱን እየላክህ ለዚሁ ማድረግ ነው፡፡
ህዳር 21 ቀን 1899 ዓ.ም አዲስ አበባ ተፃፈ
6/ ይድረስ ከወህኒ አዛዥ ወልደ ፃድቅ
ለባላምባራስ ዘለቀ ከገደራ ስልሳ ስምንት ገባር የጠሚትን ሁዳድ ከነአትክልቱ ከነጥማዱ ሰጥቼዋለሁና አንተ ከአስራት በቀር በምንም በምን አትድረስ፡፡ አስራቱ ግን የኔ ነውና እንደዚህ ቀደሙ እየተሰበሰበ እዚያው ከእኛው ጎተራ እንዲገባ ይሁን፡፡
ታህሳስ 1 ቀን 1899 ዓ.ም ተፃፈ
7/ ይድረስ ከወይዘሮ አፀደ
ግራዝማች አደራ የሚባል የአባትሽ አሽከር የደጃዝማች አስፋውን ገንዘብ ደብቋል ቢሉኝ አስሬዋለሁ፡፡ አሁንም እውነት የአባትሽን ገንዘብ መደበቁን ልብሽ የሚያውቀው እንደሆነ መርምሬ ገንዘቡን እንዳስወጣልሽ እውነቱን ነገር ላኪብኝ፡፡ ገንዘብ መደበቁን አላውቅም የምትይ እንደሆነ ግን ሁሉንም  ነገር ላኩብኝ፡፡
ሚያዝያ 26 ቀን 1899 ዓ.ም አዲስ አበባ ተፃፈ
8/ ይድረስ ከደጃዝማች ባልቻ
ይህ ግራዝማች ሱድቄ የሚባል የአንተ አገልጋይ እኔ ዘንድ መጥቶ ያስታርቀኝ አለኝ፡፡ ያንተ ሰዎች እኔ ዘንድ መጥተው ያስታርቁኝ ከማለት በቀር ባንተ ክፋት ነገር ተናግረው አያውቁም፡፡ አሁንም በእውነት ከልብ ምረኸው የተወረሰውንም ገንዘቡን አገሩን መልስለት፡፡ ታርቀህ ተስማምቶ እንደወትሮው እንዲቀመጥ ይሁን፡፡ ደግሞ በተረፈ ቀኝ አዝማች ተገኝን አስታርቅ ብየዋለሁና እሱ ያስታርቅ፡፡
ሰኔ 20 ቀን 1899 ዓ.ም አዲስ አበባ ተፃፈ
9/ ይድረስ ከደጃዝማች ይልማ
ሐረርጌ ራስ መኮንን አሠርቶት የነበረውን የበሽተኛ ማስታመሚያ ሆስቢታል ቤት የፈረንሳይ መንግስት ሐኪም አስመጥቶ ያገራችንን ሕመምተኛ ሊያስታምምልን በኢትዮጽያ ልዩ መልክተኛና ባለሙሉ ስልጣን ሚኒስትር ውሌ እሎቢኮብስኪ ስለፈረንሳይ መንግስት ሪፐብሊክ ሆኖ ገዝቶታልና ይህንኑ የሆስቢታሉን ቤት የቦታውን ልኩንና መጠኑን ለክተህ የመሄጃውንም ወረቀት አፅፈህ ለሐረርጌ ለፈረንሳይ መንግስት ቆንሲል ለሙሴ ናጀር እንድትረካከብ ይሁን፡፡
ነሐሴ ቀን 1899 ዓ.ም አዲስ አበባ ተፃፈ
10/ ይድረስ ከአፈ ንጉሥ ነሲቡ
የኢትዮጵያ መንግስት የፍርድ ሚኒስትር
ሜርታት የሚባል የአርመን ሰው ከሱናፊ ጋር በገንዘብ ተጣልቼ ሳልተሳሰብ ክፈል አሉኝ ብሏልና እንደነጋዴ ስርዓት በፊት እነነጋድረስ ኃይለጊዮርጊስ ላይ እንድተሳሰብ ይሁን፡፡ ነገሩ እዚያ የላለቀላቸው እንደሆነ ግን በኋላ አንተው ዘንድ ይጨርሳሉ፡፡
መጋቢት 29 ቀን 1900 ዓ.ም አዲስ አበበ ከተማ ተፃፈ

 

67 ዓመት የሞላው የግርማዊነታቸው የ‹ሊግ ኦፍ ኔሽን› ንግግር


67 ዓመት የሞላው የግርማዊነታቸው የ‹ሊግ ኦፍ ኔሽን› ንግግር
ክቡር ፐሬዝዳንት
ክቡራን የመንግስታት መልዕክተኞች
በፈረንሳይ ቋንቋ ብነግራችሁ እወድ ነበር፡፡ ነገር ግን ሃሳቤን በመንፈሴ ኃይል ሁሉ ከልቤ ለመናገር የሚቻለኝ በአማርኛ ቋንቋ ስለሆነ፣ በፈረንሳይ ቋንቋ በመናገሬ የመንግስታት ማኅበር ዋና ጉባኤ ይቅርታ እንዲያደርግልኝ እለምናለሁ፡፡
እኔ ቀዳማዊ ኃይሌ ሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት፣
የዛሬ  ስምንት ወር ሃምሳ ሁለት መንግስታት የዓለምን መነግስታት ሕግ የተላለፈ የአጥቂነት ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ መደረጉን አረጋግጠው ካስታወቁ በኋላ ለሕዝቤ ይደረግለታል ብለው ቃል የገቡለትን እርዳታና የሚገባውንም ትክክለኛ ፍርድ ለመጠየቅ ዛሬ ከዚህ ቀርቤአለሁ፡፡
ለእነዚህም ለአምሳ ሁለት መንግስታት የኢትዮጵያን ሕዝብ አቤቱታ ለማቅረብ ከንጉሠ ነገስቱ የሚበልጥ ሌላ ሰው አይገኝም፡፡በዚህ ጉባኤ ያንድ መንግስት ንጉሠ ነገሥት ወይም ፐሬዝዳንት ቀርቦ ሲናገር ምናልባት ገና ዛሬ መጀመሩ ነው፡፡ ደግሞ ያንድ አገር ሕዝብ ይህን የመሰለ ሕግ ሲሰራበትና አሁንም በአጥቂው እጅ ለመውደቅ ሲደርስ የታየው በእርግጥ ዛሬ ብቻ ነው፡፡
ደግሞ አንዱ መንግስት የሌላውን መንግስት አገር በጦርነት እንዳይወስድበትና ንፁሐን የሆኑትንም የሰው ወገኖች ኃይለኛ በሆነ በጋዝ ቶክሲክ መርዝ እንዳይፈጃቸው ተብሎ በዓለም ካሉ መንግስቶች ጋር በተዋዋለው ውል በክብርና በግልጥ የሰጠውን ቃል ኪዳን ተላልፎ በጨካኝነት መሣሪያ ያንዱን ሕዝብ ዘር በቁርጥ ለማጥፋት ከዚህ ቀድሞ የተነሳና ምሳሌ የሆነ መንግስት አልታየም፡፡ ስለዚህ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥትነቴ ወደ ጄኔብ የመጣሁበት ምክንያት ለጦር ሠራዊቴ ዋና መሪ ሆኜ ራሴ ከተዋጋሁ በኋላ ከብዙ ሺህ ዘመናት በፊት ጀምሮ የቆየውን ነፃነቱን ለመጠበቅ ስለሚታገለው ስለ ኢትዮጵያ ሕዝብ ለመከላከልና ይህንም ከፍ ያለ የተገባኝን ስራ ለመፈፀም ነው፡፡ እነዚህም የተከተሉኝ ሹማምንቶች ራሳቸው ከደረሰባቸውና ምስክር ከሆኑት ከሚያሰቅቅ ነገር በሕዝቤም ላይ ከተደረገው ስቃይ የዓለምን መንግስታት እግዚአብሔር እንዲጠብቃቸው እለምናለሁ፡፡
በጄኔብ የተሰበሰቡትና ለብዙ ሚሊዮን ሰዎች ሴቶችና ሕፃናት ሕይወት አላፊ ለሆኑት መንግስታት እንደራሴዎች በእነዚህ ፍጥረቶች የደረሰባቸውን የሞት አደጋ በኢትዮጵያ ላይ የደረሰባትን እድል በዝርዝር አስረዳለሁ፡፡የኢጣልያ መንግስት ጦርነት ያደረገው በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ብቻ አይደለም፡፡ ይልቁንም ከጦርነቱ ስፍራ በራቁት በሠላማዊ ሕዝብ ላይ በድንጋጤ ለመግደልና ዘራቸውንም ለማጥፋት አደጋ እየጣለ ወጋቸው፡፡ጦርነቱ እንደ ተጀመረ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1928 ዓ.ም በኢጣልያ አይሮፕላኖች በጦር ሠራዊቶቼ ላይ ጋዝ ላክሪሞዤን ያለበት ቦምብ ጣሉባቸው፡፡ ይህም ቦምብ እጅግ አልጎዳቸውም ነበር፡፡ ምክንያቱም ወታደሮቹ ቦምብ በወደቀ ጊዜ ጋዙን ነፋስ እስኪወስደው ድረስ መበታተኑን ስለ ዐወቁበት ነው፡፡
ከዚህ በኋላ የኢጣልያ አይሮፕላኖች ኤፒሪት የተባለውን ጋዝ መጣል ጀመሩ፡፡ በኢትዮጵያ የጦር ሠራዊት ላይ ኤፒሪት ያለበት በርሜል ወደቀባቸው፣ ይኸውም ሆኖ የኤፒሪቱ ጋዝ ያደረገው ጉዳት የለም፡፡ ምክንያቱም የኤፒሪቱ ውሃ የሚያገኛቸው ወታደሮች ጥቂቶች ስለነበሩና በርሜሉ በመሬት ላይ ሲወድቅ ወታደሮቹ ሕዝቡም መርዝ ያለበት መሆኑን ስለዐወቁት ነው፡፡ የኢጣልያ የጦር ጠቅላይ ሹም መቀሌ የኢትዮጵያ ወታደሮች በከበቡ ጊዜ የኢጣልያ የጦር ሠራዊት መፈታቱን ስለ ተረዳውና ስለ ሠጋ ሌላ አይነት የኤፒሪት አጣጣል አደረገ፡፡ ይህንም አደራረግ አሁን ለዓለም ገልጦ ማስታወቅ የተገባኝ ነው፡፡
በአይሮፕላኖቹ ላይ የኤፒሪቱን ውሃ የሚረጭ መኪና ተዘጋጅቶ ሰፊ በሆነው አገር ላይ ሞትን የሚያመጣ ረቂቅ ዝናብ እንዲወርድበት ተደረገ፡፡ የኢጣልያም አይሮፕላኖች አንድ ጊዜ 9፣ 15፣ 18 እየሆኑና እየተመላለሱ የኤፒሪት ዝናብ ሳያቋርጥ እንዲወርድ አደረጉ፡፡ በጥር መጨረሻ 1928 ዓ.ም ጀምሮ በወታደሮቻችን፣ በሴቶች በልጆች፣ በከብቶችና በፈሳሽ ወንዞች በኩሬዎችና በከብት መሰማሪያዎች ቦታዎች ላይ ሳያቋርጥ ሞት የሚያመጣ ይህ ዝናብ ዘነበባቸው፡፡ ፍጡር የሆኑትን ሁሉ በፍፁም ለማጥፋት ውሃውንና ለከብት የሚሆነውንም ሳር መረዝ ብቻ ለማድረግ የኢጣልያ የጦር ሹም አይሮፕላኖቹ ይህንኑ ስራቸውን እየተመላለሱ እንዲሰሩ አደረገ፡፡ ዋና የጦርነት መሣሪያ ያደረገው ይህንኑ ነው፡፡
ይኸም በረቂቅነት የሚሰራ የጭካኔ ስራ ጦርነት ከሚደረግበት ቦታ በራቁት ቦታዎች የሚገኙትን ሕዝብ አጠፋቸው፡፡ አገራቸውንም ምድረ በዳ አደረገው፡፡ አሳቡም በሚበዛው በኢትዮጵያ ግዛት ክልል ላይ ድንጋጤንና ሞትን ለመዝራት ነበር፡፡እጅግ የሚያሳዝን ነገር የሚያመጣ ይህ ብልሃት ተፈፀመበት፡፡ ሰው ከብቱም በፈፁም አለቀ፡፡ ከአይሮፕላንም የሚወርደው የሞት ዝናብ የሚነካውን ሁሉ እያሰቃየ ያባርር ነበር፡፡ ይህም የመርዝ ዝናብ የዘነበበትን ውሃ የሚጠጡ መርዙም የሚነካውን ምግብ የሚመገቡ በታላቅ ስቃይ አለቁ፡፡ በኢጣልያ ኤፒሪት ምክንያት በብዙ ሺህ የሚገመቱ ሰዎች ሞቱ፡፡ እኔም ወደ ጄኔብ ለመምጣት የቆረጥሁት የኢትዮጵያ ሕዝብ የደረሰበትን ስቃይ ለሰለጠነው ዓለም ለማስታወቅ ነው፡፡
ይህንንም የማያከራክር ምስክርነት ከእኔና ከነዚህ ከተከተሉኝ በጦርነቱ ላይ ከነበሩት ሰዎች የተሻለ ለመንግስታት ማኅበር የሚያስረዳ አይገኝም፡፡አውሮጳም ይህን ነገር እንዳለቀ አድርጎ ቢቆጥረው በራሱ የሚደርስበትን የሚጠብቀውን ይህን እድል ማሰብ ይገባዋል፡፡ይህ ሁሉ መከራ በጦር ሠራዊቴና በሕዝቤ ላይ ሲወርድበት መላክተኞቼ መንግስታት ማኅበር የሚያቀርቡት አቤቱታ ምላሽ ሳያገኝ ቀረ፡፡ መላክተኞቼም በጦርነቱ ውስጥ አልነበሩምና በኢትዮጵያ ላይ የደረሰውን መከራ እነሱ ያላዩት ስለ ሆኑ በሕዝቤ ላይ የተፈፀመበትን የወንጀል ስራ ለማስረዳት ራሴ ለመምጣት ቆረጥሁ፡፡በኢትዮጵያ ላይ በየጊዜው የደረሰውን ዛሬ ለተሰበሰው ለመንግስታት ማኅበር ዋና ጉባኤ ማሳሰብ የሚያስፈልግ አይደለምን?
ከሃያ ዓመት በፊት ጀምሮ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገስት መንግስት አልጋ ወራሽና እንደራሴ ሆኜ በኋም ንጉሠ ነገሥት ተብዬ የሕዝቤ መሪ ሆኜ ስሰራ ላገሬ ያዲሱ ሥልጣኔ ጥቅም እንዲደርሰው በተለይም ጎረቤት ከሆኑት መንግስቶች መልካም የጉርብትና መገናኛ ለማቆም መድከሜን አላቋረጥሁም፡፡ በተለይም ከኢጣልያ መንግስት ጋር በማናቸውም ምክንያት ቢሆን ጦርነት እንዳይነሳ የሚከለክል በሁለቱ መነግስቶች መካከል የሚነሳው ክርክር በወዳጅነትና በሽምግልና ዳኞች እንዲጨረስ የሚያደርግ የሰለጠኑት ዓለም መንግሥታት ለሕዝብ ሰላም እንዲሆን መሠረት ያደረጉትን የወዳጅነት ውል በ1920 ዓ.ም ተዋዋልሁ፡፡የአስራ ሶስቱ መንግስታት ጉባኤ በመስከረም 26 ቀን 1928 ዓ.ም ባቀረበው ማስታወቂያ የደከምሁበትን ሥራ አውቆ በግልጥ ተናግሮልኛል፡፡የተናገረውም ይህ ቃል ነው፡፡
‹ኢትዮጵያ ወደ መንግስታት ማኅበር በመግባትዋ ግዛትዋ እንዳይነካባትና ነፃነትዋ እንዳይጠፋ አዲስ መተማመኛ በመስጠት አሁን ካለችበት የሥልጣኔ ደረጃ ከፍ ወዳለው እንድትደርስ መንግስታት አስበው ነበር፡፡ አሁን ባላቸው በኢትዮጵያ ውስጥ በ1915 ዓ.ም ይታይ የነበረው የፀጥታ ማጣትና የሽብር ኑሮ አይታይባትም፡፡ ይልቁንም አገሩ ከፍተኛው ይበልጥ አንድ ሆኗል፡፡ የዋናውም መንግስት ሥልጣን ከቀድሞው ይበልጥ ይከበራል› ይላል፡፡ ይህንም የወዳጅነት ውል የፈረመው አሳቡን ለመሸፈኛ እንዲያገለግለው ኖርዋል፡፡የኢጣልያ መንግስት በኢትዮጵያ ሽብር ለማንሳት አንዳንድ ሰው በመግፋት፣ ለዐመፀኞችም መሣሪያ በመስጠት ይህንም የመሰለ ብዙ አይነት ችግር ባያደርግብኝ ለሕዝቤ የሠራሁት ሥራ ከዚህ የበለጠ ፍሬ አፍርቶ ይጠቅም ነበር፡፡የሮማ መንግሥት ዛሬ በግልጥ ማድረግ እችላለሁ ብሎ የተነሳበትን ኢትዮጽያን በጦርነት ለመውሰድ ያሰበውን አሳብ ባለማቋረጥ ሲያዘጋጅ ኖረ:: እንዲሁም ከእኔ ጋር የፈረመው ውል ሁሉ ከልቡ አልነበረም፡፡ ይህንንም የወዳጅነት ውል የፈረመው ሃሳቡን ለመሸፈኛ እንዲያገለግለው ኖሯል፡፡
የኢጣልያ መንግስት ዛሬ በጉልበት ያገኘውን ለመስራት ከ14 ዓመት ጀምሮ መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ ስለዚህ በ1915 ዓ.ም ኢትዮጵያ በመንግስታት ማኅበር እንድትገባ በነገሩ መደገፍና መረዳቱ በ1920 ዓ.ም የወዳጅነት ውል መዋዋሉ ጦርነት ከሕግ የወጣ ነገር ለመሆኑ በፓሪስ ላይ የተደረገውን ውል መፈረሙ የዓለምን እምነት የሚጎዳ ስራ ለመስራት ነው ማለት ይቻላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን በዚህ ታላቅ ክብር በተደረገው ውል ሁሉ የታየው የነበረው በሰላም መንገድ ላይ ሆኖ ሀገሩን ወደ ስልጣኔ ለመምራት በሙሉ ልቡና በሙሉ ኃይሉ ለመስራት የጀመረውን ስራ ለመፈፀም እንዲቻለው እንደገና መተማመኛ የሚሆነው ነገር ማግኘቱ መስሎት ነበር፡፡
በህዳር ወር በ1927 ዓ.ም የተደረገው የወልወል ጠብ ለእኔ በድንገት ከሰማይ እንደወረደ መብረቅ ቁጣ ሆኖ ተሰማኝ፡፡ ኢጣልያ ጠብ እንዲነሳ መፈለጓ ግልፅ ነበር፡፡ እኔም ይህንኑ ለመንግስታት ማኅበር ማሰማቴን አልተኹም፡፡ ስለዚህ በ1920 ዓ.ም በተደረገው ውል በተፃፈው ቃል የመንግስታት ማኅበር በቆመበት መሠረት በሽማግሌ ዳኝነት በዚሁ መንገድ ነገሩ እንዲታይ ጠየቅሁ፡፡
ይኸውም በመጀመሪያ ጊዜ የተደረገው የመንግስታት ማኅበር ውል መሻር አንድ ጊዜ ብቻ ሆኖ አልቀረም፡፡ የሮማ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ፖለቲካ የሚያበረታታለት ስለሆነ በኢትዮጵያ ላይ በመጫን የተጀመረው ስራ የኢትዮጵያ ሕዝብ የኢጣልያን ገዢነት እንዲቀበል ለማድረግ የማይበቃ የሆነ እንደሆነ በጦርነት አደርጋለሁ ብሎ ይዘጋጅ ጀመር፡፡ ለዚህም ጊዜ ማግኘት የሚያስፈልግ ሆነበት፡፡ ለእርቅ የተመረጡት የሽምግልና ዳኞች ስራቸውን ለመጀመር እንዳይችሉ በብዙ አይነት ተንኮል እየተደረገ በልዩ ልዩ ረገድ ነገሩ እንዲጎተት ሆነ፡፡ ይኸውም የሽምግልና ዳኞች ስራ እንዳይፈፀም ብዙ አይነት መሰናክል ተደረገበት፡፡ አንዳንዶቹ መንግስቶች ለዚሁ ለሽምግልና ዳኝነት የሚሆን ሰው ከዜጎቻቸው ውስጥ እንዳይመረጥ ለመከልከል ፈለጉ፡፡ የሽምግልናውን ዳኝነት ስራ ከተቋቋመ በኋላ ነገሩ ለኢጣልያ በመልካም መንገድ እንዲፈረድ ዳኞቹ ተጭነዋቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ይህ ሁሉ በከንቱ ተደከመበት፡፡ ሁለት የኢጣልያ ሰዎች የነበሩትን የሽምግልና ዳኞች በአንድ ቃል ሆነው በወልውልም ነገር ቢሆን ከዚያም በኋላ በተደረገ ነገር ቢሆን ኢትዮጵያን በአለም መንግስታት ፊት ኃላፊ የሚያደርጋት ነገር የለም ብለው ፈረጁ፡፡ይህም ፍርድ ከተፈረደ በኋላ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኢጣልያ ጋር አዲስ የወዳጅነት ዘመን ይጀምራል በማለት በእርግጥ ተማምኖ ነበር፡፡ለሮማም መንግስት በእውነተኛ መንገድ ለማግኘት እጄን ዘረጋሁ፡፡
ከህዳር ወር በ1926 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 23 ቀን በ1928 ዓ.ም በየጊዜያቱ የሆነውን ነገር ሁሉ በዝርዝሩ በመስከረም 25 ቀን 1928 ዓ.ም የተሰበሰቡ የ13 መንግሥቶች ኮሚቴ ባደረገው ራፖር ለዋናው ማኅበር ጉባኤ አስታወቀ፡፡በዚሁም ራፖር ከተፃፈው የተቆረጠው ነገር በቁጥር 24፣ 25 እና 26 ብቻ የተፃፈው ቃል አሁን አስታውሳለሁ፡፡
የኢጣልያ ማስታወሻ ለምክሩ ጉባኤ የተሰጠው በነሐሴ 29 ቀን በ1928 ዓ.ም ነው፡፡ የኢትዮጵያ ማስታወሻ የተሰጠው ግን የመጀመሪያው አቤቱታ በታህሳስ 5 ቀን በ1926 ዓ.ም ነው፡፡ በእነዚህ ሁለት ጊዜያቶች መካከል የኢጣልያ መንግስት ነገሩ በምክሩ ጉባኤ ፊት ቀርቦ እንዳይታይ ሲል በ1920 ዓ.ም በኢትዮጵያና በኢጣልያን መካከል በተደረገው ውል በተፃፈው ቃል ብቻ ነገሩ ይፈፀማል እያለ እንዲቆይ አደረገ፡፡ በዚህም ጊዜ ሁሉ በምስራቅ አፍሪቃ የኢጣልያ ወታደር እየተከታተለ ይላክ ነበር፡፡ የኢጣልያ መንግስት ወታደር የላከበት ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት ለጦርነት የሚዘጋጅ በመሆኑ ለቅኝ አገሩ የሚያሰጋው ስለሆነ ለመከላከል የሚያስፈልገው በመሆኑ ነው ብሎ ነገሩን ለምክሩ ጉባኤ ምስጢሩን ሰውሮ አመለከተ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ግን ይልቁንም በኢጣልያ አገር በኦፊሲዬል በተነገረው የዲስኩር ቃል እንደሚታየው የኢጣልያ መንግስት ለጠብ ማሰቡ ምንም የማያጠራጥር ነው ሲል በየጊዜያቱ አስታወሰ፡፡
ጠቡ ከተነሳ ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት ነገሩን በሰላም ለመጨረስ ፈለገ፡፡ በመንግስታት ማኅበር ውል በተፃፈው ቃል ነገሩ እንዲታይ ጠየቀ፡፡ የኢጣልያ መንግስት ግን በ1920 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኢጣልያ መካከል በተደረገው ውል ቃል ብቻ ነገሩ እንዲታይ ስለፈቀደ የኢትዮጵያ መንግስት ይህንኑ ተቀበለ፡፡ የሽምግልና ዳኞች ነገሩን በመልካም ሳይፈርዱለት ቢቀሩ እንኳ ፍርዱን በመልካም ፈቃድ እፈፅማሁ ብሎ አስታወቀ፡፡ የሽምግልና ዳኞቹ ወልወል የማን ግዛት እንደሆነ ነገሩን እንዲያዩ ኢጣልያ ሳትፈቅድ ስለቀረች ኢትዮጵያ ይሄንንም ተቀበለች፡፡ ይሄንም ነገሩ የሚመረምሩ ነፃ የሆኑ ሰዎች በአገሩ እንዲላኩ የምክር ጉባኤ ጠየቀ፡፡የምክሩ ጉባኤ በፈቀደው አይነት የቆረጠውን ምርመራ ለመቀበል የተዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ፡፡ የኢጣልያ መንግስት በበኩሉ የወልወል ነገሩ በሽማግሌዎች ታይቶ ከላቀ በኋላ የፈቀደውን ስራ ለመስራት እንዲችል ነፃነቱን ለመጠየቅ የማመልከቻውን ዝርዝር ለምክሩ ጉባኤ አቀረበ፡፡
ኢትዮጵያ ጋር ያለውን ነገር ሁሉ ለመጨረስ በማኅበሩ ውል የተፃፈውን ቃል ለማስፈፀም ብቻ የሚበጅ ነገር የለበትም ብሎ አስረገጠ፡፡ ደግሞ ለኢጣልያ ይሄ ነገር ዋና የሕይወት ጥቅም ያለበት ስለሆነና ራሱን ለመጠበቅ ዋና መጀመሪያ የሚያስፈልገው ስለሆነ ተስፋውን በጭራሽ በኢትዮጵያ ላይ ካላነሳና የራሱን ጥቅምና ቅኝ አገሩን ለመጠበቅ የሚያስፈልገውን ለማድረግ ሙሉ ነፃነት ካላገኘ በቀር ኢጣልያ ከሁሉ ያነሰ መጀመሪያ ማድረግ የሚገባውን ስራ ማጉደል ይሆንበታል ብሎ አደላድሎ አስታወቀ፡፡
የ13ቱ መንግስታት ምክር ቤት ያቀረበው ራፖር ቃል ይህ ነው፡፡ የምክሩና ዋናውም የማኅበሩ ጉባኤ በአንድነት ሆነው ‹የኢጣልያ መንግስት የማኅበሩ ውል ቃል ማፍረሱንና አጥቂ መሆኑን› በግልጥ አስታወቀ፡፡እኔም በግድ የመጣብኝን ጦርነት ለማድረግ አለመፈለጌን በየጊዜው ከማስታወቅ አላቋረጥሁም፡፡ የምዋጋውም የሕዝቤ ነፃነቱና የኢትየጵያም ሙሉ ግዛት እንዳይነካባቸው በማለት ብቻ መሆኑና በዚሁም ጦርነት የምከላከለው የታላቅ መንግስቶች ጎረቤት የሆኑ ትንንሽ መነግስቶች ሁሉ በኃይል አገራቸውን ለመውሰድ እንዳይችል የነርሱን ጉዳይ ጭምር ነው፡፡በ1928 ዓ.ም በጥቅምት ወር ዛሬ የሚሰሙኝ 52ቱ መንግስቶች ‹አጥቂው አያሸንፍም የሕግ መንግስት እንዲኖርና እንዲፀና ከሕግ ተላልፎ በኃይል የሚሰራ ስራ እንዲፈርስ በማኅበሩ ውል የተፃፈው ቃል ሁሉ እንዲፈፀም እናደርጋለን› ብለው ቃል ሰጥተውኝ ነበር፡፡በዓለም ሁሉ አጥቂነቱ ከተፈረደበት መንግስት ሕዝቤ እንዲከላከል ያደረግሁት እምነቴን የገለጥሁት የዛሬ ስምንት ወር 52ቱ መንግስቶች የተከተሉትን ፖለቲካ እኔም ተከትዬ ነውና ይህንኑ ፖለቲካቸውን እንዳይዘነጉት አሳስባለሁ፡፡
ምንም የጦር መሣሪያዬ ከአጥቂው ያነሰ ቢሆን አይሮፕላን መድፍ ሌላም መሣሪያ የቁስለኛ ማሳከሚያ በጭራሽ ባይኖረኝ ተስፋዬ በመንግስታት ማኅበር ውል ላይ ነበር፡፡ 52ቱ መንግስቶች ከነዚሁም በዓለም የበለጡ ያሉባቸው በአንድ አጥቂ በሆነ መንግስት ብቻ ሊሸነፉ የማይቻል ነው ብዬ አስብ ነበር፡፡ በውል ኃይል ተማምኜ በአውሮጳ አንዳንድ ትንንሽ መንግስቶች እንደደረሰበቸው ሁሉ ለጦርነት አልተዘጋጀሁም ነበር፡፡ አደጋው የሚያጣድፍ በሆነ ጊዜና በሕዝቤም ፊት ያለብኝ ኃላፊነት ህሊናዬን የሚነካ ስለሆነ በ1928 ዓ.ም መሣሪያ ለማግኘት ሞከርኩ፡፡ ብዙ መንግስቶችም እኔን ለመከላከል ሲሉ መሣሪያ ከአገር እንዳይወጣ ከለከሉ፡፡ የኢጣልያ መንግስት ግን በካናል ስዊዝ በኩል መሣሪያና ጥይት ወታደርም ሳያቋርጥና ማንም ሳይከለክለው ለማስተላለፍ ችሎ ነበር፡፡ በመስከረም 23 ቀን የኢጣልያ ወታደር ግዛቴን ለማስተላለፍ ችሎ ነበር፡፡ በመስከረም 23 ቀን የኢጣልያ ወታደር ግዛቴን አገሬን ወረረው፡፡ ከጥቂት ሰዓት በኋላ ብቻ ወታደር እንዲሰበሰብ የክተት ዐዋጅ አደረግሁ፡፡ ሰላምን ጠብቆ ለመኖር በመፈለግ አሳብ በታላቁ ጦርነት ጊዜ ጦርነቱ ሊደርስ አቅራቢያ አንድ ታላቅ መንግስት እንዳደረገው ሁሉ በማናቸውም ምክንያት እንዳደረገው ሁሉ በማንኛውም ምክንያት ጠብ ፈላጊነት እንዳይነሳ በማለት ወታደሮቼ ሰላሳ ኪሎ ሜትር ያህል ወደ ኋላ እንዲመለሱ አደረግሁ፡፡ ከዚያም በኋላ ጦርነቱ ለምክሩ ጉባኤ እንዳመለከትኩት ሁሉ በታላቅ ግፍ ይቀጥላል፡፡
በዚህ በማይወዳደር ጦርነት 42 ሚሊዮን ሕዝብ የሚገዛው የሚያስፈልገውንም መሣሪያና ገንዘብ ለማግኘት የሚችል የሰው ሕይወት ለማጥፋት በያይነቱ የሆነ መሳሪያ ለመስራት የቴክኒክ ጥበብ ሁሉ ያለው መንግስት ያለመሳሪያ ያለገንዘብ ትክክል ፍርድንና የነገስታትን ማኅበር ቃል ብቻ ተማምኖ ከተቀመጠው ትንሽ ከሆነው ከ12 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር በተደረገው በዚህ በማይወዳደር ጦርነት የሮማ መንግስት የማኅበሩን ውል አፍርሷል ተብሎ ከተፈረደና አጥቂውም እንዳያሸንፍ እንከላከላለን ከተባለ በኋላ በኢትዮጵያ መንግስት የተደረገው ያገኘውም እርዳታ እንደሌለ እናንተ ልትገምቱት ትችላላችሁ፡፡በማኅበሩ ያለው አንዳንድ መንግስት ሁሉ በማኅበሩ ውል በ17ኛው ክፍል ተፅፎ የፈረመው ፊርማ እንደሚያዘው ሁሉ አጥቂው ያደረገው ጦርነት በእያንዳንዱ ማኅበርተኛ ላይ በራሱ እንደተደረገበት ሁሉ ቆጥሮት የለምን?
ይህ ውል የተገባበት ቃል ይፈፀማል ብዬ ሙሉ ተስፋዬን በእሱ ላይ አድርጌ ነበር፡፡ ተስፋዬም ደግሞ አጥቂው ዋጋ አያገኝም ኃይልም በሕግ ፊት እንዲሸነፍ ይደረጋል ተብሎ በማኅበሩ ጉባኤ የተነገረው ቃል የሚያደላድል ተስፋ አግኝቶ ነበር፡፡በታህሳስ ወር 1928 ዓ.ም ኢትዮጽያ እንድትከፋፈል ተብሎ የቀረበውን ድርድር በዓለም ሁሉ ያለው ብዙ መቶ ሚሊዮን የሚሆን ሰው አስታውቆ ነበር፡፡ ብዙም ጊዜ ‹ይህ የተነሳው ጠብ የኢትዮጵያና የኢጣልያ መንግስት የመንግስታት ማኅበር ጠብ ነው› ተብሎ ተነግሮ ነበር፡፡እኔም ራሴ ሕዝቤም የመንግስታት ማኅበርን ውል የሚያስወግድ ለራሴ አቅም የሚሆን የቀረቡኝን ድርድር ሁሉ አልቀበልም ብዬ መመለሴ ስለዚህ ነበር፡፡ እኔም የተከላከልሁት ለጥቃት የሚያሰጋውን የትንንሾች መንግስቶች ጉዳይ ጨምሬ ነበር፡፡  እናደርግልሃለን የተሰጡኝ ቃሎች ሁሉ ወዴት ደረሱ?
ከታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም ጀምሮ ሶስት መንግስቶች በማኅበሩ ውል የገቡበትን ግዴታ ዋጋ እንደሌለው ሁሉ አድርገው በማየታቸው በታላቅ ሃዘን ተመከትሁ፡፡ ከኢጣልያ ጋራ ያላቸው አገባብ ኢጣልያ በአጥቂነት ያደረገችውን ስራ ለማቆም ማናቸውንም ነገር እንዳይቀበሉ አደረጋቸው፡፡ይልቁንም ደግሞ ለእኔ የተስፋዬን አሳብ የቆረጠብኝ ያንዳንዳቹ መንግስቶች ስራ ነው፡፡ እነዚሁም መንግስቶች በመንግስታት ማኅበር ላይ ያላቸውን እምነት ሳያቋርጡ እየተናገሩ የመንግስታት ማኅበር ሕግ እንዳይፈፀም ደግሞ ሳያቋርጡ ይደክማሉ፡፡ አንዳንድ መንግስቶች የአጥቂውን ስራ በቶሎ የሚያስቀር ደህና ነገር በቀረበ ጊዜ እንኳንስ ነገሩ እንዲፈፀምና ነገሩ ለክርክር እንዳይቀርብ በብዙ ምክንያት ያቆዩታል፡፡ በጥር ወር 1928 ዓ.ም የተደረገው የምስጢር ውል ይህን የመሰናክል ስራ አስቀድሞ ያመለከተ ኖሯልን?
የኢትዮጵያ መንግስት በቀጥታ ጥቅማቸው ያልተነካባቸው ሌሎች መንግስቶች የመንግስታትን ማኅበር ውል ለመከላከል የወታደሮቻቸውን ደም ያፈሰሱ ብሎ አልጠበቀም፡፡ የኢትዮጵያ ጦረኞች ጠይቀው የነበሩት ለመከላከል የሚሆናቸውን ነገር ብቻ ነበር፡፡ ስለዚህም ብዙ ጊዜ መሣሪያ ለመግዣ የሚሆን ገንዘብ ለማግኘት ጠይቄ ነበር፡፡ ይህንም እርዳታ ተከለከልሁ፡፡ በመንግስታት ማኅበር ውል በ16ኛው ክፍል የተፃፈው ቃልና መንግስቶች እየተባበሩ በመረዳት ፀጥታ እንዳይጠፋ ያደርጋሉ የተባለው የአፈፃፀሙ ትርጓሜ ምን ይሆን?
ከጅቡቲ እስከ አዲስ አበባ ያለው የምድር ባቡር ለኢትየጽያ የሚሆን መሳሪያ እንዲተላለፍበትና ለኢትዮጵያ መንግስት እንዲያገለግል በተጠየቀ ጊዜ መሣሪያው በዚያ በኩል እንዳይገባ ብዙ ችግር ተደረገ፡፡ ላሁኑ ሰዓት ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ያላገባብ ለገባው ለኢጣልያ ሠራዊት ዋግ የሥንቅና የመሣሪያ ማመላለሻ ሆኗል፡፡ የገለልተኝነት (የኑትራሊቴ) ደንብ እንኳ የኢጣልያ ወታደሮች እስካሉበት ድረስ ይህን የመሰለው ነገር እንዳይጫን ይከለክላል፡፡ ይህ ከሆነ የመንግስታት ማኅበር ውል በ16ኛው ክፍል በተፃፈው ቃል ማኅበርተኞች የሆኑት መንግስቶች ሁሉ አንድ መንግስት ሌላውን በአጥቂነት የወጋው እንደሆነ ሌሎች ገለልተኛ መሆናቸው ቀርቶ መርዳት የሚገባቸው  ለአጥቂው ሳይሆን ለተጠቂው ስለ ሆነ የነትራሊቴ ደንብ እዚህ መነሳት አይገባውም፡፡ በዚህ አኳኋን የመንግስታት ማኅበር ውል ከዚህ ቀድሞ ተጠብቋልን? ዛሬም እንደ ተጠበቀ ነው ለማለት ይቻላልን?
አሁን በመጨረሻው በመንግስታት ማኅበር ታላቅ አገባብ ያላቸው ታላቅ መንግስቶች በምክር ቤታቸው አጥቂው የኢጣልያ መንግስት ታላላቅ መንግስቶች በምክር ቤታቸው አጥቂው የኢጣልያ መንግስት የኢትዮጵያን መሬት አንዱን ክፍል ከያዘ በገንዘብ ጥቅም ረገድ ይህ እንዳይሆን ያቆምነውን መከላከያ መቀጠል አያስፈልግም ብለው አስታወቁ፡፡በአርጀንቲና መንግስት ጠያቂ በአጠቂው በኢጣልያ ምክንያት የሆነውን ነገር ለመመርመር የተሰበሰበው የመንግስታት ማኅበር ዋና ጉባኤ ዛሬ በፊቱ የሚገኘው አኳኋን ይህ ነው፡፡
ዛሬ የመንግስታት ማኅበር ዋና ጉባኤ በፊቱ ያለው ጉዳይ ኢጣልያ በአጥቂነት የሰራችውን ለመጨረስ ብቻ አይደለም፡፡ በሙሉ የዓለምን መንግስታት የሚነካ መሆኑን አረጋግጬ አስታውቃለሁ፡፡ ይህም ጉዳይ ለዓለም ፀጥታ እንዲሆን መንግስታት ለመረዳዳት የሚገባቸው የጋራ ፀጥታ (ሴኩሪቲ ኮሌክቲቭ) የተባለው የመንግስታት ማኅበር ሕይወተ የዓለም መንግስቶች ለተዋዋሉት ውል መሰጠት የሚገባቸው እምነት ትንንሾቹም መንግስቶች አገራቸውና ነፃነታቸው እንዳይነካ የተቀበሉት ቃል ኪዳን የሚከበርበትና ዋጋው የሚገመትበት የመንግስቶች ትክክለኛነት የተመሠረተበት መሠረት ይህን ለማፅናት ወይም ትንንሾች መንግስቶች የኃይለኞች መንግስቶች ተገዥ ለመሆን መቀበል ይገባቸው እንደሆነ ለመፍረድ ነው፡፡ በአጭር ቃል የተነካውና የተበደለው የዓለም ሕዝብ የተገባ አነዋወር ነው እንጂ ኢትዮጵያ ብቻ አይደችም፡፡ በአንድ ውል ላይ የተፈረሙ ፊርማዎች ዋጋቸውን የሚያገኙ አንዱ በሌላው ላይ የግል ጥቅሙን በቀጥታና በፍጥነት ለማግኘት ለመፈፀም እንዲችል እንዲረዱት ሲሆኑ ነውን?
በረቂቅ መንገድ መበላለጥ ዋናውን ነገር ሊለውጠው ወይም የክርክሩን መንገድ በሌላ በኩል ሊመራው አይገባም፡፡ ይህንም ማመልከቻ ለመንግስታት ማኅበር ዋና ጉባኤ የማቀርበው በእውነተኛነት ከልቤ ነው፡፡ከእግዚአብሔር መንግስት በስተቀር የፍጡር መንግስት ሁሉ አንዱ ካንዱ የሚያበላልጥ ስራ የለውም፡፡ ነገርግን በምድር ላይ ኃይለኛ የሆነው የሚገባው መስሎት የተነሳበት ጊዜ፣ ተጠቂው ወገን ለመንግስታት ማኅበር የተበደለውን የሚያቀርብበት ሰዓት ነው፡፡ እግዚአብሔርና ታሪክ ለምትሰጡት ፍርድ ምስክር ሆነው ይመለከታሉ፡፡
ሕዝቤ ዘሩ ሊጠፋ በደረሰበት የመንግስታት ማኅበርም እርዳታ ከጥፋት ለማዳን በሚችልበት ጊዜ ማናቸውንም ሳላስቀርና ሳላቆይ በተዘዋሪ ቃል ሳይሆን አውነቱን አውጥቼ እንድናገር ሊፈቀድልኝ የተገባ ነው፡፡ከዚህ ቀደም የተደረገው ሳይበቃ የቀረው ሳንክሲዮን የታሰበውን ፍሬ አላፈራም ተብሎ በማረጋገጥ ቃል ሲነገር እሰማለሁ፡፡ በማናቸውም ጊዜ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን በፈቃድ እንደማይበቃ የተደረገና ደግሞ አፈፃፀሙ እንደሚገባ ስለሆነ ሳንክሲዮን አጥቂውን ለማቆም እንደማይችል የታወቀ ነው፡፡ አጥቂውን ሳናቆመው ቀረን ያሰኛል እንጂ የማይቻል ስለሆነ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያ የገንዘብ እርዳታ እንዲደረግላት ከዚህቀደም ጠየቀች፡፡ አሁንም ትጠይቃለች፡፡ ይህስ ሊፈፀም የማይቻል ነውን?
የመንግስታት ማኅበር ግን በሰላም ጊዜ እንኳ በአጠቂው ላይ ሳንክሲዮን አናደርግበትም ላሉ ለሌሎች መንግስቶች በገንዘብ እርዳታ አድርጎላቸው ነበር፡፡ የኢጣልያ መንግስት የጨካኝነት መሣሪያ እንደያገለግለው በማድረጉ ብዙ ጊዜ እየደጋገመ የዓለምን መንግስታት ሕግ ሁሉ በመተላለፍ ምክንያት ዛሬ ሳንክሲዮን ይነሳለት የሚል አሳብ መታሰቡን ልቤ እጅግ እያዘነ ተመለከትሁ፡፡ ይህስ አደራረግና አሳብ ኢትዮጵያን አጥቂው መንግስት የፈቀደውን ይፈፅምባት ብሎ መተው አይደለምን? በመንግስታት ማኅበር ዋና ጉባኤ ፊት ለሕዝቤ በታላቅ ብርታት ለመከላከል ባቀረብሁበት ጊዜ ጥቂት ቀደም ብሎ ይህ አሳብ መታሰቡ የመንግስታት ማኅበር ማኅበርተኞች ከሆኑት መንግስቶች ኢትዮጵያ እርዳታንና መተማመኛ እንዳታገኝ አንደኛውን መጨረሻውን እድሉን የሚቆርጥባት አይደለምን? የመንግስታት ማኅበር ስራ መሪ ለመሆን ስልጣን ባላችሁ በታላላቅ መነግስቶች እርዳታ የሚገኘው የመንግስታት ማኅበርና ማኅበርተኞች በሚገባ ተስፋ አድርገው የሚጠብቁት ይህን የመሰለውን ፍፃሜ ነውን?
ኢጣልያ በአጥቂነት በሰራችው ስራ ነገሩ እዚህ ቢደርስ የመንግስታት ማኅበርተኞች የሆኑት መንግስቶች የኃይለኛውን ፈቃድ በመፈፀም ምሳሌ ለመተው ፈቃዳቸው ይሆናልን?
የመንግስታት ማኅበር ውል እንዲሻሻልና የመንግስታት መረዳዳት የሚሰጠው መተማመኛ የተፈተነ እንዲሆን ለማድረግ ተብሎ በእርግጥ ለመንግስታት ማኅበር ዋና ጉባኤ አሳብ መቅረቡ ነው፡፡ መለወጥ የሚገባው ውሉን ኖርዋልን? ውሉን የፈረሙት በሙሉ የተፃፈውን ቃል ለመጠበቅ ፈቃዳቸው ካልሆነ ውሉ ቢለወጥስ እንዲጠበቅ ምን መተማመኛ ይገኛል? የጎደለው ከዓለም መንግስታት አሳብ ነው እንጂ ከመንግስታት ማኅበር ውል አይደለም፡፡የመንግስታት ማኅበርተኛው በሆነው በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ሆኜ የመንግስታት ማኅበር ውል እንዲከበር የሚያስፈልገው ነገር እንዲፈፀም ጉባኤውን እጠይቃለሁ፡፡በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከውል የተላለፈ ነገር ስለተደረገበት በዚሁ በተደረገበት ግፍ ምክንያት ከዚህ ቀድሞ ያቀረብሁትን በመቃወም አሁንም እንደገና እቃወማለሁ፡፡ በዓለም ፊት ሆኜ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት የኢትዮጽያ መንግስትና ሕዝብ በኃይል የተደረገባቸውን ነገር አይቀበሉም፡፡ስርዓት እንዲያሸንፍ የመንግስታት ማኅበር ውል እንዲከበር የሚገባቸውም ስልጣንና ግዛት እንዲመለስላቸው የሚቻላቸውን ነገር ሁሉ ማድረጋቸውን እገልጣለሁ፡፡
በተጠቃችሁ ጊዜ አጥቂ እንዳያሸንፋችሁ እንረዳችኋለን ብለው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል ኪዳን የገቡት 52 መንግስቶች ቃል ኪዳናቸውን አፅንተው እንዲረዱ እርዳታቸውን እጠይቃለሁ፡፡ ለኢትዮጵያ ምን ልታደርጉላት ትፈቅዳላችሁ? ታናናሽ መንግስቶች እንዳይጠፉ በኢትዮጵያ የደረሰባት እድል እንዳይደርስባቸው መንግስቶች እንዲረዳዱ መተማመኛ ለማድረግ ቃል ኪዳን የገቡትም ታላላቅ መንግስቶች የኢትዮጵያ ነፃነት እንዳይጠፋ፣ ግዛቷም እንዲከበር ምን አይነት እርዳታ ለማድረግ አስባችኋል?እዚህ የተሰበሰባችሁ የዓለም እንደራሴዎች ሆይ፣ አንድ ንጉሠ ነገሥት በደረሰበት ሃዘን ማድረግ የሚገባውን ሥራውን ለመፈፀም ጄኔብ ወደ እናንት መጥቻለሁ፡፡ለሕዝቤ ምን ምላሽ ልውሰድለት??

ሰቆጣ


ሰቆጣ

ሰቆጣ
ሰቆጣ.jpg
ሰቆጣ ከተማ
ከፍታ2266 ሜትር
አገርኢትዮጵያ
ክፍላገርሰሜን ወሎ (ላሳታ)
የሕዝብ ቁጥር13፣700
ሰቆጣ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ሰቆጣ
ሰቆጣ (ኢትዮጵያ
)

ሰቆጣ ፣ ከ1956 ጀምሮ የዋግ አውራጃ ማዕከል እና የሰቆጣ ወረዳ ዋና ከተማ ነው። ከሰቆጣ 6 ኪሎ ሜትር ወጣ ብሎ የውቅሮ መስቀል ክርስቶስ አለት ውቅር ቤ.ክ. ይገኛል። በዚሁ ቤተ ክርስቲያንላስታን ከሰቆጣ ሆነው ያስተዳደሩ ዋግሹሞች ደረቅ ቅሪቶች ይገኛሉ።

ማውጫ

 [ይደበቅ]

[ለማስተካከል]ታሪክ

አክሱም መዳከም በኋላ በአረብ ጸሐፊዎች ዘንድ እንደ የኢትዮጵያ ዋና ከተማነት ብዙ ጊዜ የሚጠቀሰውኩባር የተሰኘው የጥንቱ የኢትዮጵያ ገናና ማዕከል ሰቆጣ እንደነበር በታሪክ ግንዛቤ አለ[1]። ስለሆነም ይመስላል፣ ላስታን በዋግ ሹም ማዕረግ ያስተዳደሩ ገዢዎች መቀመጫቸው ሰቆጣ ነበር።
ከጥፋት በተረፉ መዝገቦች ዘንድ ሰቆጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሶ የምናገኘው በ1738ዓ.ም. ሲሆን፣ ዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ወደ ላስታ ባደረጉት ዘመቻ ሰቆጣ ውስጥ በዋግ ሹም ነዓኩቶ ለአብ(የዋግ ሹም ቴዎድሮስ አባት) ቤት ለ5ቀን እንዳረፉ ዜና መዋዕላቸው በማተቱ ነው [2][3]
ከዚያም በ19ኛው ክፍለ ዘመን ብዙ የአውሮጳ ተጓዦች ሰቆጣን ሲጎበኙ፣ ዋልተር ፕላውዴን ለምሳሌ በኢትዮጵያ ከሚገኙ 5 ብቻ ነጋድራሶች አንዱ በሰቆጣ ይገኝ እንደነበር መዝግቧል። ከዚያም በ1800ዎቹ መጨረሻ ሰቆጣን የጎበኘው ኤ.ቢ.ዋይልድ ሰቆጣን የላስታ ዋና ከተማ አድርጎ ሲጠቅስ፣ የሰቆጣ ቤተ መንግስት ባለ ሶስት ፎቅና በ1650ዎቹ የተገነባ እንደነበር ያትታል። ቤተ መንግስቱን የሰሩት የፋሲል ግቢን አናጺዎ እደሆኑም መላምት ያቀርባል[4]። ይሄው የአውሮጳ ተጓዝ፣ በ1880ዎቹ የሰቆጣ ገበያ ከአካባቢው ካሉት ሁሉ ግዙፉ እንደነበር ፣ የዝሆን ጥርስ እና በቅሎ ገበያው የደራ እንደነበር፣ እንዲሁም 21፣000 በሬዎች፣ 2፣900 ላሞች፣ 10ሺህ ፍየሎች፣ 1፣500 በጎች በየአመቱ ለግብይት ይቀርቡበት እንደነበር ሳይጠቅስ አላለፈም[5] ።
ጥር2፣ 1929 ጣሊያኖች በሰቆጣ ላይ የመርዝ ጋዝ ቦምብ እንደጣሉ በታሪክ ተመዝግቦ ይገኛል[6]። ከሶስት ወር በኋላ ሰቆጣን ሲቆጣጠሩ፣ ለከተማው መንገድ በመስራት እና የአካባቢውን መስጊድ በማደስ ይታወቃሉ። በዚህ ወቅት የህቡ ቁጥር 4500 ነበር [7]

በ1972ዓ.ም. ሰቆጣ ለተወሰነ ጊዜ በህ.ወ.ሐ.ት ቁጥጥር ስር የነበር ሲሆን ከዚያም በኋላ የቀድሞኢ.ሕ.አ.ፓ አባል ቡድኖች ያቋቋሙት ኢ.ህ.ዴ.ን ከ1982 ዓ.ም. ጀምሮ የትግሉን ማዕክል በሰቆጣ አድርጎ ነበር[8]። በዚህ መሃል የተነሳውና ለብዙ ሰዎች መጎሳቆልና ሞት ምክንያት የሆነውየ77ቱ ድርቅ ሰቆጣን ያማከለ ነበር። በወቅቱ ከተማዋ ምግብ የምታገኘው ከኮረም እንደነበርና ይህ የፈጠረውን ችግር የተባበሩት መንግስታት የዕርዳታ ሃላፊ በኢትዮጵያ፣ ከርት ጆንሰንዘግቦት ይገኛል [9]

[ለማስተካከል]ሰቆጣ፣ ከተማው

ሰቆጣ፣ ከሌሎች ከተሞች ለየት ባለ መልኩ ክብና ሁለት ፎቅ ባላቸው ቤቶች የተመላ ነው። እንዲሁም አብዛኛዎቹ ቤቶች ሁለት ግድግዳ ሲኖራቸው በኒህ ሁለት ግድግዳዎች መካከል ወደ ፎቁ የሚያወጡ ደረጃዎች ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት ወደሰቆጣ የሚሄዱ ሁለት መንገዶች ይገኛሉ። አንዱ ከኮረም ሲሆን ሁለተኛው ከወልደያ ተነስቶ በላሊብላ አድርጎ ሰቆጣ የሚደርስ ነው።

[ለማስተካከል]የህዝብ ብዛት

እንደ 1997 ህዝብ ቆጠራ፣ ሰቆጣ ውስጥ 13፣700 ሰዎች ይኖራሉ [10]

[ለማስተካከል]ማጣቀሻ

  1. ^ Philip Briggs, Ethiopia: the Bradt Travel Guide, third edition (London: Bradt, 2002), p. 302. The problem of Ku'bar is discussed by Taddesse Tamrat, Church and State in Ethiopia (Oxford: Clarendon Press, 1972), p. 37.
  2. ^ የዳግማዊ ዓፄ ኢያሱ ዜና መዋዕል፣ ገጽ
  3. ^ [7th Int. Conf. of Ethiopian Studies 1984 p 224-225]
  4. ^ [7th Int. Conf. of Ethiopian Studies 1984 p 219]
  5. ^ Augustus B. Wylde, Modern Abyssinia (London: Methuen, 1901), p. 494
  6. ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/s/ORTSEK05.pdf
  7. ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/s/ORTSEK05.pdf
  8. ^ [12th Int. Conf. of Ethiopian Studies 1994]
  9. ^ http://www.nai.uu.se/library/resources/dossiers/local_history_of_ethiopia/s/ORTSEK05.pdf
  10. ^ CSA 2005 National Statistics, Table B.3

‹‹ልትሾም ነው››


http://www.ethiopianreporter.com/editorial/294-editorial/2746-2011-07-23-07-38-18.html
‹‹ልትሾም ነው
‹‹ከዕለታት አንድ ቀን አንድ ሰው በውድቅት ሌሊት አፍላ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወስዶት ሳለ አሰቃቂ ሕልም ያያል፡፡
››
ሕልም አላሚው በሁኔታው ተደናግጦ አይ ዘንድሮስ መሞቴ ነው መሰል አለ፡፡

በዚህም ምክንያት የመንፈስ መረጋጋት ስላጣ ባቅራቢያው ወደሚገኝ ሕልም ተርጓሚ ካህን ሔደና ‹ዛሬ አሰቃቂ ሕልም አየሁ፣ መሞቴ ነው መሰለኝ› አለው፡፡

‹ሕልምህ ምንድን ነው? እስቲ ንገረኝ አለው› ሕልም ተርጓሚው ካህን፤
‹በውድቅት ሌሊት አፍላ እንቅልፍ ጭልጥ አድርጎ ወስዶኝ ሳለ፣ እጅ እግሬ ሽባ ሆኖ፣ ዓይኔ ታውሮ፣ ጆሮዬ ደንቁሮ አየሁ፡፡ ብንን ብል ሕልም ሆነ› አለው፡፡

‹አትሞትም አይዞህ፣ አትሞትም፣ ልትሾም ነው› አለው ተርጓሚው ካህን፡፡

‹እንዴት ልትሾም ነው?› አለና የሕይወት ሞት ሞተ ሕልመኛው፡፡ ሕልም ተርጓሚው እንደተገለጠለት ሕልሙን ይተረጉምለታል፡፡

‹ስማ! እጅ እግርህ ሽባ ሆኖ ማየትህ፣ ዱሮ ወዲህና ወዲያ እየተሯሯጥክ ላገርህ፣ ለወገንህ፣ ለራስህ የሚጠቅም ሥራ ትሠራ ነበር፡፡ ከተሾምህ ግን ይህ የትሩፋት ሥራ የለም፡፡ ሹም ነህ ተብለህ፣ እጅ እግርህን ኮርትመህ መቀመጥህ እኮ ነው፡፡ ዓይንህን ታውሮ ያየኸውማ ላገር፣ ለሕዝብ፣ ለወገን ጉዳይ ሰው ሊያነጋግርህ በግር በፈረስ ሲፈልግህ ይህን ጋጋታ ማየት አትፈልግም፡፡ ከበር የሚቆመው አጋፋሪህ ከእንግዳ ጋር ናቸው፤ ሥራ ይበዛባቸዋል፤ ወደ ውጭ ሊሔዱ ነው፤ ከዚህ ወግድ እያለ ፈላጊህን ሁሉ ያባርረዋል፡፡ ስለዚህ ዓይንህ ከሌላው ሰው ይሰወራል ይጨፈናል፡፡

‹ጆሮህ መደንቆሩ ደግሞ ድሀው ሕዝብ፣ ሥራ አጡ፣ በሽተኛው፣ አቤት ባዩ፣ መንገደኛው፣ ፍርድ የጐደለበት፣ ግፍ የተሞላበትም ሁሉ ዋይ ዋይ፣ አቤት አቤት፣ ሲል የድሀውን ዋይታ፣ የድሀውን አቤቱታ አትሰማም› አለውና አጠቃልሎ አስረዳው፡፡››

ይህ ከፍ ብለን የጠቀስነው ሕልምና ፍቺ ከሦስት አሰርት ዓመታት በፊት የተጻፈና በመጽሐፍም የታተመ ነው፡፡ ሕልም ተርጓሚው ካህን እንዳለው በሕዝብ ላይ መሾም ሕዝብን ለማገልገል እንጂ፣ በሕዝብ ላይ ለመገልገል መሆን የለበትም የሚለው መልዕክት ዛሬም እውንም፣ አንገብጋቢም በመሆኑ ግን ልንጠቀምበት ተገደናል፡፡

ሁሉም ሹመኛ በሕዝብ እየተገለገለ አይደለም፡፡ ሕዝብን ለማገልገል የሚፈልጉና የሚንቀሳቀሱም አሉ፡፡ አሌ የማይባለው ግን በሕዝብ መገልገል የሚፈልጉ ሹመኞች እየተበራከቱ መምጣታቸው ነው፡፡

‹‹ልትሾም ነው›› የሚለው አባባል፣ ሕዝብን ለማገልገል ኃላፊነት ልትወስድ ነው መሆኑ ቀርቶ፣ ‹‹ልትገለገል ነው››፣ ‹‹ልትጠቀም ነው›› ሆኖ እየመጣ ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ በኅብረተሰቡ ብዙና የተለያየ አቤቱታና ቅሬታ አለ፡፡ መንግሥት ለምን ይህን ያደርጋል? ለምን እንደዚህ ዓይነት መመርያ ያወጣል? ወዘተ. የሚል፡፡ እነዚህን አቤቱታዎችና ቅሬታዎችን ተንቀሳቅሶ የሚከታተል አካል፣ የሚያይ ዓይንና የሚያዳምጥ ጆሮ ቢያገኙ ኖሮ በቀላሉ የሚፈቱና ከመግባባት ላይ የሚደርሱ ናቸው፡፡ የሚንቀሳቀስ እግር፣ የሚያይ ዓይንና የሚያዳምጥ ጆሮ ስላጡ ግን ቅሬታዎችና አቤቱታዎች ሊወገዱ አልቻሉም፡፡

በአከራይ ገቢ ላይ ታክስ ተጨምሯል ብሎ ቤት አከራይ እያማረረ ነው፡፡ በቃል እንጂ በመመርያም አይደለም የሚል አቤቱታም አለ፡፡ አስፈላጊ ነው ብሎ መንግሥት ካመነበት በመመርያ ወይም በአዋጅ አውጥቶ ከአከራይም ጋር ተወያይቶና አሳምኖ ማድረግ ይችላል፡፡ የጽሑፍ መመርያ ወይም ሕግም ስለሌለ፣ የሚያስረዳም ስለሌለ ግን ቅሬታ ይሰማል፡፡

ግብር ጨምሩ ተብለናል ብለው ቅሬታ የሚያሰሙ ባለጥቃቅን ንግዶች በርካታ ናቸው፡፡ ሁለት ሺሕ እንከፍል የነበረ ሃያ ሺሕ ክፈሉ ተባልን እያሉም አቤት እያሉ ናቸው፡፡ የሚያስረዳና የሚያወያይ ስለሌለ ቅሬታ አለ፡፡ ቀረብ ብሎ የሚያዳምጥ፣ ቀረብ ብሎ የሚያይ፣ እየተንቀሳቀሰም ችግሩን የሚያጠናና አወያይቶ የሚያሳምን ካለ በቀላሉ የሚፈታ ነበር፡፡

የንግድ ፈቃድ አሳድስ የሚለውም ብዙ መንከራተት እያስከተለ ነው፡፡ ውል ክፍል መሔድ፣ ባንክ መሔድ፣ ውጭ የነበረ ሰው እባክህ ተመለስና ጨርስ ብሎ መለመን ወዘተ.፡፡ ለምን ይታደስ ተባለ አንልም፡፡ ምክንያት ይኖራል፤ በተጨማሪም ግልጽና ሕጋዊ የሆነ ፈቃዶች እንዲኖሩ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን አንዱ እስከ ሐምሌ 30 ይላል፤ ሌላው እስከ ሐምሌ 15 ይላል፤ ሌላው የብቃት ማረጋገጫ አምጡ ይላል፤ ሌላው ይታሸጋል ይላል፤ ሌላው ሰባት ዓመት ያሳስራል የሚል ወረቀት ይጽፋል፡፡ ውጥንቅጡ ይወጣል፡፡ ቀላሉ ይካበዳል፤ በመግባባት የሚፈታውን ቅሬታ ያወሳስበዋል፡፡

ለምን ታክስ ተጨመረ አይባልም፤ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፡፡ ለምን ታክስ ክፈሉ አይባልም፤ ታክስ የግድ መክፈል አለበትና፡፡ ለምን ፈቃድ ይታደስ ተባለ አይባልም፤ መታደስ አለበትና፡፡

ችግሩ ያለው ተደራርቦ ሲመጣ፣ ማስፈራት ሲታከልበት፣ አለበለዚያ ሲበዛበት ያ በቀና መንፈስ ሲሠራ የነበረም ምን እየሆነ ነው ብሎ መደናገርና መረበሽ ይፈጠርበታል፡፡

መረጋጋት በንግድ ዓለም አስፈላጊ ነው፡፡ መንግሥት ያዳምጥ፤ እየተንቀሳቀሰ ያጥናና ያረጋግጥ፤ ችግሩንም ይመልከት፤ እየተወያየም መፍትሔ ያስቀምጥ፤ ያኔ ሁሉም ነገር ቀላል ይሆናል፡፡

ዋናው ቁም ነገሩ ከታች እስከላይ ያለ ሹመኛ እግሬም፣ ዓይኔም፣ ጆሮዬም ሕዝብን ለማገልገል እንጂ ሕዝቡ እንዲያገለግለኝ አልጠቀምበትም ብሎ ማረጋገጥ አለበት፡፡  
ምንጨ ።http://www.blogger.com/post-edit.g?blogID=6975122765494067198&postID=4365213638690244223

በርካታና ትላልቅ የልማት፣ የፍትሕ፣ የዴሞክራሲም አጀንዳዎች ስላለን በጥቃቅን ቅሬታዎች አናደብዝዛቸው፤ እንቀራረብ፤ እንተያይ፤ እንደማመጥ፤ እንመካከር፡፡
አሁኑኑ!!

“ኢቲቪ አቋሙን ይለይልን! “ የህዝብ ነው? ወይስ .. በህዝብ ስም የሚነግድ ፖርቲ


ኢቲቪ አቋሙን ይለይልን! “ የህዝብ ነው? ወይስ ..
በህዝብ ስም የሚነግድ ፖርቲ
BY DR,. ZERHUN BERHANU 
ኢቲቪ በልማታዊ ጋዜጠኝነት ሰበብ፣ በዕውቀት አጠር ጋዜጠኞቹ የፖርቲ አባልነት ሽፋን መረጃዎችን የመድፈቅ የማስተባበል ስራ የሚሰራ ሆኗል፡፡
እንደ መገናኛ ብዙሃን፤ አንገት የሚያስደፋ  የፖርቲ ልሳንነቴን የሚያረጋግጥ ተራ እየሆነብን ተቸግረናል፡፡
ልማታዊ ጋዜጠኝነትን ከታትለሁ  የሚለው ኢቲቪ ፤ አይዞህ ባይ ካላገኘ የማይናገር፣ የሚመራው  ካላኘ የማይሄድ፤ በርታ ካላሉት አሻግሮ የሚያያ ሆኖብናል፡፡ ይህንን ያስባለኝ በቀን 03/12/2003 ዓ.ም BBC ባሰራጨው  አርሶ አደሩ ግብአቶችን በፖርቲ አባልነት አላገኘም የሚል ዜና ተከታትሎ  የተሰራ ዜና ነው፡፡
ሰሞኑን የተቃዋሚ ፖርቲዎች  የሰጡት መግለጫ ራሱን ያሳመመው ኢህአዴግ / ኢቲቪ / በመረጃው ላይ የተጨፈነ  የትንታኔ ቅኝት በአድር ባይ ያልበሰሉ ሪፖርቶች አቀራረብ ሰልችቶናል፡፡
ዘገምተኛ በሚመሰል ጋዜጠኛ የሚተንተኑ ተረት አውጊ፣ የፖርቲ ልሳን ያልተገራ ግብር በምንከፍልበት ቴሌቪዥን ሲመጣ  እራሳችንን ያመናል፡፡
ቢያንስ እንኳ እንደ ጋዜጠኛ መረጃውን ሚዛናዊ ማድረግ ምን ይከብዳል BBC እንኳን የቀረበዉን ሃሳብ ከሁሉም የመንግስት አካላት አካቶ የሰራውን ዜና ቡራ ከርዩ ብሎ በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ልሳንነቱ የአንድን ጥግ ይዞ መነሳት አሳፋሪ ነው፡፡
በእርግጥ መሰረቁ እራሱን አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ቴሌቪዥን ሲል ቢሰይም የሚሻለውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነኝ ብሎ ሚነግድብን ምን አረግን ነው፡፡ የት ለይ እንተንፋስ ? ማንን እንመን ?
ደስ ሲለው እነ አሞራውን የታሪካቸው አካል አድርጉ እያሉ የሚያስገድድ፣ የአንድ ፖርቲ አቋም በውስጣችን  እንድናሰርፅ የሚጫነን  ምርግ ሆነ፡፡
መቼ ነው ከሚነፍስበት ንፋስ ነፃ የሚወጣው? “ነፃ  አስተሳሰብ ለተሻለ ህይወት” አለ ራዲዮ ፋና
በመረጃ ዘመን የተቆለፈ የግብርና ነፃነታችን የበለጠ መታገዝ የሚ¯ምረው፡፡ እኔ ላስብላችሁ … እኔ ልናግራላችሁ … እኔ ልፈፅምላችሁ ከማለት መላቀቅ የሚቻለው እንዴት ነው?
እውነታውን በውሸት ልማት ፣ መሸፈን የሚቀርበት ዘዴ ብንፈልግስ ሠሞኑን ኢህአዴግ ኪራይ ሰብሳቢው መቆረጥ አለበት ብሎ ሲል መድረክ ፈጠረ፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ እንዴት አድርገው  እንደበዘበዙን ተናዘዙ፣ ለውጥ ባይኖረውም፣ እየተፈራራ የተሸፋፈነውን ሳይጨምር ታዲያ ልሳኖች ተናዘዙ፡፡ በዚህ ሰዓት ሚዲያውን ያማረሩ የባህር ዳር  ከተማ ኗሪዎች ተጠቃሺ ናቸው፡፡ በውሸት ሀብታም ናቸው ተባልን፡፡ አመራሩ የሌለንን አላቸሁ፣ ሚሊኒየር ሁናችኋል እያለ ሲያውጅብን ምን እናድርግ፣ ተደራጅተው… ከድህነት ወጥተዋል እያሉ  ያነበንባሉ እኛ ግን አሁንም በድህነት ውስጥ ነን ሲሉ መሰከሩ፡፡
ኧረ ይህንስ አላወቅንም፤ ኧረ ይህንስ አልሰማንም በሚል መሪ ብንታጅብም፡፡
ለማንኛውም  መንግሥትን በሃሳብ  በልፅገዋል አትበሉን ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ውስጣችን አሁንም ድሃ ድሃ የሚሸት ውኃ ነነ ብለዋል፡፡ ከሚኖሩት በላይ ምን መስካሪ አለ፡፡ ካለፈበት በላይ  ማን ተናጋሪ አለ፡፡
ሌላው የኢቲቪ መረጃ የቃለ መጠይቅ አደረጀጀት ሁሌም ባጭሩ ሪፖርተሩ የሚፈልገውን ነግZህ እን­ትነግረው መደረጉ ለየት የሚያደርገው ባህሪ ነው፡፡

አንዱ የሀገራችን  ታሪክ አለ: አፄ ቴዎድሮስ ልጃቸውን አለማየሁን ይዘው  ይንጎራደዳሉ፡፡ ታዲያ ልፁል አለማየሁ የደላው ነው፡፡ ምንም አልቸገረውም እንደ አሁኖቹ የነገስታታ ልጆች  ቤተ መንግሥት ገብቶ ድሎቱ  ባያስጨንቀውም  በአቅሙ የንጉስ ልጅ አደል ሰባት አጫዋች ነበረው፡፡ የአንዷ ጀርባ አልመቸው  ሲል ሌላዋ ጀርባ ላይ እያለ  ይንደላቀቃል፡፡
ታዲያ ከአባቱ ጎን ቁሞ ” አባየ ሺፍታ ነህ ይሉሃል” ይለዋል “ሺፍታ አሉኝ ልጄ አዎ ለነፃነት፣ ለሀገር ዕድገት፣ ጫካ  ዱሩን ሳማትር ማድር የሃገርን ልዕልና፤ የምናፍቅ ሺፍታ ነኝ…” ይመልሳል አባዬ ድሃ ነህ ይሉሃል?”ይጠይቀዋል፡፡ “ይህንም ነገሩህ ልጄ አዎ የኮሶ ሻጭ ልጅ ድሃ ነኝ” ድሀ ስትሆን ልጄ ስትናገር የሚሰማህ፤ እንዳትስብ የሚያስርህ፤ ተናግረህ የሚያዳምጥህ ታጣለህ፤ ድህነት፤ የመንፈስ የቁስ ረሃብ ነው፡፡ እንዴት አድርጌ ላስረዳህ ተወው… ልዑል ድህነት ባፍ አይገባም ስትኖረው ስትኖርበት ብቻ ነው የ ሚገባህ “አዎ ሀብታምነትም በአፍ አይገባም፡፡ ባልኖርንበት  ባለፀግነት፤ ኢቲቪ የሚሰጠን ስያሜ አስከፍቶኛል ነው ጥያቄው፡፡እየኖርንበት ያለውን ድህነት ለማጥፋት ድሃውን ድሃ ማለት ካልተጀመረ በጣም ያስቸግራል፡፡ ምናልባት ልማታዊ ጋዜጠኝነትም የራሱ ነፃነት ቢኖረውም ለአፋኝና ጨቋኞቹ ተነቦ የሚተረጉም የፍላጎት መጠመዘዣ የጋዜጠኝነት የእስያ ፍልስፍና ነው፡፡
በአሁኑ ሰዓት ለሃገራችን፣ የድህነት ወለል ጋዜጠኝነት /Poverty Land reporting/ ቢኖረን ሚሻል ይመስለኛል፡፡ ህይወት ህይወት በሚሸት ዘገባ ድህነትን እያሳየን እንድንሸሸው  ብናስተምር በነፃነቱ ቀይጠን የታፈነበትን የፖለቲካ ድህነት ብንዘግብ አማራጭ አይሆንም ትላላችሁ፡፡
ወደ ቀድሞ ነገሬ ልመለስ፥
አሁንም ቢቢሲ ስላለ ብቻ ሣይሆን ተርበናል፤ ተጠምተናል፣ ማየት ተስኖናል፡፡ ችግራችንን የሚያያ መሪ፤ የተራበን ህዝብ ደጀን የሚሆን አካል እንፈልጋለን፡፡
የአሁኑ ርሃብ የተጋረጠብን ችግር ሂደቶች ሲታዩ  ከኃይለስላሴ  የክፉ ቀን ረሃብ በምን ይለያል ? ተብሉ  ተብሎ ራሳቸው የከበዳቸው ወገኖቻንን ፎቶ ሲወጣ የሚባንን መንግስት ለኔ ሁሌም ጥያቄ ያጭርብኛል፡፡
ምሣሌ የምናገራቸው ምዕራባዊያን በሚዘዋወሩት የሚዲያ ዓለም እነሱ ካላዩን እኛ እራሳችንን እንዳናይ ተረግመናል፡፡ ሂውማን ራይትስዎች ኤርትራን ከወቀሰ ኢቲቪ በደስታ ፈንጥዞ ሪፖርቱን በቀን አስሪ ያቀርበዋል፡፡ ኢትዮጵያንን የተመለከተ መረጃ ያወጣ ሰሞን ደግሞ "ምንነቱ ያልተወቀ ድርጅት እየተባለ ስሙ  ይብጠለጠላል"፡፡ ሃገሪቱን ሲያሞገስ  ደግሞ ሲምገሳ ይከርማል፡፡  ኢቲቪ የኢህአዴግ ግንባር ነው ወይስ የህዝብ መገናኛ ብዙሃን፡፡
ያለውድ በግድም ስንደሰት  ምናመሰግነው፤ ሲከፋን ብሶታችንን የምንገልጽበት የግል ሚዲያ ዘርፍ ይከፈትልን፡፡ ብሶታችንን የፖርቲ ልሣን ጋዜጠኞች ግን ልንለቅ ስለምንችል መፍትሄ እንሻለን፡፡ ኢቲቪ ግን አቋሙን ይለይልን

የህዝብ ነው ወይስ ?
በህዝብ ስም የሚነግድ ፖርቲ!